Popular Posts

Wednesday, April 21, 2021

የልጅነት ስልጣን ክፍል ሁለት


\ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 112

እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። የሉቃስ ወንጌል 1018-19

ክርስቶስ ኢየሱስን አንደ አዳኝና ጌታችን የተቀበልን ሁላችን ከጨለማው ግዛት ድነን ወደፍቅሩ ልጅ መንግስት ተሻግረናል፡፡

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 113-14

ሰይጣን ደግሞ እንደገና በባርነት ውስጥ ሊከተን ይጥራል፡፡ በሰይጣን ጥቃት ውስጥ ላለመውደቅ ሰይጣንን አጥብቀን መቃወም ይኖርብናል፡፡

መስረቅ ማረድና ማጥፋት ብቸኛው የሆነው ሰይጣን ዲያቢሎስን በልጅነት ስልጣናችን በቀጣይነት ልንቃወመው ይገባል፡፡

የልጅነት ስልጣናችንን ተጠቅመን ከእኛና እግዚአብሄር የእኛ ከሆኑት ነገሮች ሁሉ ላይ ካልተቃወምነው እርሱ ራሱ አውቆ ይሄዳል ብለን መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡

በህይወታችን ለእግዚአብሄር በመገዛት ዲያቢሎስን ከህይወታችን ከአገልግሎታችን ሁሉ መቃወም ግድ ይላል፡፡

እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ የያዕቆብ መልእክት 4፡7

ሰይጣን በክርስቶስ የመስቀል ላይ ስራ የተሸነፈ ጠላት በመሆኑ በሚገባ ስንቃወምው መሸሽ አንጂ ሌላ ምንም እድል የለውም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ስልጣን #ስልጣን #መቀመጥ #ሰማያዊ #በክርስቶስ #በጌታ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment