Popular Posts

Tuesday, October 20, 2020

ለክብራችን የማይመጥን ውርደት ነው

 


እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 631-33

አሕዛብ እግዚአብሄርን የማያውቁ ተፈጥሮአዊ ሰዎች ናቸው፡፡ አሕዛብ መኖርና መኖር ብቻ እንጂ ከመኖር ውጭ ሌላ እግዚአብሄርን በህይወታቸው የማክበር ምንም አላማ የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ አሕዛብ እንደሰው ኖረው እንደሰው የሚሞቱ እግዚአብሄርን የማያውቁ ሰዎች ናቸው፡፡ አሕዛብ የምድር ላይ ብቸኛ አላማቸው የሚበላ እና የሚለበስ አሟልተው መኖርና መሞት ብቻ ነው፡፡

አሕዛብ ስለሚበላና ስለሚለበስ ቢጨነቁ በምድር ላይ ከመብላትና ከመልበስ በላይ ምንም የሚታያቸው ሰማያዊ ራእይ የሌላቸው ጭፍን ሰዎች ስለዐሆኑ ነው፡፡ አሕዛብ በተፈጥሮ አይን የማየታየውን የእግዚአብሄርን መንግስት የማይረዱ አይናቸው ለመንፈሳዊው አለምና ለመንፈሳዊው ጌታ ለኢየሱስ አይናቸው የታወረ በደመነፍስ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ስለሆኑ ስለሚባላና ስለሚጠጣ ከመጨነቅ ውጭ ምንም አይታያቸውም፡፡ 

ኢየሱስ እንደ አዳኛችንና ጌታችን የተቀበል ሁላችን አህዛብ የሚፈልጉትን ነገር ለመፈለግ ደረጃችን አይመጥነውም፡፡ እኛ ለሚበላ እና ለሚለበስ ከመስራት እና ከመኖር የተሻለ የህይወት አላማ አለን፡፡ የእግዚአብሄርን መንግስት ፅድቁንም የመፈለግ የከበረ የህይወት አላማ አለብን፡፡

ለእኛ ለሚበላና ለሚለበስ መኖርና መስራት አይመጥነንም፡፡ የእግዚአብሄር ልጅነት ክብራችን ለሚበላና ለሚለበስ ለመኖር አይፈቅድልንም፡፡ ለሚበላና ለሚለበስ መጨነቅ ለክብራችን የማይመጥን ውርደት ነው፡፡ እንደ አሕዛብ ለሚበላና ለሚለበስ መጨነቅ ከእግዚአብሄር ልጅነት ክብራችን ጋር አብሮ አይሄድም፡፡ ለእኛ ለሚበላና ለሚጠጣ መጨነቅ ከልጅነት ክብር መውደቅ ውርደት ነው፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 631-33

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #መሰረታዊፍላጎት #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ሰለሞን #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ድንግል #ማርያም #ኦርቶዶክስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment