ህይወት
ትልቅ ሃላፊነት ነው፡፡ የተፈጠርንበትን አላማ ለመኖር ትልቅ ትጋት ይጠይቃል፡፡
ህይወት ጥንቃቄን የሚጠይቅ የቤት ስራ ነው፡፡ ህይወት ትልቅ ሃላፊነትን የሚጠይቅ ሸክም ነው፡፡
ህይወት
ደግሞ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ ህይወት ሸክም ብቻ ሳይሆን ልንደሰትበት የሚገባ የእግዚአብሄር በረከት ነው፡፡ በህይወት በመኖራችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ በመስራታችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ እግዚአብሄርን በመፍራታችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ ለእግዚአብሄር መንግስት ዋጋ በመክፈላችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ እግዚአብሄር እምላካችን ስለሆን ልንደሰት ይገባል፡፡ ለእግዚአብሄር ነገር ታማኝ
በመሆናችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ ለእግዚአብሄር ስራ በመትጋታችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ ካለፍርሃት በደስታ እንድናገለግለው ሰጥቶናል፡፡
በእርሱም
ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን። የሉቃስ ወንጌል 1፡74-75
ሰይጣን
እንደሆነ የሚለው ምንም ነገራችን በቂ አይደለም ነው፡፡ ለሰይጣን ምንም ነገራችን አያምረውም፡፡ የሰይጣን አላማ እኛን ማሰናከል ስለሆነ ለሰይጣን ምንም ነገራችን አበቃውም፡፡ ለሰይጣን ምንም ነገራችን አይጥመውም፡፡ የሰይጣንን ነገር እየሰማን በላያችን ላይ ልንከፋ አይገባም፡፡
እግዚአብሄር
ደግሞ ከእኛ ብዙ ነገር አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው በመጨረሻ እንድምንጠየቅ አድርገን ብቻ እንድንወጣና ህይወታችንን በደስታ እንድንኖር ብቻ ነው፡፡
የነገሩን
ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መጽሐፈ መክብብ 12፡13-14
እግዚአብሄር
እንድንደክም ብቻ ሳይሆን በድካማችን ደስ እንዲለን ይፈልጋል፡፡ ህይወት ሸክም ብቻ ሳይሆን ስጦታ መሆኑን አውቀን እንድንደሰትበት የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡
ህይወትን
እንደሸክም ብቻ በሚያየው ሰው እና እንደስጦታ በማይደሰትበት ሰው እግዚአብሄር አይደሰትበትም፡፡ ህይወትን እንደሸክም ብቻ የሚያየው ሰው እና እንደስጦታ የማይደሰትበት ሰው በህይወቱ ስኬታማ አይሆንም፡፡ ህይወትን እንደሸክም ብቻ የሚያየው ሰው እና እንደስጦታ የማይደሰትበት ሰው በሚዛናዊነት ስላልያዘው ብዙም አይዘልቅም፡፡
ተቈጣም
ሊገባም አልወደደም፤ አባቱም ወጥቶ ለመነው። እርሱ ግን መልሶ አባቱን፦ እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት እንደ ባሪያ ተገዝቼልሃለሁ ከትእዛዝህም ከቶ አልተላለፍሁም፤ ለእኔም ከወዳጆቼ ጋር ደስ እንዲለኝ አንድ ጥቦት ስንኳ አልሰጠኸኝም፤ የሉቃስ ወንጌል 15፡28-29
የአባቱ
መልስ ግን ለእኔ ለአባትህ መኖር በአባትህ እንዳትደሰት ሊያደርግህ አይገባም ነበር የሚል መልዕክት ያለው ነበር፡፡
እርሱ
ግን፦ ልጄ ሆይ፥ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፥ ለእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፤ የሉቃስ ወንጌል 15፡31
እግዚአብሄር
ሲባርክ የሚባርከው በትጋትና በደስታ ነው፡፡ ደስታ የሌለው ትጋት አሰቃቂ ነው፡፡ የህይወትን ሸክም የሚያቀለው የልባችን ደስታ ነው፡፡
እነሆ፥
እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ እድል ፈንታው ነውና። እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። እግዚአብሔር በልቡ ደስታን ስለ ሰጠው እርሱ የሕይወቱን ዘመን እጅግ አያስብም። መጽሐፈ መክብብ 5፡18-20
ዛሬ
አሁን ባለንበት በዚሁ በደረስንበት ደረጃ በእግዚአብሄር ስጦታ በህይወት መደሰት ካልቻልን የሆነ ያልገባን ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ህይወት ሸክም ብቻ ሳይሆን እያንዳንዷን ደረጃና ዝርዝር ልንደሰትበት የሚገባ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡
ከሚበላውና
ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል። መጽሐፈ መክብብ 8፡15
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ብልፅግና #መደሰት #ስኬት #ህይወት #ስጦታ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #ሃዋርያውአቢይ #አቢይዋቁማ #ሃዋርያውአቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #ማስተዳደር #እረፍት
No comments:
Post a Comment