Popular Posts

Thursday, July 9, 2020

የመሰረታዊ ፍላጎት እምነት



ብዙ ሰው ስለብዙ ነገር እምነት እንዳለው ይናገራል፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ ስለብዙ ነገሮች እምነት እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ እንዲሁ ሌላው ደግሞ ስለ ትልልቅ ነገሮች እምነት እንዲኖረው ይመኛል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስን አምኖ ከመቀበል ውጭ በጣም አስፈላጊው እምነት ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ማመን ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ስለብዙ ነገር እምነት የሚያስፈልጋቸው ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ከደህንነት ቀጥሎ በጣም የሚያስፈልጋቸው እምነት የመሰረታዊ ፍላጎት እምነት ነው፡፡
እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 632-33
ብዙ ሰዎች ስለብዙ ነገር እምነት እንዲኖራቸው ቢፈልጉም በቅርበት ፍላጎታቸው ቢጣራ በመሰረታዊ ፍላጎት መቸገር አለመፈለግ ነው፡፡ ስለትልልቅ ነገሮች እምነት እንዲኖራቸው የሚፈልጉት ሰዎች ፍላጎታቸው በቅርብ ቢታይ ስለትልልቅ ነገር ማን የሚፈልጉት በተዘዋዋሪ ለመሰረታዊ ፍላጎት እንዲረዳቸው መቸገርን ስለሚፈሩ ነው፡፡ ሰው አሁን ከሚጠቀምበት በላይ ብዙ ውድ ሃብት ማከማቸት የሚፈልገው ነገ እንዳይቸገር ከመፍራት ሊሆን ይችላል፡፡
ሰው ምንም አይነት እምነት አለኝ ቢል ነገር ግን ስለ ነገ ኑሮው ስለ መሰረታዊ ፍላጎቱ እግዚአብሄርን ካላመነ እምነት የለውም፡፡ ሰው ስለመሰረታዊ ፍላጎት ካመነ ደግሞ እምነቱ መሰረት አለው፡፡
ከደህንነት ቀጥሎ ስለምንንም ነገር እምነት ከማጣት በላይ ሰውን የሚጎዳው የሚያስጨንቀውና የሚያስፈራው ስለመሰረታዊ ፍለጋት እምነት ማጣት ነው፡፡
በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፥ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል። የማቴዎስ ወንጌል 13፡22
ስለመሰረታዊ ፍላጎት እምነት የሌለው ሰው በነፃነት ለእግዚአብሄር ሊኖር እግዚብሄርን ሊያገልግል አይችልም፡፡ ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ያመን ሰው እግዚአብሄር በወደደው መልኩ ሊጠቀምበት የሚችል ከፍርሃትና ከጭንቀት ነፃ የወጣ ሰው ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #መሰረታዊፍላጎት #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ሰለሞን #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ድንግል #ማርያም #ኦርቶዶክስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment