I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Sunday, August 28, 2022
Saturday, August 27, 2022
ሲሾም ያልበላ
እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ አምላክ ነው:: በቅንነት ህዝብን እንዲያስተዳድርና እንዲፈርድ እግዚአብሔር የስልጣንእድልን ይሰጣል::
ሰው እግዚአብሄር የሰጠውን ስልጣን ተጠቅሞ የብዙዎችን ህይወት ሊለውጥ ይችላል::
አንዳንድ ሰው ግን ከሚከፈለው በላይ መኖር ሲመኝ እግዚአብሔር ብዙ ሰዎችን እንዲባርክበት የስጠውንስልጣን አላግባብ በመጠቀም ህዝብን ያስጨንቃል የማይገባውን ገንዘብ ይነጥቃል::
ማማለጃን አትቀበል፤ ማማለጃ የዓይናማዎችን ሰዎች ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። ዘፅአት28:8
ጉቦኝነት የየዋህነት ተቃራኒ ተንኮለኝነት ነው::
በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃ ተሞልታለች። መዝሙር 26:10
ጉቦኝነት በየውሃቴ ሄጃለሁ፤ አድነኝ ማረኝም ብለን እንዳንፀልይ በእግዚአብሔር ፊት ያለንን ድፍረት ይመታል::
ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ። በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውምመማለጃ ተሞልታለች።እኔ ግን በየውሃቴ ሄጃለሁ፤ አድነኝ ማረኝም። መዝሙር 26:9-11
ህይወቱን ለማስተካከል ጉቦ የሚቀበል ሰው ተታሏል:: በህይወት የማይታውከው ደሞዜ ይበቃኛል ብሎ ጉቦየማይቀበል ሰው ነው::
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።መዝሙር 15:5
ጉቦ የሚቀበል ሰው ቀለል ያለ ህይወቱን እላግባብ ያወሳስባል::
ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል፤ መማለጃን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል። ምሳሌ 18:27
ጉቦ ልብን ያቆሽሻል:: ጉቦ በንፁህ ልብ እግዚአብሔርን እንዳናይ ያደርጋል::
ግፍ ጠቢቡን ያሳብደዋል፤ ጉቦም ልቡን ያጠፋዋል። መክብብ 7:7
ሰውን ለመርዳት ጉቦን የሚቀበል ሰው የለም:: ሰው ጉቦ ሲቀበል ጉቦ የሚቀበለውን ሰው ይጎዳል:: ሰው ጉቦሲቀበል የባለመብቱን ፍትህ ያጣምማል::
ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። አሞፅ 5:12
ሰው ጉቦ ሲቀበል ለማይገባው ሰው ይፈቅድለታል ይሚገባውን በመከልከል የባለመብቱን ፍትህ ያጣምማል::
ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃልያጣምማልና ጉቦ አትቀበል። ዘዳግም 16:19
ጉቦ ፍትህን ያሸጣል::
ኀጥእ የፍርድን መንገድ ለማጥመም ከብብት መማለጃን ይወስዳል። ምሳሌ 17:23
ሰው ጉቦ ሲቀበል የማይገባውን ሰው አላግባብ ይጠቅማል:: ሀገር በህግ ሳይሆን በጥቅማ ጥቅም እንድትመራያደርጋል::
ሰው በቅንነት ከመፍረድ ይልቅ ጉቦ ሲቀበል ሰው በሰውነቱ እንዳይከበር ጉልበተኛ በጉልበቱ ተመክቶ የፈለገውንእንዲያደር ያደርጋል::
አለቆችሽ አመጸኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፥ ዋጋም ለማግኘት ይሮጣሉ፤ ለድሀ አደጉአይፈርዱም፥ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም። ኢሳያስ 1:23
ጉቦ ሁሉም ሰው ሰርቶ እንዳያድግ እና እንዳይለወጥ በተቃራኒው ሌቦችና አጭበርባሪዎች በነፃነት እንዲዘርፉያደርጋል:: ህዝብ ሁሉ እንዲደኸይ ጥቂቶች ብቻ ሃብቱን አላግባብ እንዲያካብቱ ያደርጋል::
ልጆቹም በመንገዱ አልሄዱም፥ ነገር ግን ረብ ለማግኘት ፈቀቅ አሉ፥ ጉቦም እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።1ኛ ሳሙኤል 8:3
የንጹሑን ሰው ነፍስ ለመግደል ጉቦ የሚቀበል ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። ዘዳግም 27:25
እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ክእንግዲህ ወዲህም አንገተደንዳና አትሁኑ። ዘዳግም 10:17
በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው! ኢሳያስ 5:23
ጉቦ የሚቀበል ሰው አገሬን እወዳለው የሚለው ውሸቱን ነው:: ጉቦ ቤተሰብን ብሎም እገርን ያፈርሳል::
ንጉሥ በፍርድ አገሩን ያጸናል፤ መማለጃ የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል። ምሳሌ 29:4
ጉቦ የሚቀበል ሰው እግዚአብሔር ቤቴን እግዚአብሔር ይጠብቀዋል የሚለውን ድፍረቱን ያጣል::
የዝንጉዎች ጉባኤ ሁሉ ለጥፋት ይሆናል፥
የጉቦ ተቀባዮችንም ድንኳን እሳት ትበላለች። ኢዮብ 15:34
እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፤ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ። ሚክያስ 7:3
የገንዘብ ፍቅር ያለበት ጉቦ የሚቀበል ኢየሱስ መሞቱን እንኳን ይክዳል::
ከሽማግሎች ጋርም ተሰብስበው ተማከሩና ለጭፍሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋቸው። እኛ ተኝተን ሳለን ደቀመዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ። ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለንእናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን አሉአቸው። እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸውአደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል። ማቴዎስ 28:12-15
ጉቦ የሚቀበል እግዚአብሔር በነፃ የሰጠውን ቸርችሮ የሚበላበት ሰው እግዚአብሔርን አያምንም::
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፤ ከዚህምጋር። እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔርይታመናሉ። ሚክያስ 3:11
ጉቦ የሚቀበል እግዚአብሔር በህዝብ እንዲያገለግል የሰጠውን ስልጣን አላግባብ የሚጠቀም ሰውእግዚአብሔርን የረሳ ነው::
በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ጉቦን ተቀበሉ፤ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ከባልንጀሮችሽም በቅሚያየስስትን ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ህዝቅኤል 22:12
እግዚአብሔርን የሚያስደስት ሰው::
በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁንየሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቍር፥ ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው።ኢሳያስ 33:15
ያን ጊዜም ደግሞ እንዲፈታው ጳውሎስ ገንዘብ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ አደረገ፤ ስለዚህ ደግሞ ብዙ ጊዜ እያስመጣያነጋግረው ነበር። ሐዋርያት 24:26
ጉቦ የሰጠህ ሰው አንተ ትልቅ ቦታ ላይ ሆነህ በገንዘብ ስለገዛህ በልቡ ይንቅሀል ሳይወድ ስለዘረፍከው ደግሞበልቡ ይረግምሀል:: ሰው ሲረግምህ መንገድህ አይቀናም::
በጉቦ የተቀበልከው ጥቅም ላብህ ስላይደለ ያንተ አይደለምና በወጉ አትጠቀምበት:: በንፅህና ስላላገኘህው ኮሽባለ ቁጥር ትደነግጣለህ ኑሮህ የቆቅ ኑሮ ይሆናል::
ጉቦ አእምሮን ስለሚያበላሽ ከምትጠቀምበት በላይ ስለምትሰበስብ በጉቦ ያገኘኸውን ገንዘብ ለመደበቅ ስትጥርበመሃል ሌላው ይበላዋል::
በእጆችህ በመድከም ቀስ በቅስ የተከማቸ ሃብት ስላይደ ለአያያዙን ስለማታውቅበት እንደጠላት ገንዘብትበትነዋለህ::
ከደሃ አስጨንቀህ መቀበልህን እንጂ ራስህ እንደምትጠቀምበት እርግጠኛ መሆን አትችልም:: ከድሀ ኪስአውጥተህ ለማንም እንዳይሆን በክንቱ ትበትነዋለህ::
ለራሱ ጥቅም ለመጨመር ሲል ድሀን የሚጐዳ፥ ለባለጠጋም የሚሰጥ፥ እርሱ ወደ ድህነት ይወድቃል። ምሳሌ22:16
ሲሾም ያልበላ በሰላም ይኖራል::
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ