ዳሩ
ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29
እግዚአብሄር ከጥንት ሰውን የፈጠረው ሙሉ አድርጎ
ነው፡፡ ሰው ልጅ ለመውለድ እንጂ ሙሉ ለመሆን ማግባት አያስፈልገው ነበር፡፡
አሁንም ሰው ማግባት ያለበት ሙሉ ከሆነ ብቻ
ነው፡፡ ሰው ሙሉ ለመሆን የሚያገባ ከሆነ በትዳር ውስጥ የማይገኝን ነገር ጠብቆ ስለሚያገባ በመንገዱ ይሰናከላል፡፡
ወንድ አንድን ሴት ካላንቺ መኖር አልችልም ህይወቴን
ሙሉ የምታደርጊው አንቺ ብቻ ነሽ ካለ ተሳስቶዋል፡፡
ሰው ከማግባቱ በፊት ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን
ግንኙነት ማስተካከል አለበት፡፡ ሰው ከማግባቱ በፊት የሚያስፈለግውን ነገር ከእግዚአብሄር እንዴት እንደሚቀበል መማር አለበት፡፡
ሰው ከማግባቱ በፊት ከእግዚአብሄር እንዴት ለምኖ እንደሚቀበል ማወቅ አለበት፡፡
ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ባለው ህብረት ሙሉ ሳይሆን
ሚስት ሙሉ ታደርገኛለች ብሎ በከንቱ ከጠበቀ ይሳሳታል፡፡
ትዳር ሚስት ባልዋን ባል ሚስቱን ሙሉ የሚያደርግበት
መድረክ ሳይሆን ሁለት ሙሉ የሆኑ ባልና ሚስት በቤተሰብ የእግዚአብሄርን አላማ የሚፈፅሙበት መድረክ ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሚስት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ባል #እምነት
#ወንድ #ፍቅር
#ትዳር #ሰላም
#ሴት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment