ዳሩ ግን፥ ወንድሞች
ሆይ፥ ይህን
እናገራለሁ፤ ዘመኑ
አጭር ሆኖአል፤
ከእንግዲህ ወዲህ
ሚስቶች ያሉአቸው
እንደሌላቸው ይሁኑ፥
1ኛ ወደ
ቆሮንቶስ ሰዎች
7፡29
የትዳር አላማ አንዱ ሌላውን በመባረክ እግዚአብሄር
በትዳር ውስጥ ያስቀመጠውን የእግዚአብሄርን መልክ ማንፀባረቅ ነው፡፡
የእግዚአብሄር ሙሉ መልክ የሚንፀባረቀው በባልና
በሚስት ጋብቻ ውስጥ ነው፡፡
እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1
ሰው ታዲያ ይህ ትዳር የእግዚአብሄር አላማ አለበት
ብሎ የእግዚአብሄርን አላማ ለመፈፀም መስራት እና መትጋት አለበት፡፡
ከዚህ መፅሃፍ ቅዱሳዊ አላማ ያነሰ የትዳር አላማ
ከደረጃ በታች እና ርካሽ የሆነ አላማ ነው፡፡
ሰው ማግባት ያለበት ትዳሩ የእግዚአብሄር አላማ
አለበት ብሎ መሆን አለበት፡፡ በትዳር የእግዚአብሄርን አላማ ከመፈፀም ያነሰ ከደረጃ በታች የሆነ ርካሽ አላማ ነው፡፡
ሰው በትዳር ውጤታማ የሚሆነው ትዳሩ የእግዚአብሄር
አላማ እንዳለበት አውቆ ሲከተለው ብቻ ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር አላማ ባነሰ አላማ በትዳር ከቆየ እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ያዘጋጀውን
ሙሉ በረከት ተጠቃሚ ሳይሆን ህይወቱን ያባክናል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሚስት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ባል #እምነት
#ወንድ #ፍቅር
#ትዳር #ሰላም
#ሴት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment