ዳሩ ግን፥ ወንድሞች
ሆይ፥ ይህን
እናገራለሁ፤ ዘመኑ
አጭር ሆኖአል፤
ከእንግዲህ ወዲህ
ሚስቶች ያሉአቸው
እንደሌላቸው ይሁኑ፥
1ኛ ወደ
ቆሮንቶስ ሰዎች
7፡29
ሰው ሚስት የሚያገባው በዋነኝነት ለመስጠት እና
ለመባረክ መሆን አለበት፡፡ ሚስት ባል የምታገባው በዋነኝነት አንድን ባለራእይ ወንድ እግዚአብሄር በሰጣት ፀጋ እና ችሎታ ለመደገፍ
እና ለመርዳት መሆን አለበት፡፡
ባል በሚያገኘው ጥቅም ላይ አተኩሮ ለማግባ ቢነሳሳ
ከትዳሩ የሚጠበቀው ያህል በረከት እና ፍሬ አይገኝም፡፡ ሚስት ጤናማ ባልሆነ መንገድ በባልዋ ላይ የምትደገፍ ከሆነ ትዳሩ እግዚአብሄር
በትዳር ውስጥ ያስቀመጠውን ግብ ሊመታ አይችልም፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ "ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው
ይሁኑ" ማለት ወይም በሌላ አነጋገር ባሎች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ ማለት ባል በሚስቱ ላይ ጤናማ ያልሆነ መደገፍ አይደገፍ
ሚስት በባልዋ ላይ ጤናማ ያልሆነ መደገፍ አትደገፍ ማለት ነው፡፡
ሚስት ከባልዋ መጠበቅ የሌላባት ነገር አለ፡፡
ባል ከሚስቱ መጠበቅ የሌለበት ነገር አለ፡፡ ሰው ለማግባት ከእግዚአብሄ ጋር እንዴት እንደሚኖር አስቀድሞ ማወቅ አለበት የሚባለው
ስለዚህ ነው፡፡ ባልም ሆነ ሚስት ሳገባ ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት መኖር እንዳለብኝ አውቃለሁ ካሉ ይሳሳታሉ፡፡
ትዳር ባልን ሚስትን ሚስት ባልዋን በዋነኝነት
የሚያገለግሉበት እና የሚጠቅሙበት መድረክ እንጂ በዋነኝነት በመጠቀም እና በመባረክ ላይ ትኩረት አደርገው የሚገቡበት መድረክ አይደለም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሚስት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ባል #እምነት
#ወንድ #ፍቅር
#ትዳር #ሰላም
#ሴት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment