የልጅነት ስልጣን ክፍል አንድ
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12
እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። የሉቃስ ወንጌል 10፡18-19
የሰው ልጅ በእግዚአብሄር መልክና አምሳል የተፈጠረው እንዲገዛ ነበር፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26
ሰው ይገዛ የነበረው ለእግዚአብሄር በመገዛት ስለነበረ ሰው ለእግዚአብሄር መገዛት ሲያቆም እና በሃጢያት በእግዚአብሄር ላይ ሲያምፅ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረውን የልጅነት የመግዛት ስልጣኑን አጣው፡፡
ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ስለተለያየ በሃጢያት በሚመላለስበት ጊዜ ሁሉ በሰይጣን ስልጣን ስር ወደቀ፡፡ በዚህ ምክኒያት ሰይጣን በእግዚአብሄር ላይ ባመፁ ልጆች ሁሉ ላይ ስልጣን ነበረው፡፡
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡1-2
የጠላት ዲያቢሎስ ስራ ደግሞ መስረቅ ማረድና ማጥፋት ብቻ ነው፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
ክርስቶስ ኢየሱስ ደግሞ ወደምድር የመጣው የዲያቢሎስን ስራ ለማፍረስ ነው፡፡
ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡9
ክርስቶስ ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ላይ አሸንፎታል፡፡
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡15
ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ላይ ያሸነፈው ለራሱ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ላይ ያሸነፈው እኛን ወክሎ በእኛ ፋንታ ለእኛ ነው፡፡
ክርስቶስ ኢየሱስን የተቀበልን ሁላችንን ከሰይጣን ስልጣን ድነናል፡፡
እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡13-14
ኢየሱስ ክርስቶስን እንደአዳኙና ጌታው የተቀበለ ሰው ሁሉ የእግዚአብሄር ልጅነት ስልጣን አለው፡፡ ከእግዚአብሄር የተወለደ ሁሉ አለምን የሚያሸንፍበት ስልጣንን ተቀብሎዋል፡፡
እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። የሉቃስ ወንጌል 10፡18-19
እግዚአብሄር በጠላት ምድር ላይ ክርስቶስን እንድንከተል እና በምድር ላይ እንድናገለግለው ሲያዘን ካለስልጣን አይደለም፡፡ የምንኖረው ሰይጣን አስኮናኞች ኑሩ ብሎ ስለፈቀደልን አይደለም፡፡ የምንኖረው በሰይጣን ችሮታና ምህረት አይደለም፡፡ ሰይጣን ወደደም ጠላም የምንንኖረው በስልጣን ነው፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ስልጣን #ስልጣን #መቀመጥ #ሰማያዊ #በክርስቶስ #በጌታ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment