Popular Posts

Saturday, January 6, 2024

ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ ክፍል 1

በምድር ላይ በህይወት ስኬታማ መሆን የማይፈልግ ሰው የለም፡፡ በተለይ ደግሞ በጋብቻው ስኬታማ መሆን የማይፈልግ ጤነኛ ሰው በአለም ላይ አይገኝም፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ያስቀመጠውን ሙሉ በረከት ተጠቃሚ የምንሆነው የእግዚአብሄርን የትዳር አላማ ከእግዚአብሔርን ቃል ስንረዳ ብቻ ነው፡፡

ታዲያ ከጋብቻ ቁልፍ መርሆዎች አንዱ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ የሚለው ትእዛዝ ነው፡፡

ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29

ወንድ የትዳር አጋሩን ሲመርጥ ካለ እርስዋ መኖር አልችልም የሚላትን ሴት ለትዳር ከመረጠ የትዳር አላማውን መሳቱ ብቻ ሳይሆን ትልቅ ችግር ውስጥ ይወድቃል፡፡

ሰው ካገባም በኋላ ሚስቱን ካጣ ህይወቱ እንደሚጠፋ አድረጎ ፈርቶ ብቻ በትዳር ከኖረ እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ያዘጋጀውን እውነተኛውን በረከት በሙላት መካፈል አይችልም፡፡

በሚቀጥሉት ተከታታይ ትምህርቶች ከዚህ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መርህ አንፃር እግዚአብሄር የትዳር አጋራችንን እንዴት እንደምንመርጥ እና በቀጣይነት ከትዳር አጋራችን ጋር እንዴት እንደምንኖር እንመለከታለን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች

#ያገባ #ያላገባ #አላፊ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ባል #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ


 

No comments:

Post a Comment