I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Monday, January 29, 2024
Friday, January 26, 2024
Monday, January 22, 2024
Thursday, January 18, 2024
Sunday, January 14, 2024
ያልተጋባች ሴትና ድንግል
ያልተጋባች ሴትና ድንግል
1ኛ ቆሮንጦስ 7:34 ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።
ጋብቻ ክቡር ነው:: ለሁሉም ሰው ግን አይደለም::
ጋብቻ ክቡር ነው ግዴታ ግን አይደለም:: ያገባ በህይወቱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሊፈፅም እንደሚችልሁሉ ያላገባ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈፀም ይችላል: የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈፀምንበተመለከተ ባገባና ባላገባ መካከል ልዩነት የለም::
እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር። 1ኛ ቆሮንጦስ 7:20
ያላገባ የእግዚአብሔርን አላማ ሊስት ይችላል:: ያገባ እግዚአብሔር በህይወቱ ያስቀመጠውን አላማተከትሎ እግዚአብሔርን ሊያከብር ይችላል::
የሰው ታማኝነት በማግባት እና ባለማግባት አይመዘንም::
እንዲያውም ካገባ ይልቅ ያላገባ አሳቡ ሳይከፋፈል እግዚአብሔርን ሊያገለግልበት የሚችልበት ሰፊእድል አለው::
አንዳንድ ሰዎችን አሳባቸው በባል ወይም በሚስት እንዳይከፋፈል የሚፈልጋቸው ሰዎች አሉ::
እግዚአብሔር ለራሱ ብቻ አገልጋይ እንዲሆኑ የሚቀናባቸው ሰዎች አሉ::
1ኛ ቆሮንጦስ 7:34 ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን#መፅሃፍቅዱስ #ባል #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
Saturday, January 13, 2024
ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ! ክፍል 7
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች
ሆይ፥ ይህን
እናገራለሁ፤ ዘመኑ
አጭር ሆኖአል፤
ከእንግዲህ ወዲህ
ሚስቶች ያሉአቸው
እንደሌላቸው ይሁኑ፥
1ኛ ወደ
ቆሮንቶስ ሰዎች
7፡29
የትዳር አላማ አንዱ ሌላውን በመባረክ እግዚአብሄር
በትዳር ውስጥ ያስቀመጠውን የእግዚአብሄርን መልክ ማንፀባረቅ ነው፡፡
የእግዚአብሄር ሙሉ መልክ የሚንፀባረቀው በባልና
በሚስት ጋብቻ ውስጥ ነው፡፡
እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1
ሰው ታዲያ ይህ ትዳር የእግዚአብሄር አላማ አለበት
ብሎ የእግዚአብሄርን አላማ ለመፈፀም መስራት እና መትጋት አለበት፡፡
ከዚህ መፅሃፍ ቅዱሳዊ አላማ ያነሰ የትዳር አላማ
ከደረጃ በታች እና ርካሽ የሆነ አላማ ነው፡፡
ሰው ማግባት ያለበት ትዳሩ የእግዚአብሄር አላማ
አለበት ብሎ መሆን አለበት፡፡ በትዳር የእግዚአብሄርን አላማ ከመፈፀም ያነሰ ከደረጃ በታች የሆነ ርካሽ አላማ ነው፡፡
ሰው በትዳር ውጤታማ የሚሆነው ትዳሩ የእግዚአብሄር
አላማ እንዳለበት አውቆ ሲከተለው ብቻ ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር አላማ ባነሰ አላማ በትዳር ከቆየ እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ያዘጋጀውን
ሙሉ በረከት ተጠቃሚ ሳይሆን ህይወቱን ያባክናል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሚስት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ባል #እምነት
#ወንድ #ፍቅር
#ትዳር #ሰላም
#ሴት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
Friday, January 12, 2024
ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ! ክፍል 6
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች
ሆይ፥ ይህን
እናገራለሁ፤ ዘመኑ
አጭር ሆኖአል፤
ከእንግዲህ ወዲህ
ሚስቶች ያሉአቸው
እንደሌላቸው ይሁኑ፥
1ኛ ወደ
ቆሮንቶስ ሰዎች
7፡29
ጋብቻ ክቡር ነው፡፡ ጋብቻ እግዚአብሄር አላማ
የምንፈፅምበት ወርቅማ እድል ነው፡፡ ይህ ግን የሚሆነው ባልም ሆነ
ሚስት በየግላቸው እኔ ለትዳሩ ምን አድርጋለሁ? ምን የምሰጠው ነገር አለኝ? ምን አበረክታለሁ? በሚለው ሃላፊነታቸው ላይ ሲያተኩሩ
ብቻ ነው፡፡
ትዳር የሚሰምረው የትዳር አጋሩ ከደስታ እና
ከሙላት ሲያገባ እና ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ሰው ስለጎደለው የሚያገባ ከሆነ ትዳር በዋነኝነት የሰውን ጉድለት ለማሟላት ያልታቀደ ስለሆነ
ይሰናከላል፡፡ ሰው በትዳር የሚቆየው በዋነኝነት እንዳይጎድለው በምስኪን እኔ አስተሳሰብ ከሆነ እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ያስቀመጠውን
በረከት ሳያገኝ ይቀራል፡፡
ባል ሚስቱን ለመባረክ እና የተባረከች እና የሚቀናባት
ሴት በማድረግ ላይ ሲያተኩር ትዳሩ ይሰምራል፡፡ ሴትም ባልዋን እንዲወጣ እንዲያሸንፍ በመርዳት ላይ ስታተኩር እና ስትደግፈው ትዳሩ
እግዚአብሄር ያቀደለትን አላማ ይፈፅማል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሚስት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ባል #እምነት
#ወንድ #ፍቅር
#ትዳር #ሰላም
#ሴት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
Thursday, January 11, 2024
ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ! ክፍል 5
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች
ሆይ፥ ይህን
እናገራለሁ፤ ዘመኑ
አጭር ሆኖአል፤
ከእንግዲህ ወዲህ
ሚስቶች ያሉአቸው
እንደሌላቸው ይሁኑ፥
1ኛ ወደ
ቆሮንቶስ ሰዎች
7፡29
ሰው ሚስት የሚያገባው በዋነኝነት ለመስጠት እና
ለመባረክ መሆን አለበት፡፡ ሚስት ባል የምታገባው በዋነኝነት አንድን ባለራእይ ወንድ እግዚአብሄር በሰጣት ፀጋ እና ችሎታ ለመደገፍ
እና ለመርዳት መሆን አለበት፡፡
ባል በሚያገኘው ጥቅም ላይ አተኩሮ ለማግባ ቢነሳሳ
ከትዳሩ የሚጠበቀው ያህል በረከት እና ፍሬ አይገኝም፡፡ ሚስት ጤናማ ባልሆነ መንገድ በባልዋ ላይ የምትደገፍ ከሆነ ትዳሩ እግዚአብሄር
በትዳር ውስጥ ያስቀመጠውን ግብ ሊመታ አይችልም፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ "ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው
ይሁኑ" ማለት ወይም በሌላ አነጋገር ባሎች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ ማለት ባል በሚስቱ ላይ ጤናማ ያልሆነ መደገፍ አይደገፍ
ሚስት በባልዋ ላይ ጤናማ ያልሆነ መደገፍ አትደገፍ ማለት ነው፡፡
ሚስት ከባልዋ መጠበቅ የሌላባት ነገር አለ፡፡
ባል ከሚስቱ መጠበቅ የሌለበት ነገር አለ፡፡ ሰው ለማግባት ከእግዚአብሄ ጋር እንዴት እንደሚኖር አስቀድሞ ማወቅ አለበት የሚባለው
ስለዚህ ነው፡፡ ባልም ሆነ ሚስት ሳገባ ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት መኖር እንዳለብኝ አውቃለሁ ካሉ ይሳሳታሉ፡፡
ትዳር ባልን ሚስትን ሚስት ባልዋን በዋነኝነት
የሚያገለግሉበት እና የሚጠቅሙበት መድረክ እንጂ በዋነኝነት በመጠቀም እና በመባረክ ላይ ትኩረት አደርገው የሚገቡበት መድረክ አይደለም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሚስት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ባል #እምነት
#ወንድ #ፍቅር
#ትዳር #ሰላም
#ሴት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
Tuesday, January 9, 2024
ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ! ክፍል 4
ዳሩ
ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29
እግዚአብሄር ከጥንት ሰውን የፈጠረው ሙሉ አድርጎ
ነው፡፡ ሰው ልጅ ለመውለድ እንጂ ሙሉ ለመሆን ማግባት አያስፈልገው ነበር፡፡
አሁንም ሰው ማግባት ያለበት ሙሉ ከሆነ ብቻ
ነው፡፡ ሰው ሙሉ ለመሆን የሚያገባ ከሆነ በትዳር ውስጥ የማይገኝን ነገር ጠብቆ ስለሚያገባ በመንገዱ ይሰናከላል፡፡
ወንድ አንድን ሴት ካላንቺ መኖር አልችልም ህይወቴን
ሙሉ የምታደርጊው አንቺ ብቻ ነሽ ካለ ተሳስቶዋል፡፡
ሰው ከማግባቱ በፊት ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን
ግንኙነት ማስተካከል አለበት፡፡ ሰው ከማግባቱ በፊት የሚያስፈለግውን ነገር ከእግዚአብሄር እንዴት እንደሚቀበል መማር አለበት፡፡
ሰው ከማግባቱ በፊት ከእግዚአብሄር እንዴት ለምኖ እንደሚቀበል ማወቅ አለበት፡፡
ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ባለው ህብረት ሙሉ ሳይሆን
ሚስት ሙሉ ታደርገኛለች ብሎ በከንቱ ከጠበቀ ይሳሳታል፡፡
ትዳር ሚስት ባልዋን ባል ሚስቱን ሙሉ የሚያደርግበት
መድረክ ሳይሆን ሁለት ሙሉ የሆኑ ባልና ሚስት በቤተሰብ የእግዚአብሄርን አላማ የሚፈፅሙበት መድረክ ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሚስት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ባል #እምነት
#ወንድ #ፍቅር
#ትዳር #ሰላም
#ሴት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
Monday, January 8, 2024
ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ! ክፍል 3
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች
ሆይ፥ ይህን
እናገራለሁ፤ ዘመኑ
አጭር ሆኖአል፤
ከእንግዲህ ወዲህ
ሚስቶች ያሉአቸው
እንደሌላቸው ይሁኑ፥
1ኛ ወደ
ቆሮንቶስ ሰዎች
7፡29
ይህን የመፅሃፍ ቅዱስ መርህ ለመረዳት እግዚአብሄር
ትዳርን የፈጠረበትን የጥንቱን አላማ በጥቂቱ እንመልከት፡፡
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ሙሉ እና ፍፁም
አድርጎ ነው፡፡ ሰው የሚጎድለው ምንም ነገር አልነበረም፡፡
እግዚአብሄር ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም
አይደለም ያለው ሰው ለህይወት የሚጎድለው አንዳች ነገር ስለነበረ አይደለም፡፡
ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ፍጹም የሆነ የአባትና
የልጅ ግንኙነት ነበረው፡፡ ሰው ምንም አይነት ድካም አልነበረበትም፡፡ ሰው የሚጎድለው አንዳች ነገር አልነበረም፡፡
ታዲያ እግዚአብሄር ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ
መልካም አይደለም ያለው "ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥" የሚለውን የመባዛት አላማ ብቻውን መፈፀም ስለማይችል
ብቻ ነበር፡፡
በአጠቃላይ ሰው እንዲያውም ሚስት ያገባው ሙሉ
ሰው ስለነበረ እንጂ ሙሉ ለመሆን ፈልጎ አልነበረም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ባል #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
Sunday, January 7, 2024
ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ! ክፍል 2
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤
ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29
እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ካስቀመጠው በረከት
አንፃር ባል ከሚስቱ የሚጠቀመው ነገር አለ ሚስትም ከባልዋ የምትጠቀመው ነገር አለ፡፡
የዚህ ጥቅስ ትእዛዝ ባል ከሚስቱ ሚስትም ከባልዋ
አትጠቀም የሚል ማስጠንቀቂያ አይደለም፡፡ የዚህ ትእዛዝ አላማው ባል ከሚስቱ በሚጠቀመው ጥቅም ላይ ከመጠን ያለፈ እንዳይደገፍ እንዲጠነቀቅ
ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ ሚስት ከባልዋ በምትጠቀመው ጥቅም ላይ ከመጠን ያለፈ እንዳትደገፍ እና እንድትጠነቀቅ ብቻ ነው፡፡
ምንም አይነት መልካም ነገር ከመጠን ሲያልፍ
መጀመሪያ የተፈጠረበትን አላማውን ይስታል፡፡ ምንም መልካም ነገር ከመጠን ሲያልፍ ይጎዳል፡፡
ባል በሚስቱ ላይ ያለው ከመጠን ያለፈ መደገፍ
የትዳርን አላማ ያስተዋል፡፡ ሚስት በባልዋ ላይ ያላት ከመጠን ያለፈ መደገፍ በትዳሩ ውስጥ እግዚአብሄር ያዘጋጀውን በረከት በሙሉ
ተጠቃሚ እንዳትሆን እንቅፋት ይሆንባታል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሚስት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ባል #እምነት
#ወንድ #ፍቅር
#ትዳር #ሰላም
#ሴት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
Saturday, January 6, 2024
ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ ክፍል 1
በምድር
ላይ በህይወት ስኬታማ መሆን የማይፈልግ ሰው የለም፡፡ በተለይ ደግሞ በጋብቻው ስኬታማ መሆን የማይፈልግ ጤነኛ ሰው በአለም ላይ
አይገኝም፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ያስቀመጠውን ሙሉ በረከት ተጠቃሚ የምንሆነው የእግዚአብሄርን የትዳር አላማ ከእግዚአብሔርን
ቃል ስንረዳ ብቻ ነው፡፡
ታዲያ
ከጋብቻ ቁልፍ መርሆዎች አንዱ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ የሚለው ትእዛዝ ነው፡፡
ዳሩ
ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29
ወንድ የትዳር አጋሩን ሲመርጥ ካለ እርስዋ መኖር
አልችልም የሚላትን ሴት ለትዳር ከመረጠ የትዳር አላማውን መሳቱ ብቻ ሳይሆን ትልቅ ችግር ውስጥ ይወድቃል፡፡
ሰው ካገባም በኋላ ሚስቱን ካጣ ህይወቱ እንደሚጠፋ
አድረጎ ፈርቶ ብቻ በትዳር ከኖረ እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ያዘጋጀውን እውነተኛውን በረከት በሙላት መካፈል አይችልም፡፡
በሚቀጥሉት ተከታታይ ትምህርቶች ከዚህ መፅሃፍ
ቅዱሳዊ መርህ አንፃር እግዚአብሄር የትዳር አጋራችንን እንዴት እንደምንመርጥ እና በቀጣይነት ከትዳር አጋራችን ጋር እንዴት እንደምንኖር
እንመለከታለን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
#ያገባ #ያላገባ #አላፊ
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሚስት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ባል #እምነት
#ወንድ #ፍቅር
#ትዳር #ሰላም
#ሴት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ