Popular Posts

Wednesday, July 20, 2016

መሪዎች ያስፈልጉናል - መሪ እንሁን


በጋራ ወደ ውጤት ለመድረስ መሪ ወሳኝ ነው፡፡ ካለ መሪ ሰዎች አንድነትም ሆነ የጋራ ቅንጅት ብሎም ወደ ውጤትና ስኬት ሊደርሱ አይችሉም፡፡ 

 
በቤተሰብና በቤተክርስቲያን የእግዚአብሄር ሰዎች ካሉበት ቦታ አግዚአብሄር ወዳየላቸው የክብር ቦታ እንዲደርሱ መሪነት አማራጭ የሌለው ፍላጎት ነው፡፡ 


በራእይ የሚያስተባብር መሪ በሌለበት ህዝብ መረን ይወጣል፡፡ 


መሪነት ደግሞ ስልጣን ወይም ማዕረግ ሳይሆን ተፅእኖ ነው ፡፡ የመሪዎች ህይወታቸው ፡ መሰጠታቸው ፡ ቅናታቸውና  ትጋታቸው በተመሪዎች ላይ ተፅእኖ ያደርጋል ሰዎችም በደስታ ይከተሏቸዋል፡፡ 


መሪዎች ራእይ ያላቸው መንገዱን የሚያውቁ ሌሎችን በድፍረት በመምራት ወደ ውጤትና ስኬት የሚያደርሱ ናቸው፡፡ 


እንደ እነዚህ አይነት መሪዎች ያስፈልጉናል፡፡ እንደ እነዚህ አይነት መሪዎች እንሁን ፡፡ 


ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ! 





Monday, July 18, 2016

በላይ ያለውን እሹ

ከክርስቶስ ጋር በትንሳኤ በመነሳታችንና በሰማያዊ ስፍራ ከክርስቶስ ጋር በመቀመጣችን እንዲሁም በሰማያዊው በረከት ሁሉ ከመባረካችን የተነሳ ሰዎች የሚጋደሉለት የምድር ነገር አያጓጓንም ፡፡
ለጊዜያዊ ደስታ ብለን አባታችንን እግዚአብሄርን ማሳዘን አንፈልግም፡፡ ለምድራዊ ተራ ነገር እግዚአብሄን መፍራታችንን አንተውም፡፡ 
 
ለምድራዊ ክብር ለማግኘት ሰዎችን አንጠላም አንበድልም ፡፡ ለከንቱ የምድር ውድድር የተሰጠንን የክርስትና ወንጌል ተልዕኮ ቸል አንልም፡፡ 
 
ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡32 እንደሚሉ ሰዎች ምድራዊ የሚያልፍ ገንዘብ ለማግኘት ሰዎችን አንቀማም፡፡ 
 
ይህ የእግዚአብሄር ቤተሰብነት የልጅነት ክብራችን አይፈቅድልንም፡፡ ክርስቶስን ለማወቅና ለእርሱና ለእርሱ ብቻ ለመኖር ሁሉን እንደ ጉድፍ እንቆጥራለን፡፡ 
 
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ! 
 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

እንደ ሌባ



እየሱስ የሰው ልጆች ሰለ ደህንታቸው ምን እንዳደረጉ ሊጠይቅና በምድር ላይ ሊፈርድ ተመልሶ የሚመጣው እንደሌባ ድንገት ነው፡፡ ሰዎች የእለት ተእለት ኑሯቸውን እየኖሩ እየበሉ እየጠጡ እያገቡና እየተጋቡ ማንም ሳያውቅ ኢየሱስ በድንገት ይመጣል፡፡ 

ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤ የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡1-2
እየሱስ በቶሎ እንደሚመጣ እንጂ በምን ቀንና ሰአት እንደሚመጣ አናውቅም፡፡ ማድረግ የምንችለው የተሻለ ነገር ተዘጋጅቶ መጠበቅ ብቻ ነው፡፡ 

የእግዚአብሄር ሰው ማርቲን ሉተር ክርስቶስ ትናንትና እንደሞተ ፡ ዛሬ ጠዋት እንደተነሳ ፡ ነገ ተመልሶ እንደሚመጣ አድርጋችሁ በዝግጅት ኑሩ በማለት ይመክራሉ፡፡ 

ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም። የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። ማቴዎስ 24፡36-39

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ! 

እየሱስ ይመጣል



የሰው ልጆች ሁሉ በሃጢያት ሃይል ስር ወድቀው ነበር፡፡ ሰዎች ሁሉ በሃጢያት ምክኒያት ለዘላለም ከእግዚአብሄር በተለያዩ ጊዜ የሃጢያታቸውን እዳ ለመክፈል በመስቀል ላይ ለመሞት እየሱስ ወደ ምድር ላይ መጥቶ ነበር፡፡ 

እየሱስ የሞትን ሃይል አሸንፎ ከሞት ተነስቶአል፡፡ በክብርም አርጎ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀምጦዋል፡፡ 

አሁን ዓመተ ምህረት ወይም የምህረት አመት ነው፡፡ ማንም ሰው ሃጢያተኝነቱን ተረድቶ ሀጢያቱ ለዘላለም ከእግዚአብሄር እንደሚለየው አውቆ ንስሃ ለመግባት መልካመ አጋጣሚ ነው፡፡ የሰው ልጆች ንስሃ እንዲገቡና እንዲመለሱ በመታገስ እየሱስ በሰማይ ቆይቶዋል፡፡ 

እየሱስ ዋጋ የከፈለው ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ለሰው ልጆች ሁሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡
ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡4

እየሱስ በቅርብ ተመልሶ ይመጣል፡፡ 

እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። ራእይ 22፡12

የሚገርመው ነገር ግን ተመልሶ የሚመጣው የሃጢያት እዳ ሊከፍል የሰው ልጆችን ሊያድን በድካም አይደለም፡፡ በቅርቡ ተመልሶ ሲመጣ በሃይልና በስልጣን ለእያንዳንዱም እንደ ስራው ሊከፍል በመላዕክት ታጅቦ ነው የሚመጣው፡፡ 

በቶሎ እመጣለሁ የሚለው ቃል እየሱስን ለሚከተል ሰው የሚያስፈነድቅ የምስራች ሲሆን እየሱስን ላልተቀበለ የሚያርበደብድ አስፈሪ መልዕክት ነው፡፡ 

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ! 




Sunday, July 17, 2016

ማኅፀን ገብቶ ይወለድ?

አንዳንድ ሰው የትም እንደማያመልጣቸው ሲናገሩና ሌላውን ሲያስፈራሩ የእናትህ ሆድ ተመልሰህ እንደምትገባ አይሃለሁ! ይላሉ፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስም ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? የሚል ጥያቄ ያቀረበ ኒቆዲሞስ የሚባል ሃይማኖተኛ የአይሁድ አስተማተሪ ነበረ፡፡

ኒቆዲሞስ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው እየሱስ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም ስላለው ነበር፡፡

ምንም የኢትዮጲያን ብናውቅ ኢትዮጲያን ብንወድ ስለ ኢትዮጲያ ታሪክ አስተማሪ ብንሆን ነገር ግን ከኢትዮጲያዊ ካልተወለድን በስተቀር ወደዚህ ወደ ኢትዮጲያ ምድር መግባትና ኢትዮጲያዊ መሆን በፍፁም አንችልም፡፡

እንደዚሁ የእግዚአብሄርን መንግስት ብንፈልግ ስለ እግዚአብሄር መንግስት ታሪክ ብናውቅ ስለመንግስቱ ብናስተምር እንኳን የእግዚአብሄር መንግስት በመካከላችን ብትኖርም እንኳን ዳግመኛ ካልተወለድን በስተቀር ልናያትም ሆነ ልንገባባት እንችልም፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ዮሐንስ 3፡3-5

ሰው ወደ ምድር ለመግባት ከእናቱና ከአባቱ መወለድ ግዴታው እንደሆነ ሁሉ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት ከውሃና ከመንፈስ መወለድ አለበት፡፡ እየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለው የሃጢያት እዳ ለእኔ ነው ብሎ የተቀበለና እየሱስን የህይወቱ አዳኝና ጌታ እድርጎት የሾመ ሰው ሁሉ ዳግመኛ ከእግዚአብሄር ይወለዳል፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ ይሆናል ከእግዚአብሄር ጋር ለዘላለም ይኖራል፡፡

ነገር ግን ሰው ከእናቱ እስከሚወለድ ድረስ ምድርን እንደማያያትና እንደማይገባባት ሁሉ እንዲሁ ሰው ምንም ሃይማኖተኛና መልካም ሰው ቢሆንም ዳግመኛ ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሄርን መንግስትና ቤተሰብ ሊያያትም ሊገባባትም አይችል፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር ያድርጉ



Saturday, July 16, 2016

Are You Gods wife?

 
New York City: It's a cold day in December. A little boy about 10-year-old was standing before a shoe store on Broadway, barefooted, peering through the window, and shivering with cold. A lady approached the boy and said, "My little fellow, why are you looking so earnestly in that window?"
"I was asking God to give me a pair of shoes," was the boy's reply. 

The lady took him by the hand and went into the store, and asked the clerk to get a half dozen pairs of socks for the boy. She then asked if he could give her a basin of water and a towel. He quickly brought them to her. She took the little fellow to the back part of the store and, removing her gloves, knelt down, washed his little feet, and dried them with a towel. 

By this time the clerk had returned with the socks. Placing a pair upon the boy's feet, she then purchased him a pair of shoes, and tying up the remaining pairs of socks, gave them to him. She patted him on the head and said, "No doubt, my little fellow, you feel more comfortable now?"
As she turned to go, the astonished lad caught her by the hand, and looking up in her face, with tears in his eyes, answered the question with these words: "Are you God's wife?" 

 Author : Unknown


Are You Gods wife?

የአይን መከፈት

ጌታ እየሱስን ተቀብለን የዚህ የእግዚአብሄር መንግስትን ጥቅሞች ተጠቃሚ እንዳንሆን የሚያደርገው አንዱ ምክኒያት መንፈሳዊ እውርነት ወይም የአይን አለመከፈት ነው፡፡ አይናቸው የተከፈተላቸው በቀላሉ የሚያዩትን በረከት እኛ ማየት ባለመቻላችን ብቻ ህይወታችን ውስን ከመሆኑም በላይ በክርስትና ህይወታችን መደሰት ያቅተናል፡፡ 
 
 
እውር ሰው አጠገቡ ያለውን መልካም ነገር ማየት እንደማይችል የልቦናችን አይኖቻችን ካልተከፈቱ በስተቀር እግዚአብሄር በክርስቶስ ያዘጋጀልንን በጎነትና ክብር ማየት ይሳነናል፡፡ 
 
 
እግዚአብሄር በክርስቶስ እየሱስ ለህይወትና እግዚአብሄርን ለመምሰል የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ካዘጋጀልን በኋላ ባርከኝ የሚለው ጥያቄያችን አንዳንዴ ተገቢ አይደለም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የእኛ ችግር የበረከት እጥረት ሳይሆን በረከቱን የማየት የእይታ እጥረት ብቻ ነው፡፡ 
 
 
ስለዚህ ነው የመንፈስ አይናችን እየተከፈተ ሲሄድ ባርከኝ የሚለው ጥያቄያችን እየቀነሰ ለበረከት በሁሉ እጅግ ባለጠጎች መደረጋችንን ስላምናውቅ ፀሎታችብን ለበረከት አድርገኝ በሚለው የፀሎት ርእስ የሚሞላው፡፡ ስለዚህ ነው በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ያለውን ተዝቆ የማያልቅ ሃብት ለማየት የልብ አይን መከፈት ወሳኝ ነው የሚባለው፡፡
 
 
ይህንን በክርስቶስ ያለውን አርነት ስናይ ብቻ ነው ክርስትናችንን በሚገባ የምናጣጥመው፡፡ 
 
 
ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡18-19
 
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!