Popular Posts

Friday, January 22, 2021

የመተው ባለጠግነት

 

እግዚአብሄር የመርህ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንድንይዘው የሚፈልገው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሄር እንዳንይዘው እንድንለቀው የሚፈልገው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሄር እንድንለቀው የሚፈልግውን ነገር ብንይዝ እኛ እንጎዳለን፡፡

ሰው አንዴ የያዘውን እግዚአብሄር ቢያሳየውም ለመልቀቅ የሚያመነታው አንድ ጊዜ ሰርቶለት ስለሚያውቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር በፈጠራ የተሞላ አምላከ ነው፡፡ እግዚአብሄር አንድ መንገድ ብቻ የለውም፡፡ እግዚአብሄር በአንድ አሰራር ብቻ አይወስንም፡፡

ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡10

ሰው አንዴ የያዘውን ነገር መልቀቅ የማይፈልገው አጣለሁ ይጎድልብኛል ብሎ ስለሚፈራ ነው፡፡

አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ። ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። የሉቃስ ወንጌል 6፡37-38

እግዚአብሄር በሰው ላይ የያዝነውን ቂም እንድንተው ሊፈልግ ይችእላል፡፡ እግዚአብሄር ያበደርነውን እንድንተው ሊነግረን ይችላል፡፡ እግዚአብሄር ክስን እንድንተው ሊጠይቀን ይችላል፡፡ እግዚአብሄር የማይፈልገውን ልምምድ እንዳናደርግ ሊያዝዘን ይችላል፡፡

በምንም መልኩ ይሁን መተው ያለብንን አለመተው እግዚአብሄር ካሰበልን ከሚበልጠው ነገር ያጎድለናል፡፡

መተው ያለብንን ነገር አለመተው እግዚአብሄር ወዳሰበልን ወደሚቀጥለው የህይወት ደረጃ እንዳንሻገር ያቆመናል፡፡

መተው ያለብንን ነገር እንደመተው ያለ ባለጠግነት ደግሞ ከሰማይ በታች የለም፡፡

አግዚአብሄር ተው ይበለን እንጂ ለመተው ዛሬውኑ መወሰን አለብን፡፡

የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። ወደ ዕብራውያን 10፡34

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/AbiyWakumaDinsa/notes

Abiy Wakuma Dinsa አቢይ ዋቁማ ዲንሳ

#አዲስፍጥረት #አዲስ #መዋጀት  #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #መልቀቅ #አቁማዳ #መተው #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ጌታ #ማሪያም #መላእክት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ሰላም ትግስት #ልጅ


Wednesday, January 13, 2021

አቢይ የጥሞና ቃል #ሰባት የእግዚአብሔር መንግሥት ደስታ

 

አቢይ የጥሞና ቃል #ሰባት የእግዚአብሔር መንግሥት ደስታ

የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1417

የእግዚአብሄር መንግስት ሁለንተናዋ ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ነው፡፡ 

የእግዚአብሄር መንግስት አንዱ ውበትዋ በመንፈስ ቅዱስምሆነ ደስታ ነው፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት የመኖር አንዱ እድል ደስታ በሌለበት አለም ደስታን ማግኘት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት አንዱ ጥቅም በሁኔታዎች ያልተደገፈ ደስተኝነት ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት መልክ ከምንም ነገር ጋር ባልተያያዘ መልኩ በጌታ ደስ መሰኘት ነው፡፡

ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡4

አለም በሚያሳዝን ነገር በተሞላች አለም ውስጥ ሃይላችንን የሚመጣው ከእግዚአብሄር ደስታ ብቻ ነው፡፡

እርሱም፦ ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው። መጽሐፈ ነህምያ 8፡10

እግዚአብሄር ሆይ በልጅህ በክርስቶስ በኩል ስለሰጠኽኝ ደስታ አመሰግናለሁ፡፡ የደስታዬ ምንጭ አንተ ብቻ ስለሆንክ ደስታዬ በምንም ነገር ስለማይለዋወጥ አመሰግናለሁ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!

#አቢይጥሞና #ሐዋርያውአቢይ #ሐዋርያጥሞና


Tuesday, January 12, 2021

አቢይ የጥሞና ቃል #ስድስት የእግዚአብሔር መንግሥት ሰላም

 

አቢይ የጥሞና ቃል #ስድስት የእግዚአብሔር መንግሥት ሰላም

የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡17

እግዚአብሄር ንጉስዋ የሆነላትና በመንፈስ በምድር ላይ የምትገዛው የእግዚአብሄር መንግስት ሁለንተናዋ ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ነው፡፡  

ከጽድቅና ከሰላም በመንፈስ ቅዱስም ከሆነ ደስታ አንፃር ውጭ የእግዚአብሄር መንግስት   ልትታይም ሆነ ልትለካ አትችልም፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ሃላፊነትዋም ጥቅምዋም ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ዜጎችዋን የምትባርክው በፅድቅ እና በሰላም ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ረብሻ በሞላበት አለም ለዜጎችዋ ልዩ የሆነ አእምሮን የሚያልፍ ሰላምን በመስጠት ትታወቃለች፡፡

በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ። የዮሐንስ ወንጌል 16፡33

አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡7

በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ የሚኖር ሰው ብዙ የሚታይ ነገር ላይኖረው ይችላል ነገር ግን ሰላም የእርሱ ነው፡፡ ለእግዚአብሄር መንግስት የሚገዛ ሰው በመከራ ሊያልፍ ይችላል ነገር ግን ሁለንተናውን አእምሮ የሚያልፍ ሰላም ግን ይቆጣጠረዋል፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ሰዎች በመጀመሪያ ከፈጠራቸው ከእግዚአብሄር ጋር ጥለኛ አይደሉም በክርስቶስ ኢየሱስ መስቀል ታርቀዋል ሰላም ናቸው፡፡

ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን 

Monday, January 11, 2021

አቢይ የጥሞና ቃል #አምስት የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅ

 


አቢይ የጥሞና ቃል #አምስት የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅ

የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1417

ኢየሱስ ክርስቶስን አንደ አዳኛችን ተቀብለን የምንኖርባት ፣ እግዚአብሄር ንጉስዋ የሆነላትና በአይን የማትታየው የእግዚአብሄር መንግስት በጽድቅና በሰላም ብሎም በመንፈስ ቅዱስም በሆነ ደስታ ላይ ብቻ የተመሰረተች ናት፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ከእነዚህ ከጽድቅና ከሰላም በመንፈስ ቅዱስም ከሆነ ደስታ ውጭ ልትመሰረተም ፣ ልትታይም ብሎም ልትለካም አትችልም፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ሃላፊነትዋም ጥቅምዋም ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ዜጎችዋን የምትባርክው በፅድቅ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የምትታወቀው በራሳቸው ጽድቅ የሌላቸውን ሃጢያተኛ ሰዎች ስለእነርሱ በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ፅድቅ ማፅደቅ ነው፡፡

እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 521

የእግዚአብሄር መንግስት ስለ ፅድቅ ትኖራለች፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ስለ ፅድቅ ትቆማለች፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የምትኖረውም የምትቆመውም የምትሰራውም ስለፅድቅ ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ካለ ፍርሃትና ካለ በታችነት ስሜት በእግዚአብሄር ፊት የመቆም የልጅነት መብት ነው፡፡

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ወደ ዕብራውያን 416

የእግዚአብሄር ፅድቅ የእግዚአብሄር ልጅነት መብት ነው፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12

የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ፊት ትክክል ሆኖ የመገኘት ሃላፊነት ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት መንግስቱን እና ፅድቁን የማስቀደም ሃላፊነት ነው፡፡  

እግዚአብሄር ሆይ በልጅህ በክርስቶስ በኩል ስለሰጠኽኝ የክርስቶስ ፅድቅ አመሰግንሃለሁ፡፡ በክርስቶስ እንደተወደደ ልጅ  በፊትህ እመላለሳለሁ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!

#አቢይጥሞና #ሐዋርያውአቢይ #ሐዋርያጥሞና

Tuesday, January 5, 2021

መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡1-10 ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች፦ ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል። እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም። አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል። ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና። ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።


መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡1-10

ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች፦ ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል።

እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።

 አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።

የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል።

ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች።

እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።

እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።

ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ።

 እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና።

ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።