I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Monday, June 29, 2020
እግዚአብሔር ትልቅ ዘማሪት ህሊና ካሳሁን
፡ ትልቅ (Egziabhier
Teleq) - ህሊና ፡ ካሳሁን
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሙላትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሰላምህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከጉልበትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከዙፋንህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
፡ ይቀልጣሉ ፡ መገኘትህን ፡ ሲረዱ
፡ ዙፋን ፡ ስጡኝ ፡ ያሉ
፡ ሄዱ ፡ እያፈሩ (፪x)
፡ ትልቅ (፬x)
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ (፬x)
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ አለቃ ፡ ብቻህን ፡ ምትገዛ
፡ ፍጥረትን ፡ በቃልህ ፡ ያጸናህ (፪x)
፡ ማይወጣልህ ፡ ኃይልህ ፡ አይለካ
፡ መጠለያ ፡ ክንድህ ፡ የበረታ (፪x)
፡ በእኔ ፡ ጓዳ (፪x)
፡ ለምን ፡ ልፍራ
፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ ፡ (፬)
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
Sunday, June 28, 2020
ብዙ ጊዜ እንደምናስበው እጅግ በጣም አስፈላጊ አይደለንም በአእምሮዋችን ከምናስበው በላይ ግን ተወደናል
Saturday, June 27, 2020
Don't Quit by John Greenleaf
Friday, June 26, 2020
ለምን ? ለምን ?
Thursday, June 25, 2020
Wednesday, June 24, 2020
ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ . . . እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። . . . ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር። የማርቆስ ወንጌል 16:17-20
Tuesday, June 23, 2020
በምድራዊ እውቀት የማይደረስበት መንፈሳዊ ክልል
ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው። የሉቃስ ወንጌል 13፡16
በህይወታችን ላይ የሚነጣጠሩ ብዙ ጥቃቶች ከምናስበው
በላይ መንፈሳዊ ናቸው፡፡
ለምሳሌ የጤና መታወክ ሲደርስብን ቶሎ የሚመጣልን የሳይንሱ እውቀትና የሳይንሱ መፍትሄ ነው፡፡ ብዙ ነገር ሲደርስብን ቁሳዊ እናደርገዋለን፡፡ ብዙ ነገር ሲደርስብን በህክምና እውቀት ብቻ ልንተረጉመው እንፈተናለን፡፡
የበላሁት ምግብ ነው ወይም ቫይረስ ነው ብለን
እንደሰው ልማድ ብቻ ጥቃቱን ልንዋጋው እንፈልጋለን፡፡ እንደሰው ልማድ ተዋግተን ከተሳካልን እሰየው፡፡ የሰይጣን ስራ ለማፍረስ ያለንን
ነገር ሁሉ እምነታችን እና እውቀታችንን ሁሉ እንጠቀማለን፡፡
እንደሰው ልማድ ብቻ ከመዋጋት ያለፈ ነገር የሚጠይቅ
ብዙ የዲያቢሎስ ጥቃት አለ፡፡
የሰው ልጆች ጥቃት በቀጥታ ባይሆንም ቢያንስ በተዘዋዋሪ
ከሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን ሌላ ራእይ የለውም፡፡ ራእዩ መስረቅ ማረድና ማጥፋት ብቻ ነው፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
አንዳንዴ ሰይጣን በመንፈሱ በቀጥታ ባያጠቃንም ማድረግ ያለብንን ነገር በቸልተኝነት እንዳናደርግ በአእምሮዋችንም ቢሆን ያጠቃናል፡፡ ወይም የእግዚአብሄርን አላማ በምድር ላይ እንዳንፈፅም በፍርሃት ሽባ ያደርገናል፡፡ ሌላም ጊዜ በፀጋ ከተቀበልነው በሽታን በእኛ ላይ ሊያደርግ ይሞክራል፡፡
ተዘዋዋሪ የሰይጣን አላማ ቢሆኑም ንፅህናን ባለመጠበቅ
የሚመጡ በሽታዎች ከሰይጣን አላማ ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ጥንቃቄያችንንም ተጠቅሞ ከጠላት ጥቃት ያስመልጠናል፡፡
ተጠንቅቀንም እግዚአብሄር አስመለጠን ነው የምንለው
እንጂ ጥንቃቄያችንም ፍፁም በማይሆነው በጥንቃቄያችንም አንታመንም፡፡
እግዚአብሄር ለእኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለደህንታችን
ያለውንም ነገር ሁሉ ይጠቀማል፡፡ እግዚአብሄር የዶክተሮችን ጥበብ ተጠቅሞ በሽታን ይዋጋልናል፡፡ የዲያቢሎስን ስራ ለማፍረስ ያለንን
ምድራዊ እውቀት እና መንፈሳዊ እውቀርት ሁሉ እንጠቀማለን፡፡ ሰይጣን በህይወታቸን በጤናችን ምንም ስፍራ እንዳያገኝ እስከመጨረሻው
ፀንተን እንቃወመዋለን፡፡
በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡9
ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡8
ከዶክተሮች እውቀት በላይ ያለ ነገር ደግሞ አለ፡፡ ዶክተሮች በምድራዊ ጥበባቸው የማይደርሱበት መንፈሳዊ ክልል አለ፡፡
ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡14
እግዚአብሄር እምነታችንን ተጠቅሞ ከበሽታው ጀርባ
ያለውን መንፈሱን በኢየሱስ ስም እንድንቃወመው አይናችንን ይከፍታል ይመራናል፡፡
ይህችን ሴት በወቅቱ ዶክተሮች ጋር ብትታይ ዶክተሮች
በምድራዊ እውቀታቸው የማይረዱት መንፈሳዊ ክልል ስላለ ስለበሽታዋ አንድ ምክኒያት ይሰጧታል፡፡
ኢየሱስ ግን ከዚህ በሽታ ጀርባ ያለውን ሊሰርቅ
ሊያርድና ሊያጠፋ የሚመጣውን ሰይጣንን አየው፡፡ ኢየሱስ በሽታውን ሳይሆን ከበሽታው በስተጀርባ ያለውን የበሽታውን ምንጭ አደረቀው፡፡
ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው። የሉቃስ ወንጌል 13፡16
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት
#ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#እምነት #ተስፋ
#አሁን #ጌታ
#ሰላም #ደስታ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
Monday, June 22, 2020
Lauren Daigle - You Say (Official Music Video)
Sunday, June 21, 2020
ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ። ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል። መጽሐፈ መክብብ 3፡12-13 ፣ 8፡5
Saturday, June 20, 2020
Friday, June 19, 2020
የእግዚአብሄር ሰው አዴቦዬ ስለ እግዚአብሄር ሰው ኬኔት ሃገን አገልግሎት ከመሰከሩት
Wednesday, June 17, 2020
Tuesday, June 16, 2020
እውነተኛ የህይወት ለውጥ የሚጀምረው
Monday, June 15, 2020
እግዚአብሔር የሚቀጣው እንዲበድል ያደረገውን ስጋዊ ፍላጎት ነው
ብዙ ሰዎች በደልን እንዴት እንደሚይዙ ስላማያውቁ
በህይወታቸው ዘመን ይሰቃያሉ፡፡ ገንዘባችንን እንዴት እንድምንይዝ ፣ ጤናችንን እንዴት እንድምንጠበቅ ፣ ስራችንን እንዴት እንደምንሰራ
የመሳሰሉትን ከምናውቀው እውቀት በላይ ከሰው ጋር እንዴት እንድምንኖር ማወቅ ከብዙ ኪሳራ ከብዙ የስሜት በሽታ ብሎም ከብዙ ችግሮች
ይጠብቀናል፡፡
ሰውን እንድናምን ከሰው ጋር እንድንኖር ተፈጥረናል፡፡
ሰው ጠቃሚ እንደመሆኑም መጠን ግን በተለያየ ጊዜም ይበድለናል፡፡
ሰው አውቆም ይሁን ሳያውቅ ሰውን ስለሚበድል ሰው
ሰውን የመበደሉ እውነት የማይቀር ነገር ነው፡፡ ዋናው ነገር ሰው ሰው ሰውን ይበድላለ ወይ የሚለው ጥያቄ አይደለም፡፡
ዋናው ነገር የተበደለው ሰው በደሉን እንዴት ይይዘዋል የሚለው ጥያቁ ነው፡፡ ሰው ለበደል እንዴት እንደሚመልስ ካወቀ ያርፋል፡፡
ሰው በደሉን በትክክል ከያዘው ይማርበታል ያድግበታል የተሻለ ሰው ሆኖ ይለወጥበታል፡፡
ሰው በደሉን በትክክል ካልያዘው ይሰቃይበታል ህይወቱን ያባክንበታል፡፡
ሰው ሲበድለን በመጀመሪያ ደረጃ ነፃ የሚያወጣን ነገር ስለበደሉ የተቻለንን ያህል
ሃላፊነት መውሰዳችን ነው፡፡ እርሱ 100 % ጥፋተኛ ነው እኔ 0% ጥፋተኛ ነኝ የሚለው ነገር አያዋጣም፡፡ ቢያንስ ሲያጠፋ እኛ
ጥፋቱን የመለስንበት መንገገድ ትክክል ላይሆን ይችላል፡፡
ሁለተኛ እግዚአብሄር የሚቀጣው የበደለውን ሰውዬ ሳይሆን እንዲበድል ያደረገውን ስጋዊ
ፍላጎት ነው፡፡
ሶስተኛ ማወቅ ያለብን እርሱን እንዲበድል ያደረገው ያው ስጋዊ ፍላጎት እኛም ውስጥ
እንደሚኖር አውቀን ትምህርትና ግሳፄ መውሰድ ነው፡፡ እኔ እንደዚህ መበደል አልችልም ማለት ሞኝነት ነው፡፡ በበዳዩ ውስጥ ያየነውን
የስጋ አስከፊነት ካየን እኛ ውስጥ ያለው ስጋ በሌሎች ላይ ተመሳሳይ በደል እንዳያደርግ እንጨክንበታለን፡፡
አራተኛ የበደለን ሰው እስኪወድቅ አለመጠበቅ ነው፡፡ ሰው ስራውን ትቶ የበደለኝ
ሰው ከመቼ መቼ ይቀጣል እያለ ስለበደለው ሰው የሚከታተል ከሆነ የራሱን የህይወት አላማ ትቶ ስቶዋል ማለት ነው፡፡ ከበደለው ሰው
ጋር በመፎካከር የህይወት አላማውን አሽቀንጥሮ የሚጥል ሰው የህይወት አላማው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የማያውቅ ሰው ነው፡፡
የበደለ ሰው ስጋ በአስቸጋሪ ነገር ውስጥ በማለፍ የስጋ ፍላጎቱ ሊገደል ይችላል፡፡
በደል ያስደረገው ያ ስጋዊ ፍላጎት ዛሬ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በምን መጠን በምን ሁኔታ ይቀጣ አታውቅምና ትተኸው ህይወትህን ኑር፡፡
ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥
እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡19
አንተን ስለበደለህ እንዲጠፋ ከመፈለግ ይልቅ ሰው እንዲለወጥ እንዲሻሻል እንዲመለስ
ፀልይለት፡፡ አንተን ስለበደለ እንዲቀጣ ብቻ ሳይሆን በዚህ አጋጣሚ እንዲመለስ እንዲስተካከል ፈልግ፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ
እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡1
አንተ የበደለህ ሰው እርዳታህን በሚፈልግበት ጊዜ መርዳትህ እንዳልበደለህ አይናገርምና
እርዳው፡፡ የበደለ ሰው ይታዘንለታል እንጂ አይቀናበትም፡፡
ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት
ፍም ትከምራለህና። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡20
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #የሚፈርድ #የሚያማ #ወንጌል #መውደድ #ፍቅር #ምህረት #መታዘዝ #ማገልገል #መውደድ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ