Popular Posts

Thursday, March 5, 2020

በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም


እግዚአብሄር በሰው ሃጢያት ምክኒያት ምድርን በውሃ ካጠፋ በኋላ እግዚአብሄርን እንዲህ አለ፡፡
ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ አቆማለሁ፤ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም። ኦሪት ዘፍጥረት 9፡11
እግዚአብሔርም በልቡ አለ፦ ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰው አልረግምም፥ . . . ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና አልመታም። ኦሪት ዘፍጥረት 8፡21
እግዚአብሄርም አለ፡- በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም። ኦሪት ዘፍጥረት 8፡22
ይህ ታላቅ የምስራች ነው፡፡ በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ አይቋረጥም፡፡
አንዳንድ ጊዜ በመዝራት ፣ አሁንም በመዝራት አሁንም ደግመን በመዝራት ላይ ብቻ እንዳለን ይመስለናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ መዝራት መዝራት ብቻ እንጂ ማጨድ እንደማይመጣ ይሰማናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ መዝራት እንጂ ማጨድ እንደተቋረጠ ይሰማናል፡፡  
የምስራቹ ግን መዝራትና ማጨድ አይቋረጥም፡፡ እየዘራን ነው ማለት ልናጭድ ነው ማለት ነው፡፡ እያጨድን ነው ማለት መዝራት አለብን ማለት ነው፡፡
መዝራትና ማጨድ የማይለያዩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ መዝራት ካለማጨድ አይሆንም ማጨድ ካለመዝራት አይሆንም፡፡ የምንዘራው ለማጨድ ነው የምናጭደው ለመዝራት ነው፡፡
መዝራትና ማጨድ አይቋረጡም፡፡ ህይወት የሚቀጥለው በመዝራትና በማጨድ ህግ ብቻ ነው፡፡ መዝራትና ማጨድ ተቋረጠ ማለት ህይወት ተቋረጠ ማለት ነው፡፡
ትግስት ይጠይቅ እንጂ ስንዘራ በጊዜው እንደምናጭድ እያወቅን ሊሆን ይገባዋል፡፡ ስናጭድ የመዝራት ሃላፊነታችንን እየተረዳን ሊሆን ይገባዋል፡፡ የብርድና የሙቀት መለዋወጥ እንደማይቋረጥ የመዝራትና የማጨድ ጊዜ እንዳለና እንደማይቋረጥ ሊያስታውሰን ይገባል፡፡
ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡10
ስንዘራ እንደምናጭድ አውቀን በተስፋ ልንዘራ ይገባናል፡፡ ስናጭድ ልንዘራው የሚገባንን ዘር  እያጨድን እንደሆነ ልንዘነጋው አይገባም፡፡ ሌትና ቀን እንደማይቋረጥ መዝራትና ማጨድ አይቋረጥም፡፡  
አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡7
መዝራትና ማጨድ አይቋረጥም፡፡ ማተኮር ያለብን ምን እንድምንዘራ በዘራችን ላይ ብቻ ነው፡፡ ዘራችንን እንጂ የምናጭደውን ዘራችን እንጂ እኛ አንወስንም፡፡
የመዝራትና የማጨድን ህግ እንለውጠውም፡፡ መለወጥ የምንችልው ምንም እንድምንዘራ እና እንዴት እንደምንዘራ ብቻ ነው፡፡
ይህንም እላለሁ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡6
እግዚአብሄርም አለ፡- በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም። ኦሪት ዘፍጥረት 8፡22
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #መዝራት #ማጨድ #ክረምት #በጋ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment