Popular Posts

Sunday, July 5, 2020

የእርሱን አሳብ አንስተውም




በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 211
እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራው በፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚገኘው በፍቅር መካከል ነው፡፡
ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1 የዮሐንስ መልእክት 48
በተቃራኒው ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ይመጣል፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋት ውጭ ሌላ አሳብ የለውም፡፡ ይህንን አላማውን የሚያስፈፅመው በጥላቻ ነው፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 1010
ይቅር አለማለት ምሬትና ጥላቻ የሰይጣን ለም መሬት ነው፡፡ ሰይጣን በጥላቻ ልብ ውስጥ ምንም ክፉ ነገር ቢዘራ ይበቅልለታል፡፡ በሰው ውስጥ ጥላቻን ማድረግ ከቻለ ሰውን ይሰርቃል ያርዳል ያጠፋል፡፡
ሰይጣን ሰውን ሲሰረቅ ሲያርድና ሲያጠፋ አላማው ይህንን አላማ በስፋት ማከናወን ነው፡፡ የተሰረቀው ሰው ለሌላውን ሰው ይጠላል፡፡
ሰይጣን ሲገድል የአንዱን ግድያ አሳቦ አንዱ ሌላውን እንዲጠላውና ፈረሱ እንዲሆንለት ያደርጋል፡፡ የሰይጣንን ጥላቻ የሚያስተናግድ ሰው ሰይጣን ወደፈለገው ቦታ የሚጋልበው የሰይጣን ፈረስ ነው፡፡
እናንተ ግን ይቅር የምትሉትን እኔ ደግሞ ይቅር እለዋለሁ፤ እኔም ይቅር ካልሁ፥ ይቅር ያልሁትን ስለ እናንተ በክርስቶስ ፊት ይቅር ብዬአለሁ፥ በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 210-11
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ዲያቢሎስ #ጠላት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ማታለል #የተሸነፈ #በረከት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment