Popular Posts

Monday, August 23, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 8

ሃጢያት ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡

እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን። ዘፍጥረት 1፡31

እግዚአብሄር ሃጢያትን አልፈጠረም፡፡ እንዲሁም እግዚአብሄር በሽታን አልጠረም፡፡ ሃጢያትና  በሽታ የመጣው ከሰይጣን ነው፡፡ ሰው በሰይጣን ተታሎ በሃጢያት እስራት ከወደቀ በኋላ ከበሽታ እስራል ላይ ወደቀ፡፡

ሰይጣን የሚመጣው የሰዎችን ህይወት ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ነው፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ፣ ማረድና ማጥፋት ውጭ ሌላ ምንም አላማ የለውም፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሐንስ 10፡10

ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ የሰዎችን ነፍስ ከሃጢያት እስራት ለመፍታት እንዳገለገለ ሁሉ በሃጢያት መክኒያት ወደምድር የገባውን የሰዎችንም በሽታ በትጋት ይፈውስ ነበር፡፡

ኢየሱስ ሰዎችን ከሃጢያት እስራት ለማላቀቅ ይሰብክ እንደነበር ሁሉ ከበሽታቸው ለማላቀቅ በቅናት ይፈውሳቸው ነበር፡፡ 

የኢየሱስን አገልግሎት በአጠቃላይ የኢየሱስን የምድር አገልግሎት ስናይ ለበሽታ የነበረን ጥላቻ እንመለከታለን፡፡ የኢየሱስን የምድር አገልግሎት ስናይ ሰዎችን ከህመማቸው ለማላቀቅ በቅናት ሲያገለግል እንመለከታለን፡፡

እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ ሐዋሪያት 1038 

ኢየሱስ እንድም ቦታ ነፍሳችሁ ከዳነ ስጋዋ ባይፈወስም ችግር የለውም ሲል አንመለከተውም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Sunday, August 22, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 7

ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ስለነፍሳችን ዋጋ ሊከፍል ብቻ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ስለነፍሳችን ሃጢያት ዋጋ ሊከፍልና እንዲሁም ደግሞ በሃጢያት ምክኒያት ስለመጣብን በሽታ ዋጋን ሊከፍል ጭምር ነው፡፡ ኢየሱስ ስለ ሃጢያታችን ሞተ ስለህመማችን ተገረፈ፡፡

በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። ማቴዎስ 8፡16-17

ሰው ነፍሱ ሁሉ ድኖ ነገር ግን ስጋው ካልተፈወሰ በምድር ላይ እግዚአብሄርን እንደሚገባው ሊያገለግል አይችልም፡፡ የሰው ነፍስ ከእስራት ድኖ ስጋው ግን ከህማምና ከበሽታ ነፃ ካልሆነ እግዚአብሄርን በምድር ላይ እንደሚገባው ለረጅም ጊዜ ሊያገለግል አይችልም፡፡  

ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡24

ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰ ጊዜ ሁሉ ስለነፍስ የሃጢያት እስራት መድሃኒት የሆነውን የእግዚአብሄርን ቃል ሰብኮዋል፡፡ እንዲሁም ስለስጋቸው መፈወስ በትጋት የፈውስ አገልግሎትን ሲያደርግ እንመለከተዋለን፡፡

እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ ሐዋሪያት 10፡38 

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Saturday, August 21, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 6

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 6

እግዚአብሄር ሰዎችን መፈወስ ይወዳል፡፡ 

ኢየሱስ በምድር ላይ በሚመላለስበት ጊዜ አንድ ለምፃም ወደ እርሱ ቀርቦ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ አለው፡፡ ለምፃሙ ስለኢየሱስ የመፈወስ ችሎታ አልተጠራጠረም፡፡ 

ብዙ ሰው ስለእግዚአብሄር የመፈወስ ችሎታ አይጠራጠርም፡፡ 

አንዳንድ ሰው ግን ፈውስ የእግዚአብሄር ፈቃድ እንደሆነ እርግጠኛ አይደለም፡፡ 

እነሆም፥ ለምጻም ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወዳለሁ፥ ንጻ አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ። ማቴዎስ 8፡2-3

የኢየሱስ መልስ ግን እግዚአብሄር ሰዎችን መፈወስ እንደሚችል ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር ሰዎችን መፈወስ እንደሚፈልግና እንደሚወድ ያሳያል፡፡ 

አንደኛው የእግዚአብሄር ስም ፈዋሽ አምላክ የሚል ነው፡፡ እግዚአብሄር በመፈወስ ይታወቃል፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን ሙሉ በማድረግ 

ኢየሱስንም በታላቅ ቅናት እና ትጋት በያሉበት ሁሉ በመሄድ ሰዎችን ይፈውስ ነበር፡፡ 

እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ ሐዋሪያት 10፡38

ይህ የኢየሱስ አገልግሎት የእግዚአብሄርን የመፈወስ ታላቅ ቅናት ያሳያል፡፡ 

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Friday, August 20, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 5

የእስራኤል ህዝብ የእግዚአብሄር ብቸኛ ህዝብ ነበሩ፡፡ እግዚአብሄር የእስራኤልን ህዝብ የያዘበትን መንገድ በመመልከት እግዚአብሄር ህዝቡን እንዴት እንደሚይዝና እንደሚንከባከብ መመልከት ይቻላል፡፡

የእስራኤል ህዝብ በበደላቸው ምክኒያት እባብ በነደፋቸው ጊዜ እንኳን እግዚአብሄር እነርሱን የሚፈልግበትን መንገድ ከመፈለግ አላቆመም፡፡

ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው። ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።  ዘኍልቍ 21፡8-9

እግዚአብሄር በየጊዜው እንዴት ራሳቸውን በጤንነት እንደሚይዙ እና ጤንነታችውን ካጡትም አንዴት መልሰው እንደሚፈወሱ በነቢያቶቻቸው በኩል ያስተምራቸው ነበር፡፡

ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል። ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት። ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና። ምሳሌ 4፡20-22

እነሆ፥ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፥ እፈውሳቸውማለሁ፤ የሰላምንና የእውነትን ብዛት እገልጥላቸዋለሁ። ኤርሚያስ 33፡6

አቤቱ፥ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ፤ አድነኝ እኔም እድናለሁ፤ አንተ ምስጋናዬ ነህና። ኤርሚያስ 17፡14

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Thursday, August 19, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 4

አንደኛው የእግዚአብሄር ስም ፈዋሽ አምላክ የሚል ነው፡፡  እግዚአብሄር በመፈወስ ይታወቃል፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን ሙሉ በማድረግ ይታወቃል፡፡

ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥ መዝሙር 103፡2-3

ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለስ ጊዜ ከበሽታቸው የፈወሳቸውንና ከአጋንንት እስራት ነፃ ያወጣቸውን ሰዎች ያዩ ሰዎች ሁሉን ደኅና አድርጎአል ብለው መስክረውለታል፡፡

ያለ መጠንም ተገረሙና፦ ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል አሉ። ማርቆስ ወንጌል 737

መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው (ዮሐንስ 1፡18) ተብሎ እንደተፃፈ የእግዚአብሄር ልብ ያየንበት የኢየሱስ አገልግሎትን ስንመለከት እግዚአብሄር ሰዎችን ለመፈወስ ምን ያህል እንደሚፈልግ እንመለከታለን፡፡

በአጠቃላይ የኢየሱስን የምድር አገልግሎት እና ኢየሱስ በሽታን የሚያይበትን መንገድ ስንመለከት እግዚአብሄር ምን ያህል የሰዎችን ጤንነት እንደሚፈልግ እንመለከታለን፡፡

እግዚአብሄር ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ እና በሃይልም ቀባው፡፡ እግዚአብሄር ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ ብቻ አይደለም በሃይልም ቀብቶታል፡፡ ለሰው ልጆች ፈውስና ነፃ መውጣት እግዚአብሄር ያለውን ሃይል ሁሉ በኢየሱስ ላይ አፍስሶዋል፡፡ 

እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ ሐዋርያት ሥራ 10፡38

ኢየሱስንም በታላቅ ቅናት እና ትጋት በያሉበት ሁሉ በመሄድ ሰዎችን ይፈውስ ነበር፡፡

ይህ የኢየሱስ አገልግሎት የእግዚአብሄርን የመፈወስ ቅናት ያሳያል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Wednesday, August 18, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 3

እግዚአብሄር በእስራኤላዊያን ብርታትና ጤንነት ደስ ይለው ነበር፡፡

ሰው ምግቡን እና የሚጠጣውን ካስተካከለ ምግብን በማስተካል ብቻ አብዛኛውን በሽታ መከላከልና መቋቋም እንደሚቻል ሳይንስ ያስተምራል፡፡ ምክኒያቱም የምንበላው ምግብ እና የምንጠጣው መጠጥ ለጤንነታችን ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል እንዲሁም የምብላውነማ የምንጠጣው ጤንነታችንን ሊያውክ ይችላል፡፡

እግዚአብሄር የምንበላውንና የምንጠጣውን ከባረከ ምግቡና መጠጡ ይስማማናል ፣ ጤንነታችንን ያበዛዋል እንዲሁም በሽታ የመከላከል አቅማችንን በእጅጉ ያሳድገዋል፡፡

አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ። ዘጸአት 23፡25

በብሉይ ኪዳን እስራኤላዊያን የእግዚአብሄር ብቸኛ ህዝብ ነበሩ፡፡ እግዚአብሄር ከእስራኤላዊያን ጋር የነበረው ግንኙነት በመመልከት እግዚአብሄር ከህዝቡ ጋር ስላለው ግንኙነት እግዚአብሄር ስለ ህዝቡ ፈውስ እና ጤንነት ብዙ ነገር መማር ይቻላል፡፡

እግዚአብሄር ስለ ጤንነታችን ግድ ይለዋል፡፡

እስራኤላዊያን ከግብፅ ሲወጡ በመካከላቸው አንድም በሽተኛ አለመኖሩ እግዚአብሄር ለህዝቡ ጤንነት እና ጥንካሬ ምን ያህል ግድ እንደሚለው ያሳያል፡፡  

ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም። መዝሙር 105፡37

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Tuesday, August 17, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 2

እግዚአብሄር በሰዎች ብርታትና ጤንነት ደስ ይለዋል፡፡

እግዚአብሄር ከማናችንም ጋር አይፎካከርም፡፡ እግዚአብሄር ከማናችንም ጋር እልኽ ውስጥ አይገባም፡፡ እግዚአብሄር የማናችንም ጤንነት አያስቀናውም፡፡

እግዚአብሄር በመጀመሪያም የፈጠረን ለብርታትና ለጤንነት ስለሆነ ስንወጣ ስንገባ ስንሰራ ፍሬያማ እና ምርታማ ስንሆን ደስ ይለዋል፡፡

የጤንነታችን አንደኛ ደጋፊ እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡

እግዚአብሄር በሽታን በሁሉም አቅጣጫ ይቃወመዋል፡፡ እግዚአብሄር ሰዎች በቃሉ ሲያምኑ እንዲፈወሱ የፈውስን ቃል አዘጋጅቶዋል፡፡

ክርስቶስን የሚከተሉ ሰዎች ሲታመሙ የሚፈወሱበትን መንገድ ጌታ አዘጋጅቶዋል፡፡

ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። ያዕቆብ 5፡14-15

ሰዎች የፈውስን ቃል ከመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልገው ሲያገኙና ሲያምኑ የእግዚአብሄር ፈውስ በመለኮታዊ አሰራር የእግዚአብሄር ፈውስ በህይወታቸው ያልፋል፡፡

እግዚአብሄር ተአምራዊ የፈውስን ስጦታ ብቻ ሳይሆን ሰዎች በሳይንሳዊ ህክምና ከበሽታቸው እንዲገላገሉ በየዘመናቱ እግዚአብሄር ለባህላዊና ለዘመናዊ የህክምና ባለሙያዎች ጥበብን ይሰጣል፡፡

እግዚአብሄር በሽታን የሚዋጋው አንድም ሳያስቀር በሁሉም ግንባር ነው፡፡