Popular Posts

Wednesday, August 24, 2022

የድህነት ድንጋጤን ማሸነፍ

 


እያንዳንዳችን በተለያየ ጊዜ በማጣት እና በድህነት ተፈትነን እናውቃለን፡፡ እጦቱ ቢያልፍም በጊዜው ያለፍንበት እጦት በውስጣችን ድንጋጤን ሊተው ይችላል፡፡ የእጦት ድንጋጤ በውስጣችን ቀርቶ አንዳንዴ "ወደዚያ ድህነት ውስጥ ልትመለስ ነው" ብሎ ያስፈራራናል፡፡

እጦት ውስጥ ልገባ ነው እንዴ? የሚል ፍርሃት መሰማት ተፈጥሮአዊ ስሜት ነው፡፡ በፍፁም የፍርሃት ስሜት እንዳይሰማን ማድረግ አንችልም፡፡

የፍርሃት ስሜት በራሱ ጥሩ ወይም መጥፎ አይደለም፡፡ ማንኛውም ስሜት በህይወታችን የራሱ አላማ እና ስፍራ አለው፡፡

ጠቢብ ሰው ይፈራል ከክፉም ይሸሻል፤ ሰነፍ ግን ራሱን ታምኖ ይኰራል። መጽሐፈ ምሳሌ 1416

ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፤ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይጐዳሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 22:3

የህይወት ድንጋጤ ትዝታው ከጊዜ ወደጊዜ ሊመጣ ይችላል፡፡ የህይወትን ድንጋጤ ሊያነሳሱ የሚችሉ ነገሮች በህይወታችን ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ የድንጋጤውን ስሜት ሊያስቆም የሚችለው ምንም ነገር የለም፡፡ ማድረግ የምንችለው አንድ ነገር ድንጋጤው አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሮብንና በድንጋጤው ተነሳስተን እርምጃ አለመውሰድ ነው፡፡

ያለፍንበት የማጣት ድንጋጤ እና ህመም ለረጅም ጊዜ በውስጣችን ሊቆይ ይችላል፡፡ በዚያ በማጣት ህመም ተነሳስተን የማይገባንን ነገር አለማድረግ ይኖርብናል፡፡

አንዳንድ ሰው የማጣትን ህመማ ከሚገባው በላይ ከመፍራቱ እና ከማክበሩ የተነሳ እጦት እንዳይገጥመው በድህነት ፍርሃት ተነሳስቶ የማይገባውን ነገር ሁሉ ያደርጋል፡፡ እንዳያጣ በመፍራት ይዋሻል ይሰርቃል ይቀማል ይጠላል ይበድላል እንዲሁም ይገድላል፡፡

ልዩነት የሚያመጣው ፍርሃቱ መሰማቱ ሳይሆን የፍርሃቱን ስሜቱን የምንይዝበት መንገድ ነው፡፡ የፍርሃትን ስሜት የምንይዝበት መንገድ ፍርሃቱነ አሸንፈን እንድንወጣ ወይም ደግሞ በፍርሃቱ ተሸንፈን እንድንቀር ሊያደርገን ይችላል፡፡

በፍርሃት መንፈስ አስጠንቃቂነት ተረድተን ወደ ድህነት እንዳንገባ የሚገባንን እርምጃ መውሰድ የራሱ የሆነ ጥቅም አለው፡፡ በህይወታችን ለስንፍና ስፍራን ባለመስጠት መትጋት ይጠበቅብናል፡፡ነገር ግን የኑሮ ፍርሃት እኛን የኑሮ ፍርሃት በማስፈራራት የማይገባንን ነገር እንድናደርግ አያድርገን፡፡ በህይወታችን ኪሳራ የሚገጥመን የፍርሃት ስሜቱ ስለተሰማን ሳይሆን ፍርሃት ከህይወት አላማችን ካስቆምን ብቻ ነው፡፡

የድህነት ፍርሃት የህመም እና የድንጋጤው ስሜት ሳይጠፋ የፍርሃቱ ስሜት እያለ የህይወት አላማችንን ካደረግነው ስኬታማ እንሆናለን፡፡

የፍርሃት ስሜት የሚሳካለት ከህይወት ፊት ካልሰጠነው እና አላማችን ካስቆመን ብቻ ነው፡፡

መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡12-13

በህይወታችን ያለፈው የድህነት ወይም የማጣት ታሪክ የወደፊት ህይወታችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዲያደርግ እና ከህይወት አላማችን እንዲያስተጓጉለን አንፍቀድለት፡፡ 

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 

Sunday, August 21, 2022

ከአእምሮ በላዩ የእግዚአብሔር ቸርነት

 

እግዚአብሔር መልካም ነው። መልካምነቱ እጅግ በጣም ጥሩ ከመሆኑ የተነሳ ቸርነቱ ከማንም ቸርነት ጋር ሊወዳደር አይችልም።

እኛ በብዙ ነገር ውስን ነን። አንድን ቃል ስንሰማ የቃሉን ትርጉም በልምዳችን እንገድበዋለን። ሀሳባችን ከልምዳችን በላይ መሄድ አይችልም። ቸርነት የሚለውን ቃል ስንሰማ በህይወታችን ውስጥሉት መልካም ነገሮች ልምምድ ይወሰናል

የእኛ የመልካምነት ትርጓሜ ውስን ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው "እግዚአብሔር መልካም ነው" ሲል መልካምነቱን ልንገምት እንችላለን፡፡ ነገር ግን መልካምነትን በምናውቀው ሰው ላይ ከምናየው መልካምነት ባሻገር መገመት አንችልም። ለዚህም ነው ኢየሱስ ቸርነት የሚለው ቃል ከምድራዊው አባት ቸርነት ጋር እንዳይምታታ ቸርነት የሚለውን ቃል የበለጠ የገለፀው

እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ስጦታን አይሰጣቸውም? ማቴዎስ 711

የእግዚአብሄርን ቸርነት በጥሩ ሰው መልካምነት ከገደብነው የእግዚአብሄርን ቸርነት ሙሉ ለሙሉ ልንረዳውና ልንደሰትበት አንችልም።

የእግዚአብሔር ቸርነት ከማንም ሰው ቸርነት ጋር ሊወዳደር አይችልም። አምስ ምክንያቶች

v  የእግዚአብሔር ማስተዋል የማይመረመር ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል። እሱ የማያውቀው ነገር የለም፡፡ ሰፊ እውቀቱን ለጥቅማችን ይጠቀምበታል። አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 4028

v  እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ ሊጠረጠር አይችልም። እግዚአብሔር አፍቃሪ ብቻ ነው። እውነት ነው እኛም ፍቅርን እንለማመዳለን፡፡ ነገር ግን ፍቅራችን ከስግብግብነት እና ከራስ ወዳድነት ጋር ሊደባለቅ ስለሚችል ውስን ነው፡፡ በምድር ላይቀጣይነት ትግል ላይ ነን። የእኛ መልካምነት እንደ እግዚአብሔር መልካምነት ፍጹም ላይሆን ይችላል። የእግዚአብሔር ቸርነት ከፍቅሩ ጋር ፍጹም ነው።

v  እግዚአብሔር አይለወጥም፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል፡፡ አእምሮው የማይመረመር ነው፡፡ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። የያዕቆብ መልእክት 1፡17

v  እግዚአብሔር በሰማይ ይኖራል። እግዚአብሔር እኛ በምንፈተንበት በማንኛውም መንገድ አይፈተንም፣ የእግዚአብሔር ቸርነት ፍጹም ነው።

v  እግዚአብሔር ዋቢ ነው። እግዚአብሔር መልካም ብቻ አይደለም። እርሱ የመልካምነት ዋቢ ነው። እሱ የመልካምነት መለኪያ ነው። እሱ መልካም ነው የሚለው ሁሉ መልካም ነው፡፡ እሱ መልካም አይደለም የሚለው ሁሉ መልካም አይደለም፡፡ ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው ኢሳይያስ 520


The Goodness of God beyond Imagination

 


God is good. Good is so good that his goodness can’t be compared with anyone’s goodness.

We are limited. When we hear a word, we limit the meaning of the word with our experience. Our imagination can’t go beyond our experiences. When we hear the word goodness, we are limited in the experience we have with any goodness in our lives.

Our interpretation of goodness is limited. For instance, when someone says "God is good" we may guess, but we can’t imagine goodness beyond the goodness we see in the best person we know. That is the reason Jesus qualified the word goodness further, not to be confused with the goodness of the earthly father.

If you, then, though you are evil, know how to give good gifts to your children, how much more will your Father in heaven give good gifts to those who ask him! Matthew 7:11

If you limit the goodness of God with the best person's goodness, you know you get it wrong.

The goodness of God can’t be compared with any person’s goodness. Here are the seven reasons

-              God’s understanding is unsearchable. God knows everything. There is nothing he doesn’t know. He uses his vast knowledge for our good.

Do you not know? Have you not heard? The LORD is the everlasting God, the Creator of the ends of the earth. He will not grow tired or weary, and his understanding no one can fathom Isaiah 40:28

-          God is able. Not only God use his unsearchable wisdom for our good, God also use all his might for our goodness. 

 “I know that you can do all things; no purpose of yours can be thwarted. Job 42:2

-              God is love. God’s motive can’t be doubted. God only loves. We practice love, but we are limited as our love may be mixed with greed and selfishness. We are in a continuous struggle on earth. Our goodness may not be as perfect as God’s. God’s goodness is perfect with his love.

-              God doesn’t change. God knows everything; his understanding is unsearchable. Every good and perfect gift is from above, coming down from the Father of the heavenly lights, who does not change like shifting shadows.

-              God lives in heaven. God isn’t in any way tempted with anything we are tempted, God's goodness is perfect.

-              God is the reference. God isn’t only good. He is the reference of goodness. He is the very standard of goodness. Whatever he says is good, it is. Whatever he says is not good, it is not.

Woe to those who call evil good and good evil, who put darkness for light and light for darkness, who put bitter for sweet and sweet for bitter Isaiah 5:20

Thursday, August 18, 2022

እምነት ድንገተኛ አይደለም

 


እምነት ከቁሳዊው አለም ባሻገር መንፈሳዊውን አለም የምናይበት እጅግ አስፈላጊ መነፅር ነው፡፡ እኛም ከቁሳዊው አለም ባሻገር መንፈሳዊውን አለም በማየት በእምነት እንድንኖር በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ተፈጥረናል፡፡

በእምነት መመላለስ የትጉዎች አካሄድ እንጂ የሰነፎች አካሄድ አይደለም፡፡ እምነት በየእለቱ የምንለማመደው የህይወት ዘይቤያችን እንጂ ረስተንን ቆይተን የሆነ ነገር ሲፈጠር ብቻ ድንገት የምንመዘው ድንገተኛ አይደለም፡፡

እምነት ከትንሽ ጀምረን በየእለቱ በትጋት የምንለማመደውና የምናሳድገው ልምምድ እንጂ አንዳንዴ የምንመዘው መጠባበቂያ መሳሪያ አይደለም፡፡

ከእግዚአብሄር ጋር ባለን ግንኙነት እያንዳንዱ የህይወት እርምጃችን በቃሉ ላይ ባለ እምነት መመስረት አለበት፡፡ በእያንዳንዱ የህይወት እንቅስቃሴያችን ስለእኛ የተፃፈውን የእግዚአብሄርን ቃል ማመን እና መተግበር አለብን፡፡

እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስ 4፡4

ሰው የሚኖረው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል አይደለም፡፡ ሰው የሚኖረው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ በእያንዳንዱ ቃል ነው፡፡

እያንዳንዱ የኑሮ አቅጣጫችን የእግዚአብሄርን ቃል ማወቅ ፣ መረዳትና ማመን ይጠይቃል፡፡ የእምነት ልምምድ ሙሉ ጊዜያችንን ፣ ሙሉ ትኩረታችንን እና ሙሉ ህይወታችንን የሚጠይቅ የእለት ተእለት ተግባራችን እንጂ ረስተነው ድንገት የምንመዘው የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ መሳሪያ አይደለም፡፡ 

Monday, August 15, 2022

ስለ ነፍሱ



ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማቴዎስ 16:26

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው፡፡ ሰው ክቡር ነው፡፡ የሰው ፍላጎት በሚበላው በሚጠጣው እና በሚለብሰው ነገር አይሟላም፡፡ የሰው ፍላጎት ከፍ ያለ ነው፡፡

ሰው በስጋ ውጥ የሚኖር መንፈስ እንደመሆኑ መጠን ነፍሱ አምላክ ትፈልጋለች፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን እንዲያምልክ ተደርጎ ስለሆነ የሰው ነፍስ ሁልጊዜ የምታምነው የምትደገፈውን አምላክ ትጠማለች፡፡

የሰው ነፍስ የምትሰማውን የምትከለተለውን አምላክ ትናፍቃለች፡፡

የሰው ነፍስ ከእግዚአብሄር አምላክ ውጭ ምንም እንዳያረካት ተደርጋ ስለተፈጠረች በምንም በሌላ ነገር አትረካም፡፡ የሰው ነፍስ ይህን የአምላክነት ፍቅር የሚተካ ምንም ማስመሰያ ተመሳሳይ ነገር ቢቀርብላት አትረካም፡፡

የሰው ነፍስ የሚወዳትን እና የምትወደውን አምላክ ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ የምትከተልውንና የምትኖርለትን አምላክ ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ ፍቅር የምትሰጠውን እና የምትቀበለውን አምላክ ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ ራስዋን መስዋእት የምታደርግለትን ከእርስዋ ከፍ ያለ አምላክ ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ ለምን እንደምትኖር እውነተኛውን የኑሮን ትርጉም ማወቅ ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ አስፈላጊ መሆንዋን የሚያሳያት ፣ የሚያደንቃት ፣ የሚወዳት እና ዋጋን የሚሰጣት አምላክ ትፈልጋለች፡፡

ለነፍሳችን ሁሉን ነገር አድርገንላት እውነተኛውን እና ዋነኛውን ጥማትዋን እና ረሃብዋን ካላረካንላት ምን ይጠቅማታል? ለነፍሳችን ተመሳሳዩን ነገር ሁሉ ሰጥተናት እውነተኛውን ዋናውን ነገር ካልሰጠናት ምን ይጠይቅማታል?

Sunday, August 14, 2022

ያድናል ኢየሱስ ያድናል - ዘሪቱ ከበደ || Yadinal Eyesus Yadinal - Zeritu Kebede

የክርስትና ሚሊየነርነት

 

በአለም ላይ የተለያዩ የክንውን መመዘኛዎች አሉ፡፡ እያንዳንዱ የስኬት መመዘኛ እንደዋጋ አሰጣጡ ይለያያል፡፡

በክርስትናም "ይህ ሰው ኑሮው ሲያስቀና ውይ ታድሎ" የሚባልለት ሰው አለ፡፡ በክርስትና የተሳካለት የተከናወነለት የሚባለው ሰው ምን አይነት ሰው እንደሆነ የህይወት መመሪያችን የሆነው በህይወታችን ላይ የመጨረሻው ስልጣን ያለው መፅሃፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡  

በክርስትና "ይህ ሰው ሲያስቀና" የሚባልለት እና እጅግ የተከናወነለት ሰው እግዚአብሄርን ስለ መሰረታዊ ፍላጎቱ የሚያምን እና ጌታን የሚከተለ ሰው ነው፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33

ለሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ ጌታን ከመከተል በላይ የስኬት እና የክንውን ጣራ የለም፡፡ ሰው መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ ጌታን ከተከተለ ከእርሱ በላይ በእውነት የተከናወነለት ሰው በምድር ላይ የለም፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8

ከምትበላው ከምትጠጣው ከምትለብሰው በላይ እግዚአብሄር ቢሰጥህ ለአንተ አይደለም፡፡ አንተ የተሰጠህ ሃብት ባለ አደራ እንጂ ባለቤት አይደለህም፡፡ እግዚአብሄር ድርጅት ቢሰጥህ ብዙዎች ተቀጥረው ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩበት የልጃቸውን የትምህርት ቤት የሚከፍሉበት እንጂ የአንተ አይደለም፡፡

ምንም ባለሃብት ብትሆን ከመሰረታዊ ፍላጎት ከምትበላው ፣ ከምትጠጣው እና ከምትለብሰው በላይ አትጠቀምም፡፡ ምንም ዝና ቢኖርህ ሰዎች እንዲቀበሉህ እና በውስጥ ያለውን ክህሎት እንዲጠቀሙ የተሰጠህ ስጦታ እንጂ የአንተ ሃብት አይደለም፡፡ ምንም ሃያል ብትሆን እንድትባርክበት የተሰጠህ እድል እንጂ የአንተ ሃብት አይደለም፡፡ ምንም ጥበበኛ ብትሆን ለሰዎች በህይወት የሚያሸንፉበትን ጥበብ እንድታካፍል የተሰጠህ ስጦታ እንጂ የአንተ አይደለም፡፡   

የእኔ ነው የምትለው እውነተኛው ሃብት እና የስኬት ጣሪያው ለመሰረታዊ ነገር ጌታን ማመን እና ጌታ ኢየሱስን ማመን እና መከተል ብቻ ነው፡፡