Popular Posts

Monday, January 8, 2024

ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ! ክፍል 3

 


ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 729

ይህን የመፅሃፍ ቅዱስ መርህ ለመረዳት እግዚአብሄር ትዳርን የፈጠረበትን የጥንቱን አላማ በጥቂቱ እንመልከት፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ሙሉ እና ፍፁም አድርጎ ነው፡፡ ሰው የሚጎድለው ምንም ነገር አልነበረም፡፡

እግዚአብሄር ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ያለው ሰው ለህይወት የሚጎድለው አንዳች ነገር ስለነበረ አይደለም፡፡

ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ፍጹም የሆነ የአባትና የልጅ ግንኙነት ነበረው፡፡ ሰው ምንም አይነት ድካም አልነበረበትም፡፡ ሰው የሚጎድለው አንዳች ነገር አልነበረም፡፡

ታዲያ እግዚአብሄር ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ያለው "ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥" የሚለውን የመባዛት አላማ ብቻውን መፈፀም ስለማይችል ብቻ ነበር፡፡

በአጠቃላይ ሰው እንዲያውም ሚስት ያገባው ሙሉ ሰው ስለነበረ እንጂ ሙሉ ለመሆን ፈልጎ አልነበረም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ያገባ #ያላገባ #አላፊ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ባል #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ


No comments:

Post a Comment