Dibora Getachew
Published on 28 Mar 2021
ውዴ ሆይ ተመስገን እላለው
ውዴ ሆይ ተባረክ እላለው x2
ሁልጊዜ ፊትህን እያየው
ንጉስ በውበትህ ውዴ ውዴ እያልህ
ዙፋንህን ጥለህ መንደሬ ተገኘህ
በቤቴ ዝማሬ ብዙ እልልታ ሆነ
የደስታዎች አውራ ኢየሱስ ስላለ
መአዛዬን ቀየርክ ህይወቴን ባረከው
እንደ መልካም እርሻ ውበትን ሰጠኸው
ወደ ህልውናህ እኔን ስታስገባኝ
ከሰማይ ጠል ጠጣሁ ከምድር ስብ ጠገብኩ
ለኔ ያለህ ፍቅር እጅግ ግድ ብሎህ
ተራሮችን ዘለህ በሬን ታንኳኳለህ x 2
በቃ ልሂድ ሳትል ከኔ ጋር ታድራለህ
ውዴ ሆይ ተመስገን እላለው
ውዴ ሆይ ተባረክ እላለው x2
ሁልጊዜ ፊትህን እያየው
በአለት ንቃቃት እጅህን ሰደድክልኝ
ወደ ፊትህ ብርሀን ስበህ አወጣኸኝ
ቃልን ሳትናገር ውዴ ፍቅርህ ይሰማል
ምድር አስረስቶ ሰማይ ሰማይ ይላል
ለኔ ያለህ ፍቅር እጅግ ግድ ብሎህ
ተራሮችን ዘለህ በሬን ታንኳኳለህ x 2
በቃ ልሂድ ሳትል ከኔ ጋር ታድራለህ
ውዴ ሆይ ተመስገን እላለው
ውዴ ሆይ ተባረክ እላለው x2
ሁልጊዜ ፊትህን እያየው
No comments:
Post a Comment