Popular Posts

Friday, October 9, 2020

ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም

 

ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም

ከማርያምና ከእኅትዋ ከማርታ መንደር ከቢታንያ የሆነ አልዓዛር የሚባል አንድ ሰው ታሞ ነበር። ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር። ስለዚህ እኅቶቹ ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል ብለው ወደ እርሱ ላኩ። ኢየሱስም ሰምቶ፦ ይህ ህመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ። የዮሐንስ ወንጌል 11፡1-4

እግዚአብሄር እርሱን ከማንፈልግባቸው ነገሮች ይልቅ እርሱን የምንፈልግባቸው ነገሮች ያስደስቱታል፡፡ 

በእግዚአብሄር ላይ ከማደገፍባቸው ሁኔታዎች ይልቅ በእግዚአብሄር ላይ የምንደገፍባቸው ሁኔታዎች እርሱን ያስደስቱታል

ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ብለን ለእርዳታ ከማንጮህባቸው ሁኔታዎች ይልቅ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ብለን የምንጮህባቸው ሁኔታዎች እግዚአብሄርን ደስ ያሰኙታል፡፡  

የእግዚአብሄርን እርዳታ ከምንረሳባቸው ሁኔታዎች ይልቅ የእግዚአብሄርን እርዳታ በእጅጉ የምንፈልግባቸው ሁኔታዎች እግዚአብሄርን ደስ ያስኙታል፡፡ 

ትኩረታችን ራሳችን ላይ ከሚሆንበት ጊዜ ይልቅ ትኩረታችን እግዚአብሄር ላይ የሚሆንበት ጊዜ እግዚአብሄርን ያረካዋል፡፡ 

ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ቢመስለንም በመሰለን በእግዚአብሄር ዘንድ ግን ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ነገር የለም፡፡ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ በመሰለን ጊዜ በርሱ ላይ መደገፋችንን እግዚአብሄር ይወደዋል፡፡ 

እግዚአብሄርን እንድንፈልግ ስለተፈጠረን እግዚአብሄርን በብርቱ የምንፈልግባቸው ሁኔታዎች ሲገጥመን እግዚአብሄርን ደስ ያሰኘዋል፡፡ 

ከአቅማችን በላይ የሆነ ነገር ሲገጥመን እግዚአብሄርን ለመፈለግ ትሁት ስለሚያደርገን እግዚአብሄር ይደስታል፡፡ 

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ 

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ ትህትና #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment