Popular Posts

Tuesday, September 19, 2017

ሰበብ የለም

ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡6-10
እግዚአብሄር ሰውን ያውቀዋል፡፡ እግዚአብሄር የሃጢያትን እዳ ሁሉ በኢየሱስ ከከፈለ በኋላ ሰው ግን ላለመዳን ምክኒያት እንደሚፈልግ ያውቀዋል፡፡ ሰው ቀላል የሆነውን ነገር እንዴት እንደሚያወሳሰብና የማይቻል እንደሚያደርገው እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ስለዚህ ነው እንዲህ ተብሎ የተፃፈው፡፡  
በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል ሮሜ 10፡6-7
ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ ፣ ከዘላለም ፍርድ መዳን ፣ የዘላለም ህይወት ማግኘት ከባድ አይደለም፡፡ መዳን የአመታት ስራ አይጠይቅም፡፡ መዳን የአመታት ጥረት ፣ ትጋትና ጉስቁልና አይጠይቅም፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሃጢያት እዳችንን ሁሉ ስለከፈለ ለመዳን የሚጠበቅብን ነገር የደህንትን ነፃ ስጦታ በእምነት መቀበል ብቻ ነው፡፡
የቃሉ ማስጠንቀቂያ እነዲህ ይላል መዳን እንደ ሰማይ የራቀ ነው አትበል፡፡ እንዲሁም መዳን እንደ ጥልቅ ሩቅ ነውም አትበል፡፡ ለመዳን ሰበብ አይኑርህ፡፡ ላለመዳን የምታቀርበው ማንኛውም ምክኒያት በቂ አይደለም፡፡ ላለመዳን የምታቀርበው የቱም ምክኒያት ሰንካላ ምክኒያት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር በክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ ፈፅሞ ከከፈለ በኋላ ላለመዳን ለምናቀርበው ማንኛውም ምክኒያት ጆሮ የለውም፡፡  
እግዚአብሄር መዳንን እጅግ አቅርቦታል፡፡ ለመዳን እጅግ ዋጋ ቢከፈለምና መዳን እጅግ የላቀ ዋጋ ያለው ቢሆንም እግዚአብሄር ለእኛ ግን መዳንን ቀላል አድርጎታል፡፡
በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ሮሜ 10፡8
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ኢየሱስን እንደአዳኝና ጌታ አሁኑኑ መቀበል ከፈለጉ ይህን ፀሎት አብረው ይፀልዩ
እግዚአብሄር ሆይ በልጅህ በኢየሱስ የሃጢያቴን እዳ ሁሉ ስለከፈለክ አመሰግንሃለሁ፡፡ ስለሰጠኸኝ የደህነት ነፃ ስጦታ አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ እግዚአብሄር ከሙታን እንዳስነሳው በልቤ አምናለሁ፡፡ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #ነፃስጦታ #ፀጋ #ሞት #የዘላለምህይወት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ብትመሰክር #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ብታምን #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Monday, September 18, 2017

ሰዎች ለምን መዳን አይፈልጉም ?

ብዙ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ስለሃጢያታቸው በመስቀል ላይ የከፈለላቸውን ዋጋ ለእኔ ነው በማለት ጌታን ለመከተል ይወስናሉ፡፡ እግዚአብሔርም በኢየሱስ ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ ስለተቀበሉ ልጆች አድርጎ ወደ ቤተሰቡ ይቀበላቸዋል፡፡
አንዳንድ ሰዎች ግን ቢያንስ ቢያንስ እስካሁን ኢየሱስን አልተቀበሉም፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ተቀብለው የማይድኑበትን ምክኒያቶች እንመልከት፡-
1.      ሰዎች የደህንነት ነፃ ስጦታነት ስለማይረዱት ነው፡፡
እግዚአብሄር በነፃ ሊያድናችሁ ይፈልጋል ሲባሉ በጣም የተጋነነ ከእውነት የራቀ አባባል ይመስላቸዋል፡፡ ስለዚህ ነፃውን ስጦታ ከመቀበል ይልቅ በራሳቸው ስለሃጢያታቸው ዋጋን ለመክፈል መልካምን ለማድረግ በዚያም ደህንነትን ለማግኘት ይጥራሉ፡፡ ሃጢያተኛ ሰው በቅዱሱ በእግዚአብሄ ፊት መልካምን ነገር በማድረግ ስለሃጢያቱ ዋጋን ሊከፍል አይችልም፡፡ ሰዎች ግን በራሳቸው ለሃጢያታቸው ዋጋ ለመክፈል ከፈለጉ ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለያየት ነው የሚከፍሉት፡፡ ስለሃጢያት ሊከፍል የሚችለው ሰው ሃጢያት ያልሰራ ብቻ ነው፡፡ ሃጢያት የሌለበት ኢየሱስ ስለሃጢያታችን ፈፅሞ ከፍሎዋል፡፡ እኛ መክፈል አንችልምም አይገባንምም፡፡ እኛ ማድርግ የሚገባን በእምነት ይህንን ስጦታ መቀበል ብቻ ነው፡፡
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌሶን 2፡8-9
2.     አንዳንድ ሰዎች የደህንነትን መልእክት የማይቀበሉት ለደህንነት የሃይማኖት ስርአትን መፈፀም የሚበቃ ስለሚመስላቸው ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሄር በክርስቶስ ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ የማይቀበሉት የአንድ ሃይማኖት ተከታይ መሆን የሚያድን ስለሚመስላቸው ነው፡፡ እውነተኛ ሃይማኖት ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለውን የሃጢያት መስዋእትነት የሚሰብክ ነው፡፡ ያንን እግዚአብሄር ያዘጋጀውን ብቸኛ የመዳኛ መንገድ መቀበል እንጂ የሃይማኖት ስርአትን መፈፀም ብቻ ማንንም ሊያድን አይችልም፡፡ የሃይማኖትን ስርአት መፈፀም የሚያድን ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ ወደ ሃይማኖተኞች መጥቶ ስለ ዳግመኛ መወለድ አይሰብክላቸውም ነበር፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ዮሃንስ 3፡3
በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ ያለን ሰው ኢየሱስ ካላዳነው የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ መሆኑ በራሱ አያድነውም፡፡ የኢየሱስን አዳኝነት ከመቀበል ውጭ የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይነት ለመዳን በቂ አይደለም፡፡ 
3.     አንዳንድ ሰዎች መዳን የማይፈልጉት ሃጢያትን ስለሚወዱ ነው፡፡
ሰዎች ኢየሱስን መከተል የማይፈልጉት ሃጢያትን ስለሚወዱ ነው፡፡ በሃጢያት የሚገኝ ጊዜያዊ ደስታ የዘላለም ህይወትን ያሳጣቸዋል፡፡ በሃጢያት ስለሚገኝ ደስታ በጌታ ኢየሱስ የሚገኘውን ሰላምና እረፍት ይለውጡታል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን እንዲቀበሉ ሲነገራቸው ብዙ ምክኒያት የሚዘረዝሩት በጨለማ ስለሚመላለሱና ወደብርሃን መውጣት ስለማይፈልጉ ነው፡፡
ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ ዮሃንስ 3፡19-20
4.     አንዳንድ ሰዎች መዳን የማይፈልጉት በመልካም ባህሪያቸው ስለሚመኩ ነው
አንዳንድ ሰዎች የደህንነትን መልእክት የማይቀበሉት ደህንነት የባህሪ ለውጥ ስለሚመስላቸው ነው፡፡ "እኔ በተቻለ ህሊናዬን ጠብቄ እኖራለሁ ስለዚህ ምንም አያስፈልገኝም" ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ደህንነት የባህሪ ለውጥ ሳይሆን የመጥፋትና የመዳን ጉዳይ ነው፡፡ ደህንነት ጥሩ ሰው የመሆን ጉዳይ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ለዘላለም መለያየትና ከእግዚአብሄር ጋር   የመታረቅ ጉዳይ ነው፡፡ ደህነንነት የመልካም ስነምግባር ጥሪ ሳይሆን የሞትና የህይወት ምርጫ ጥሪ ነው፡፡
ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። 1ኛ ዮሃንስ 5፡12
ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ሮሜ 5፡10
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36
5.     አንዳንድ ሰዎች መዳን የማይፈልጉት በቂ ጊዜ ያላቸው ስለሚመስላቸው ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች መዳን በኢየሱስ ብቻ እንዳለ ያምናሉ ነገር ግን በሌሎች ነገሮች በጣም ባተሌ ከመሆናቸው የተነሳ የደህንነታቸውን ነገር ሁሌ ለሌላ ጊዜ ያስተላልፉታል፡፡ አፍላ ህይወታቸውን ለጌታ መስጠት ይሳሳሉ፡፡ ህይወትን ለጌታ ከመስጠት በላይ አስፈላጊ ነገር እንዳለ ያስባሉ፡፡ ለእግዚአብሄር የህይወታቸውን ጭላጭ ሊሰጡት ይቀጥራሉ፡፡
ሌላውንም፦ ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ አለ። ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው። ደግሞ ሌላው፦ ጌታ ሆይ፥ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን አስቀድሜ ከቤቴ ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ አለ። ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው። ሉቃስ 9፡59-62
በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡2
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ፀሎት
አሁን ኢየሱስን ለመቀበል ከወሰንክ ይህንን ፀሎት ከልብህ ወደ እግዚአብሔር ፀልይ
እግዚአብሄር ሆይ የመዳንን እውቀት ስለላክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፡፡ በሃጢያቴ ካንተ እንደተለሁ አውቃለሁ፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያቴን ዋጋ ሁሉ እንደከፈለ አውቄያለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ ልጅህ አድርገህ ወደ ቤተሰብህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Sunday, September 17, 2017

የደህንነት ነፃ ስጦታ

ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ተለያይቶዋል፡፡ ሰው በሃጢያቱ ሙት ሆኖዋል፡፡ ሰው ከዚህ ሞት መዳን አለበት፡፡ ሰው ካልዳነ በስተቀር ለዘላለም ከእግዚአብሄር ይላያያል፡፡
ደህንነት ደሞ ነፃ ስጦታ ነው፡፡ ደህንነት እጅግ ውድ ከመሆኑ የተነሳ ደህንነትን በምንም ነገር ሊገዙት አይችሉም፡፡  
ሰው በሃጢያት የተነሳ በእግዚአብሄር ዘንድ ሙት በመሆኑና ከእግዚአብሔር ጋር ጠላት በመሆኑ በህይወት ዘመኑ ሁሉ መልካምን ስራ ቢሰራ መልካም ስራው ደህንነትን ሊገዛለት አይችልም፡፡
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌሶን 2፡8-9
መልካ ስራ ደህንትን ቢያስገኝልን ኖሮ ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት አያስፈልገውም ነበር፡፡
መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ቲቶ 2፡14
ሰው በአለም ላይ ያለውን ገንዘብ ሁሉ ቢያፈስ የአንድ ሰውን ደህንነትን ለመግዛት አይበቃም፡፡ ደህንነት እንዳውም በገንዘብ ሊተመን የማይችል እጅግ ውድ ነገር ነው፡፡  
ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማርቆስ 8፡36-37
ከጥፋተ መዳን የምንችለው ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያታችን ያደረገው መስዋእትነት ለእኔ ነው ብለን በእምነት በመቀበል ብቻ ነው፡፡  
ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።1ኛ ጴጥሮስ 1፡18-19
ሰው ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት የከፈለለትን የሃጢያት እዳ ክፍያ በእምነት ባይቀበል ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለያየት ይከፍለዋል፡፡ ሰው እግዚአብሄ በክርስቶስ የሰጠውን ነፃ ስጦታ ቸል ቢል ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለያየት ይጠፋል፡፡
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16
እግዚአብሔር ሆይ ስለላክልኝ ስለደህነነት ቃል አመሰግንሃለሁ፡፡ ልጅህ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ ሊሰቀል ወደምድር ስለመጣ  ስለሞተልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ተለይቶ በሶስተኛው ቀን እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአደፌ እመሰክራለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Saturday, September 16, 2017

መልካም ስራን መስራት ለመዳን ለምን አይጠቅምም?

ብዙ ሰዎች ለመዳን በመልካም ስራቸው ላይ ይደገፋሉ፡፡ መዳንን ሲያስቡ መልካም ስራዬ ያድነኝ ይሆንን ብለው ስለመልካም ስራቸው ጥንካሬ ይጨነቃሉ፡፡ መልካም ስራ መስራት እንደማያድን እና ሰው ለመዳን መልካም ስራ እንደሚያስፈገው ከእግዚአብሄር ቃል እንመልከት፡፡
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከሰው ጋር ህብረት ማድረግ እንዲችል ሰውን በመልኩ ፈጠረው፡፡ ሰው የተፈጠረው ወደ እግዚአብሄር ቤተሰብ ውስጥ ነበር ፡፡
እግዚአብሄር ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንዲኖር አስቦ ነው ሰውን የፈጠረው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንዲኖር ፣ ከእርሱ ጋር ህብረት እንዲያደርግና እንዲታዘዘው ነበር፡፡ ለዚህም ነው እግዚአብሄር ሰውን እንዲታዘዘው ያዘዘው በእርሱ ላይ ባመፀ ጊዜ እንደሚሞት ያስጠነቀቀው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ባልታዘዘ በዚያው ቅፅበት ሞተ፡፡ ሰው የተፈጠረበትን አላማ ሳተ፡፡ ሰው በአመፁ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው የአባትና የልጅነት ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ተቆራረጠ፡፡ ሰው በራሱ ሆነ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ጠላት ሆነ፡፡
ስለዚህ ምክኒያት ምንም አይነት ለመዳን ወይም ለመጽደቅ የሚደረግ መልካም ስራ ሊያፀድቅ የማይችልበትን ምክኒያቶች እንመልከት፡፡
1.      ሰው ከእግዚአብሄር ክብር ወድቆዋል
በእግዚአብሄር መልክና አምሳል በእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሮ ነበር፡፡
እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ዘፍጥረት 2፡27
ሰው ሃጢያትን ሲሰራ ከለእግዚአብሄር ክብር ወድቆዋል፡፡ ሰው ሃጢያትን ሲሰራ የእግዚአብሄን መልክ አጥቶታል፡፡ ሰው ሃጢያት በመሰራቱ ከእግዚአብሄር ክብር ጎድሎዋል፡፡
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ 3፡23
ሰው ሃጢያት ሲሰራ ከእግዚአብሄ ክብርት ደረጃ ወደ ሳርነትና አባባነት ደረጃ ተዋርዶዋል፡፡ እግዚአብሄር በክብሩ የፈጠረው ሰው ከወደቀ በኋላ በሳርነትና በአበባነት ክብር የሚሰራው ስራ እግዚአብሄርን አያስደስተውም፡፡ እግዚአብሄር የአመፀኛ ምንም አይነት ስራ አያስደስተውም፡፡
ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡24
2.     ሰው ሃጢያት ሲሰራ ከእግዚአብሄር ቤተሰብ አባልነት ወጥቶዋል፡፡ 
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ለህብረት ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በመጀመሪያ የፈጠረው ለህብረት እንጂ ለስራ አይደለም፡፡ ሰው ወደ እግዚአብሄ ቤተሰብ ውስጥ ተፈጥሮዋል፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ወንድና ሴት ልጅ እንዲሆን ተፈጥሮዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ግንኘኙነት እንዲኖረው ተፈጥሮዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው የአባትና የልጅ ግንኙነት ሲቋረጥ ሰው አጣ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው ግንኙነት በሃጢያት ምክኒያት ሲቋረጥ ሰው እግዚአብሄርን የሚመስልበትን ባህሪ አጣው፡፡ እግዚአብሄር ያለመውን ህብረትና ግንኙነት ከሰው ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ሳይሆን ሰይጣንን በመስማቱ መልካም ባህሪ አጥቶ የሰይጣንን ባህሪ ተካፈለ፡፡
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44
ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን የልጅነት ግንኙነት ያቋረጠውና የእግዚአብሄን ባህሪ ያጣው ሰው  በመልካም ስራ እግዚአብሄርን ሊያስደስተው አይችልም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ስራውን ሳይሆን ግንኙነቱና የራሱን ባህሪ በሰው ውስጥ ማየቱን ነው፡፡ ግንኙነቱንና ህብረቱን አቋርጦ ባህሪውን ጥሎ ስራውን ልስራ የሚል ሰው እግዚአብሄርን አይማርከውም፡፡ 
3.     ሰው አላማውን ስቶዋል፡፡
ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን እየሰማና እየታዘዘ እንዲኖር ነው፡፡ ሰው ሃጢያት ሲሰራ የተፈጠረበትን አላማውን ሁሉ ስቶዋል፡፡ ሰው የተፈጠረው መልካም በሚላቸው ነገሮች እግዚአብሄርን እንዲያስደስት አይደለም፡፡ ሰው የተሰራው ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት በማድረግ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር እንዲያደርግ ነው፡፡ ስለዚህ የተፈጠረበትን የህብረት አላማ የሳተ ሰው በራሱ አነሳሽነት ነገሮችን በማድረግ እግዚአብሄርን ሊያስደስተው አይችልም፡፡
በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም። ሮሜ 8፡8
4.     ሰው በሃጢያቱ ምክኒያት ሞቶዋል፡፡
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ዘንድ ህያው ሆኖ ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት እያደረገ ለዘላለም እንዲኖር ነው፡፡ ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው የአባትነትና የልጅነት ግንኙነት ሲቋረጥ ሞተ፡፡ ንስሃ ያልገባና ኢየሱስን ያልተቀበለ በሃጢያት የሚኖር ሰው በእግዚአብሄር አይን ሙት ነው፡፡ ኢየሱስን የማይከተል ሰው ሰው ለእግዚአብሄር ህያው አይደለም፡፡ ሃጢያተኛ ሰው ይበላል ይጠጣል ይንቀሳቀሳል በእግዚአብሄር አይን ግን ሙት ነው፡፡ የሰው መንፈሱ ሞቶዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኝበት የመንፈስ ክፍሉ ሞቶዋል፡፡ የሞተ ወይም የተለየ ሰው ማንንም ማስደሰት እንደማይችል ሁሉ ሃጢያተኛ ሰው እግዚአብሄርን በመልካም ስራ በፅድቁ ሊያስደስተው አይችልም፡፡
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን  2፡1-2
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። ኢሳያስ 64፡6
5.      ሰው በሰይጣን ግዛት ውስጥ ውድቆዋል
ሰው እግዚአብሄርን እንቢ ሲል ሰይጣንን እሺ ብሎዋል፡፡ ሰው ለፈጠረው ለእግዚአብሄር ካልተገዛ ለሰይጣን ይገዛል፡፡ ሰው ወይ የኢየሱስ ተከታይ ይሆናል ወይም የሰይጣን ተከታይ ይሆናል፡፡ ከሁለቱም መካከል ነኝ የሚል ሰው የለም፡፡ ሰው በንስሃ ኢየሱስን ካልተቀበለ በሰይጣን ግዛት ውስጥ እያለ ኢየሱስን ሊያገለግል መልካምን ስራ ሊሰራ አይችልም፡፡  ሰው መልካምን ለመስራት መጀመሪያ ከተያዘበት ከዲያቢሎስ ግዛት ነፃ መውጣት አለበት፡፡
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን  2፡1-2
እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ቆላስይስ 1፡13-14
6.     ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ጠላት ሆኖዋል፡፡
ሰው እግዚአብሄር አታድርግ ያለውን በማድረጉ በእግዚአብሄር ላይ አምፆአል፡፡ ስለዚህ አመፀኛ የሆነ ሰው ላመፀበት መልካምን ነገር ከማድረጉ በፊት ከአመፁ ንስሃ መግባት አለበት፡፡ ከአመፁ ንስሃ ሳይገባና ሳይመለስ ከእግዚአብሄር ጋር ሳይታረቅ በጠላትነት የሚያደርገው መልካም ስራ ሁሉ ለመዳን በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ሰው መልካመነ ስራ ከመስራቱ በፊት መታረቅ ግዴታ ነው፡፡
ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ሮሜ 5፡10
መልካምን ስራ መስራት ምንም ጉዳት የለውን ለመፅደቅ ወይም ለመዳን ግን አይጠቅምም፡፡ ሰው የሚድነው ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራለትን ስራ ለእኔ ነው ብሎ በእምነት ሲቀበል ነው፡፡ መልካምን ስራ ለመስራት ከሞተ ስራ ንስሃ መግባትና እንደገና መመለድ ይጠይቃል፡፡ ኢየሱስን የተቀበለ ሰው ሁሉ መልካምን መስራት አለበት፡፡ ነገር ግን መልካምን የሚሰራው ለመዳን ሳይሆን ስለዳነ ነው፡፡
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የእግዚአብሔር ፍጥረት ወይስ የእግዚአብሔር ልጅ?

ሰውን ሁሉ የፈጠረው እግዚአብሔር ነው፡፡ ሰውን እግዚአብሔር የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው ሰው የእግዚአብሔር የቤተሰቡ አባል እንዲሆንና ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንዲኖረው ነው፡፡ ሰው ከእርሱ ጋር ለዘላለም በአባትና በልጅ ግንኙነት እንዲኖር ስለፈለገ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጠረው፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዳይበላሽ ስለፈለገ ሰውን ካልተፈቀደለት ፍሬ እንዳይበላና እንዳይሞት አዘዘው፡፡
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍጥረት 2፡16-17
ሰው ግን በሰይጣን አማካኝነት አትብላ የተባለውን ፍሬ በላ፡፡ ሰው በበላም ቀን ሞተ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው የአባትነትና የልጅነት ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ ሰው በመንፈሱ ከእግዚአብሔር ተለየ ሞተም፡፡  
ሰውን ሁሉ የፈጠረው እግዚአብሔር እንጂ ሰይጣን የፈጠረው ሰው የለም፡፡ ሰይጣን ሰውን አሳመፀ፡፡ ያመፀውም የሰው ልጅ እንኳን የእግዚአብሔር ፍጥረት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ፍጥረት መሆን ማለት ግን የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ማለት አይደለም፡፡ በምድር ላይ የምታዩት ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ፍጥረት ነው፡፡ በምድር ላይ የምታዩት ሰው ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጅ ላይሆን ይችላል፡፡
የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን መመዘኛ አለው፡፡ መመዘኛው ስራ አይደለም፡፡ መመዘኛው እምነት ብቻ ነው፡፡ መመዘኛው በእምነት የኢየሱስን የመስቀል ላይ እዳ መክፈል መቀበል ነው፡፡
ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሃጢያት ሁሉ በመስቀል ላይ ስለሞተ የእግዚአብሔር ፍጥረት የሆነ ሰው ሁሉ መመዘኛውን ካሟላ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ይችላል፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን ስለሞተ ብቻ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ አይሆብንም፡፡ ኢየሱስ የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ ስለከፈለ ኢየሱስ የከፈለው ለእኔ ነው ብሎ የኢየሱስን አዳኝነት የተቀበለ ሁሉ እግዚአብሔር ልጅ ይሆናል፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
የእግዚአብሔ ፍጥረት የሆነ ሰው ኢየሱስ ስለሃጢያቱ በመስቀል ላይ የከፈለለትን ለእኔ ነው ብሎ ባይቀበል ግን ለዘላለም ይጠፋል፡፡ ሰው ኢየሱስን ባይቀበል የዘላለም ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36
የእግዚአብሔር ፍጥረት የሆኑ ሁሉ ኢየሱስን እንደ አዳኝና ጌታ አድርጎ በመቀበል ብቻ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ይችላሉ፡፡ እግዚአብሔር ወደ ቤተሰቡ ሊቀበላቸው ይፈልጋል ኢየሱስን ተቀበሉ እንላለን፡፡
የእግዚአብሄር ልጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ ይህን ፀሎት አብሮ ይፀልይ፡፡  
እግዚአብሔር ሆይ ስለላክልኝ ቃል አመሰግንሃለሁ፡፡ ልጅህን ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ ስለተሰቀለልኝና ስለሞተልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ከሙታን እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ እንደሁም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌተ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን ፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Friday, September 15, 2017

የልጅነት መንገድ

እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው የቤተሰቡ አባል እንዲሆንና ከእርሱ ጋር የአባትና የልጅ ህብረት እንዲኖረው ነው ፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ልጁ እንዲሆን ነው፡፡ ሰውን የፈጠረው እግዚአብሔር ለሰው አባቱ ሊሆነው ነው፡፡
እግዚአብሔር ለሰው የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ በአምስት ቀን ውስጥ ሰርቶ በስድስተኛው ቀን ሰውን ፈጠረው፡፡ ሰው በስድስተኛው ቀን የተፈጠረው እንደ ልጅ ከአባቱ ጋር በሰባተኛው ቀን እንዲያርፍ ነው፡፡
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር የቤተሰብ አባልነቱና በልጅነቱ ለዘላለም እንዲኖር ነበር፡፡ ስለዚህ ነው እግዚአብሔር የተከለከለውን እንዳይበላ ሰውን ሲያዘው የምንመለከተው፡፡ እግዚአብሔር ለሰውን ልጅ ሆኖ ለዘላለም የሚኖርበትን መንገድ አሳየው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ሰው ካልታዘዘ ከልጅነቱ እንደሚሻር ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የአባትና የልጅ ግንኙነት እንደሚቋረጥ አስጠነቀቀው፡፡
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍጥረት 2፡16-17
ሰው እግዚአብሔርን ባለመታዘዙ በመንፈሱ ሞተ፡፡ ሰው እግዚአብሔር ላይ በማመፁ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው የአባትነት እና የልጅነት ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ቤት ወጣ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ከአባቱ ጋር ተጣልቶ በመንፈሳዊ አነጋገር ጎዳና ተዳዳሪ ሆነ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር የሚመጡለት የቤተሰብ አባል መብቶችና ጥቅሞች ሁሉ ተቋረጡበት፡፡
ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ተጣላ፡፡ ሰው በእግዚአብሔር ላይ አመፀ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ህልውና ራቀ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ቤተሰብ ተለየ፡፡ ሰው በራሱ ሆነ፡፡ በአዳም ሃጢያት ምክኒያት ሃጢያት በሰው ልጆች ላይ ሁሉ ወደቀ፡፡  
እግዚአብሔር ለዘላለም አብሮት እንዲኖር የፈጠረው ሰው ከእርሱ ለዘላለም እንዲለይና እንዲጠፋ አልወደደም፡፡ ኢየሱስን ወደምድር በመላክ የሃጢያትን እዳ ሁሉ እንዲከፍል አደረገው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን የአባትነትና የልጅ ግንኙነት እንዲቋረጥ ያደረገውን የሃጢያትን እዳ በመስቀል ላይ በመሞት ሙሉ ለሙሉ እንዲከፍል አደረገው፡፡
አሁን የሃጢያት እዳ ሁሉ ተከፍሎዋል፡፡ አሁን እንደገና መታረቅ እንችላለን፡፡ አሁን ወደ ቤተሰቡ መመለስ እንችላለን፡፡
ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡18-19
ኢየሱስን እንደ አዳኛችንና እንደ ህይወታችን ጌታ ከተቀበልነው እግዚአብሔር መልሶ ልጅ አድርጎ ይቀበለናል፡፡  
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። 1ኛ ዮሐንስ 4፡10
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። 1ኛ ዮሐንስ 3፡1
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #አቅርቦት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ጥሪ #ክህንነት #ስራ #መልክተኛ #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Thursday, September 14, 2017

ትንቢት የሚፈተንባቸው ስድስቱ መንገዶች

ትንቢት ፍፁም አይደለም፡፡ ነቢያትም ፍፁም አይደሉም፡፡ ፍፁሙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ግን ሊሳሳት በሚችል ሰው ውስጥ ነው የሚተላለፈው፡፡ እግዚአብሔር ግን ከማይተላለፍ ፍፁም ባልሆነ ሰው ውስጥ ቢተላለፍ ይሻላል ብሎ ነው ነቢያትን የሰጠን፡፡
በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚኖረው በነቢያት በካህናትና በነገስታት ላይ ብቻ ስለነበረ የእግዚአብሔር ህዝብ ቃሉን ከመቀበል ውጭ በውስጡ ባለው መንፈስ ትንቢቱን የሚመዝንበት እድል አልነበረውም፡፡
ሰዎች በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ቃል የሚገኝበት ነቢይ እዚህ ይኖራል? በማለት ችግር ሲገጥማቸው ነቢያትን ይፈልጉ ነበር፡፡
በአዲ ኪዳን ግን መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሁለ ውሰጥ አለ፡፡ እንዲያውም በውስጡ መንፈስ ቅዱስ ከሌላ አማኝ አይደለም፡፡
የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም። ሮሜ 8፡9
ትንቢትን የመፈተን ትልቁ ሃላፊነት ያለው እኛ ጋር ነው፡፡ ነቢይ ስላሳሳተኝ ነው ብለን የምንሰጠው ሰበብ ሊኖር አይችልም፡፡
ነቢይ በጉባኤ ሲናገር ሌሎች ነቢያት የሚናገረውን ነገር እንዲፈትኑት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡
ነቢያትም ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ይናገሩ ሌሎችም ይለዩአቸው፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡29
በጉባኤም ይሁን በግል የተሰጡትን ትንቢቶች መቀበል ወይም አለመቀበል ሃላፊነቱ ያለው አማኙ ጋር ነው፡፡ እኔ ታላቅ ነቢይ ነኝና የምናገረውን ሁሉ ሳትጠራጠረሩ ዋጡ የሚል ነቢይ እኛም አማኞች እያንዳንዳችን እንደ ነቢይ የምንለይበት መንፈስ እንዳለን ማወቅ ይገባዋል፡፡
ትንቢት የሚፈተሽባቸው ስድስት መንገዶች
1.      ትንቢት ከእግዚአብሔር ቃል ጋር መስማማት አለበት፡፡
ትንቢት ከእግዚአብሔር ቃል ከተቃረነ በቃሉ ላይ ከጨመረ ወይም ከቀነሰ ስህተት መሆኑን አውቆ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሰባት ጊዜ የተፈተነ ራሱ የትንቢት ቃል ነው፡፡ እያንዳንዱ ትንቢት ከተፈተነው ከእግዚአብሔር ቃል ካለተስማማ ትንቢቱ ተሳስቷል ያሳስታልም፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አንዱ በአንዱ ላይ አንዳችሁም እንዳይታበዩ፦ ከተጻፈው አትለፍ የሚለውን በእኛ ትማሩ ዘንድ፥ ይህን በእናንተ ምክንያት ስለ ራሴና ስለ አጵሎስ እንደ ምሳሌ ተናገርሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 4፡6
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ 1ኛ ጴጥሮስ 4፡11
2.     ትንቢት ከመንፈሳችን ምሪት ጋር መስማማት አለበት
አንዳንድ ጊዜ ትንቢት ከአጠቃላይ የእግዚአብሔር ምክር ጋር ተስማምቶ ነገር ግን አግዚአብሔር በጊዜው ያልሰጠን ሬማ ቃል አይደለም ይሆናል፡፡ ምንም እንኳን ነቢዩ ከመፅሃፍ ቅዱስ ጠቅሶ ቢተነብይም ለጊዜው እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠን መልእክት መሆኑን ማመረጋገጥ አለብን፡፡ ነቢይ ለግል ህይወታችን የሚናገረው ነገር ጉሉ እግዚአብሔር ለግላችን በመንፈሱ የሚያተረጋገጥልን ካልሆነ አለመቀበል እንችላለን፡፡ እግዚአብንሔርን በልባችን ለግላችን ያልመራንን  ነቢዩ ስለተናገረ ብቻ ለምን አልፈፀሙትም አይለንም፡፡
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ሮሜ 8፡14፣16
እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27
3.     ትንቢት የሰው ፈቃድ መሆን የለበትም
ትንቢት የሚናገረው ከራሱ ፍላጎት ብቻ ከሆነ ትንቢቱ ትክክል አይሆንም፡፡ ትንቢትን የሚናገረው ሰው ከኪሱ አውጥቲ እንደሚሰጥ ከሆነ ትንቢቱ እውነተኛ ላይሆን ይችላል፡፡ ትንቢት በሰው ፈቃድ አይመጣም፡፡
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ነቢያቱ ውሸት በስሜ ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፤ የውሸቱን ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል። ኤርሚያስ 14፡14
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ፤ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል፤ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ። ኤርምያስ 23፡16

ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡21
4.     ትንቢት መፈፀም አለበት  
ትንቢቱ ካለተፈፀመ ትንቢቱን እንደተሳሳተ እንረዳለን፡፡ በተለይ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ህዝብ ትንቢትን በመንፈስ የመለየት ምንም እድል ስላልነበረው የትንቢትን እውነተኝነት የሚያረጋግጡት መፈፀሙንና አለመፈፀሙን ጠብቀው አይተው ነበር፡፡ ነቢይ እንደማንም ሰው ሊሳሳት ይችላል፡፡ ነቢዩም ትንቢይ ካመጣ ደግሞ ተሳስቻለሁ ብሎ ይቅርታ መጠየቅ አለበት፡፡
በልብህም፦ እግዚአብሔር ያልተናገውን ቃል እናውቅ ዘንድ እንዴት ይቻለናል? ብትል፥ ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው። ዘዳግም 18፡21-22
5.     የነቢዩን አጠቃላይ የህይወት ባህሪ በመመልከት
ሰው ነቢይ ነኝ ቢል ነገር ግን ገንዘብን መውደድ የተሞላ ከሆነ እግዚአብሔር ለነቢይነት ቢጠራውም አንኳን ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነው እንደሚል ነቢይነቱን ለራሱ የግል ጥቅም ለክፋት ሊጠቀምበት ስለሚችል ከዚህ አይነት ሰው ትንቢት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? ማቴዎስ 7፡15-16
6.     የነቢዩን አምልኮ እና ለእግዚአብሔር ያለውን መሰጠት በመመልከት
በብሉይ ኪዳን እንዲያውም ሰው የተናገረው እንኳን ቢፈፀም እንኳን ነገር ግን ባእዳን አማልክትን እናመልክ ካለ ስቷል፡፡ ከተፈጥሮ በላይ ሃይል ነው ማለት ከእግዚአብሔር ብቻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ግን ያልሆነ ሃይል በአለም ላይ አለ፡፡
በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም ተአምራትም ቢሰጥህ፥ እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም፦ ሔደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ቢልህ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስማ። ዘዳግም 13፡1-3
ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና። 1ኛ ዮሐንስ 4፡1
እግዚአብሔር በነቢያት ቢጠቀምም እግዚአብሔር አብዛኛውን ጊዜ የሚናገረው በልባችን ነው፡፡ እግዚአብሔር በልባችን እንደሚናገረን አስተማማኝ መልእክት የለም፡፡ እግዚአብሔር በግላችን እንዲናገረን ጊዜ እንስጠው፡፡ እግዚአብሔር በነቢያቱ የሚናገረንን አንናቅ ነገር ግን ሁሉን እንፈትን መልካሙን እንያዝ፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ቅባት #መንፈስቅዱስ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ነቢያት #ነቢይ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ