Popular Posts

Saturday, March 14, 2020

የቸኮለ ፀሎት

በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14
ስለፀለይን ብቻ እግዚአብሄር አይሰማንም፡፡ እግዚአብሄር የሚሰማው ፀሎት እንደ እርሱ ፈቃድ የተፀለየውን ፀሎት ነው፡፡ ስለዚህ ከመፀለይ በፊት የሚቀድመው ፈቃዱን ማግኘት ነው፡፡ የፀሎት ዋናው ክፍል የፀሎት ቃልን መናገር ሳይሆን ስላለንበት ሁኔታ የእግዚአብሄር ፈቃድ መረዳት ነው፡፡ የፀሎት ንግግር ከመናገር ያላነሰ አስፈላጊው ነገር የእግዚአብሄን ፈቃድ መረዳት ነው፡፡ መፀለይ ስለምንፈልገው ነገር አንድ ጊዜ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከተረዳን የፀሎት ንግግርን መናገር የሰከንዶች ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡
እግዚአብሄር እንደ ፈቃዱ ያልሆነውን ጸሎት ሁሉ አይሰማም፡፡ ፈቃዱን ሳናገኝ የምንፀልየው ፀሎት እንደ ፈቃዱ ሊሆን ስለማይችል በእግዚአብሄር አይሰማም፡፡
እግዚአብሄር የሚሰማው እንደ ፈቃዱ የሆነውን ፀሎት ብቻ ነው፡፡ የእኛ ድርሻ ፈቃዱን ከእግዚአብሄር ፈቃድ ፈልገን ማግኘትና እንደፈቃዱ መፀለይ ብቻ ነው፡፡  
እግዚአብሄር የሚሰማው እንደእግዚአብሄር ፈቃድ የሆነውን ፀሎት ነው ማለት ደግሞ ሁልጊዜ በፀሎታችን መጨረሻ "እንደ ፈቃድህ" ወይም "ፈቃድህ ቢሆን" የሚለውን ቃል እናስገባለን ማለት አይደለም፡፡
አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሄርን ፈቃድ ፈልገው ለማግኘት አይተጉም፡፡ ከመፀለያቸው በፊት የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመረዳት የእግዚአብሄርን ቃል ከማጥና ከማሰላለስ እና በአግባቡ ከመረዳት ይልቅ ሲፀልዩ ብቻ "እንደ ፈቃድህ" ወይም  "ፈቃድህ ቢሆን" የሚል ቃልን በማስገባት እንደፈቃዱ የፀለዩ ይመስላቸዋል፡፡ "እንደ ፈቃድህ" ወይም  "ፈቃድህ ቢሆን" የሚለውን ቃል በፀሎታችን መካከል በማስገባት የምንፀልየውን ነገር እንደእግዚአብሄር ፈቃድ አናደርገውም፡፡ የምንፀልየውን ነገር እንደ እግዚአብሄር ቃል የሚያደርገው ከመፀለያችን በፊት መፀለይ ስለምንፈልገው ነገር የእግዚአብሄርን ፈቃድ ፈልገን ማግኘት ነው፡፡  
እንደፈቃዱ የምንለምነውን ይሰማናል ማለት ፈቃዱን ለማግኘት የእግዚአብሄን ቃል መፈለግ ማንበብ መረዳት አለብን ማለት እንጂ እንደው በፀሎት መጨረሻ "እንደ ፈቃድህ" ወይም "ፈቃድህ ቢሆን" የሚል ቃል እናስገባበታለን ማለት አይደለም፡
የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከእግዚአብሄር ቃል አግኝተን እንደፈቃዱ ከፀለይን ይሰማናል እንደሚሰማን ካወቅን ደግሞ እንደምንቀበል እናውቃለን፡፡
በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15
ነገር ግን ስለ ሁኔታችን የእግዚአብሄርን ቃል ሳንረዳ "እንደ ፈቃድህ አድርግ" ወይም "ፈቃድህ ቢሆን" የሚሉትን ቃላት በማስገባት ብቻ ስለፀለይን እንጂ እንደፈቃዱ ስላልፀለይን እግዚአብሄርን እንደሚሰማን አናውቅምን፡፡ እንደሰማን ካላወቅን ደግሞ እንደምንቀበል አናውቅም፡፡
ኢየሱስ በእንድ ስፍራ ራሱን ለመስጠት ፈቃድህ ቢሆን ብሎ ፀልዮዋል፡፡
ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ። የማቴዎስ ወንጌል 26፡39
ከዚህ ስፍራ ውጭ እንደ ፈቃድህ ወይም ፈቃድህ ቢሆን እያለ ከመፀለይ ይልቅ ፈቃዱን ተረድቶ እንደ ፈቃዱ በድፍረት ሲጠይቅ እንመለከተዋለን፡፡
ድንጋዩንም አነሡት፦ ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ፦ አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ። የዮሐንስ ወንጌል 11፡41-42
በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ምስጋና

No comments:

Post a Comment