Popular Posts

Saturday, October 17, 2020

ንፍታሌም በሞገስ ጠግቦአል

 


ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም በሞገስ ጠግቦአል፥ የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል። ኦሪት ዘዳግም 33፡23

እነሆ፥ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፥ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣሉ። ትንቢተ ኢሳይያስ 55፡5

እግዚአብሄር በህይወታችን አላማውን ለመፈፀም ሞገስን ይሰጣል፡፡ ሞገስ ማለት ደግሞ ተቀባይነት ማግኘት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር  ሞገስ ሲሰጣችሁ ሰዎች ካለምክኒያት ፊታችሁን ይቀበሏችኋል፡፡ እግዚአብሄር ሞገስን ሲሰጣችሁ ሰዎች ጥያቄያችሁን ይመልሳሉ፡፡ እግዚአብሄር ሞገስ ሲሰጣችሁ ሰዎች ፍላጎታችሁን ለሟሟላት ይተጋሉ፡፡ እግዚአብሄር ሞገስ ሲሰጣችሁ ሰዎች የልባችሁን መሻት ለመፈፀም ይረባረባሉ፡፡

እግዚአብሄር ሞገስ ሲሰጣችሁ ሰዎች ድካማችሁን የራሳቸው ድካም እድርገው ለመሸፈን ይተጋሉ፡፡ እግዚአብሄር ሞገስ ሲሰጣችሁ ስታዝኑ ሰዎች አብረዋችሁ ያለቅሳሉ፡፡ እግዚአብሄር ሞገስ ሲሰጣችሁ ስትታመሙ ሰዎች አብረዋችሁ ይታመማሉ፡፡ እግዚአብሄር ሞገስ ሲሰጣችሁ ራሳችሁን ለመምረጥ በምትፈተኑበት ጊዜ ሰዎች እናንተን ይመርጧችኋል፡፡ እግዚአብሄር ሞገስ ሲሰጣችሁ ሰዎች ከእናንተ ጋር ራሳቸውን ማስተባበር ይፈልጋሉ፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

 ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህብረት #አጋርነት #አብሮማደግ #የጋራ #ሞገስ #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment