Popular Posts

Wednesday, July 5, 2017

በመንፈስ የመመላለስ ሌላው ትርጉም

በመንፈስ መመላለስ እጅግ ርቆ ያለ ጥቂቶች ብቻ ሊደርሱበትና ሊገቡበት የሚችሉ ልምምድ አይደለም፡፡ በመንፈስ መመላለሰ ማንኛውም በጌታ ኢየሱስ አዳኝነት ያመነ ሰው ሁሉ ሊለማመደው የሚችል የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምንፈፅምበት በዚያም እግዚአብሄርን ደስ የምናሰኝበት የእግዚአብሄር አሰራር ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ተመሳሳይ ትርጉሞችን ማየት በመንፈስ መመላለስ ምን ማለት እንደሆነ ተጨማሪ መረዳትን ይሰጠናል፡፡  
በመንፈስ መመላለስ በብርሃን መመላለስ ነው፡፡
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። 1ኛ ዮሐንስ 1፡7
በመንፈስ መመላለስ በእምነት መመላለስ ነው፡፡
ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻለም፡፡ በእምነት እግዚአብሄርን ደስ መሰኘት ይቻላል፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት የሚታየውን አለማየት የማይታየውን ማየት ነው፡፡ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18
እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና፡፡ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7
በመንፈስ መመላለስ በፍቅር መመላለስ ነው፡፡
በፍቅር መመላለስ ማለት እግዚአብሄርንና ሰውን መውደድ ነው፡፡ ለሰው መልካም ማሰብ መልካም መናገርና መልካም ማድረግ ፍቅር ነው፡፡ በፍቅር የሚኖር ህጉን ሁሉ ፈፅሞታል፡፡ ገላትያ 5፡4
እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ። ኤፌሶን 5፡1-2
እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። ሮሜ 13፡8
በመንፈስ መመላለሰ በጥበበ መመላለስ ነው፡፡
ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። ቆላስይስ 4፡5
እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ኤፌሶን 5፡15
በመንፈስ መመላለሰ በቃሉ መመላለስ ነው፡፡
ቃሉ በሙላት ያለበት ቃሉን የሚያሰላስል ከቃሉ ውጭ የማያስብ ሰው በመንፈስ ይመላለሳል፡፡
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሃንስ 15፡7
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ሮሜ 8፡5
በመንፈስ መመላለስ በሰማያዊ ሃሳብ መመላለስ
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2
በመንፈስ መመላለሰ በእውነት መመላለስ
ወንድሞች መጥተው አንተ በእውነት እንደምትሄድ ስለ እውነትህ ሲመሰክሩ እጅግ ደስ ብሎኛልና። ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም። 3ኛ ዮሐንስ 1፡4
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #በመንፈስመመላለሰ #ቃሉንማሰላሰል #መንፈስበእኛ #ህግንመፈፀም #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሔርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፍቅር #እውነት #እምነት #ብርሃን #ሰማይ

በመንፈስ ስለመመላለስ ማወቅ ያለብን 5 ወሳኝ ነገሮች

ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ገላትያ 5፡16
ክርስትያኖች በመንፈስ እንድንመላለስ ታዘናል፡፡ በክርስትያ ስኬታማ የምንሆነው በመንፈስ ስንመላለስ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈፀም በመንፈስ መመላለስ ሌላ አማራጭ የሌለው ነገር ነው፡፡
1.      በመንፈስ መመላለስ የአትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ጉዳይ አይደለም፡፡
በመንፈስ መመላለስ ማለት አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ በሚሉ ህጎች መኖር ማለት አይደለም፡፡ እነዙህ ንጎች ሰውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲፈፅም የሚጠቅሙ ቢሆኑ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ህዝብ እግዚአብሔርን ባስደሰተው ነበር፡፡ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሚሉ ህጎች የእግዚአብሔርን አላማ እንድንፈፅም የሚረዱ ቢሆኑ ኖሮ ኢየሱስ ለሃጢያታችን መሞትና መንፈስ ቅዱስ መሰጠቱ አለዓስፈለገም ነበር፡፡ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ በሚሉት ህንጎች የእግዚአብሔርን መንገድ መጠበቅ የምንችል ቢሆን ኖሮ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ መኖርና መምራት አያስፈልገውም ነበር፡፡  
እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። ቆላስያስ 2፡22
2.     በመንፈስ መመላለስ በሆነ ደመና ውስጥ መመላለስ ማለት አይደለም፡፡
በመንፈስ መመላለስ ማለት የሆነ ልዩና የማይደረስበት መንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ መግባት ማለት አይደለም፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማንም ክርስትያን ሊያደርገው የሚችለው ነገር ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ እያንደሳንዱ ክርስትያን እንዲያደርገው የታዘዘውም ነገር ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ባንታዘዘው ሃጢያት የሚሆንብን የእግዚአብሔር ሊፈፀም የሚችል ትእዛዝ ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ጥቂት የተመረጡ ሰዎች እንደ እድል የሚገቡበት ልምምድ ሳይሆን ጌታ ኢየሱስን እንደ አዳኝና ጌታ የተቀበልን ሁላችን በየእለቱና በየደቂቃው የምንኖረው የህይወት ዘይቤ ነው፡፡
ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ገላትያ 5፡16
3.     በመንፈስ መመላለስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ መኖሩ ማለት ነው፡፡
የእግዚአብሔ ህይወት በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ህይወት ይመራናል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ህይወት ሃይልን ይሰጠናል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ህይወት በውስጣችን መኖሩ በመንፈስ እንድንኖር ያደርገናል፡፡  
እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም። ሮሜ 8፡9
4.     በመንፈስ መመላለስ በእግዚአብሔር ቃል ሃሳብ መኖር ማለት ነው፡፡
በመንፈስ መመላለስ ማለት የእግዚአብሔርን ቃል ማሰብ ማለት ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት እንደቃሉ መመላለስ ማለት ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት ከቃሉ ውጭ የሆነን ነገር አለማሰብ ማለት ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት እንደቃሉ ማሰብ መናገር እና ማድረግ ማለት ነው፡፡
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ ሮሜ 8፡5-7
5.     በመንፈስ መመላለስ የእግዚአብሔርን ህግ ሁሉ መፈፀም ነው፡፡
በመንፈስ የሚመላለስ ሰው እያንዳንዱን የብሉይ ኪዳን ህጎች መጠበቅ ሳያስፈልገው በመንፈስ በመመላለስ ብቻ በራሱ ሁሉንም የእግዚአብሔርን ህግ ይፈፅመዋል፡፡ መንፈስ ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለሚመራ በመንፈስ የሚመላለስ ሰው በዝርዝር ሳያውቀው የእግዚአብሔርን ህግ ይፈፅመዋል፡፡ በመንፈስ የሚመላለስ ሰው በህጉን ሁሉ ፀሃፊ ስለሚመላለስ የሚስተው አንድም የእግዚአብሔር ህግ የለም፡፡ በመንፈስ የሚመላለሰ ሰው የቱን ህግ እየፈፀምኩ ነው ብሎ በአእምሮው ሳይመራመር  የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሲፈፅም ራሱን ያገኘዋል፡፡
እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። ሮሜ 8፡13
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #በመንፈስመመላለሰ #ቃሉንማሰላሰል #መንፈስበእኛ #ህግንመፈፀም #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሔርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #መሪ

Tuesday, July 4, 2017

መንፈስ ቅዱስ በእኛ

ክርስትና ስርአትንና ወግን የምንፈፅምበት ባዶ ሃይማኖት አይደለም፡፡ ክርስትና በምድር እግዚአብሔርን መስሎ የመኖር ህይወት ነው፡፡ ክርስትና ሁለንተናን ለእግዚአብሔር መንግስት መስጠት ነው፡፡ ክርስትና በሁለንተና ጌታ ክርስቶስን መከተል ነው፡፡ ክርስትና ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ በመፈፀም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ነው፡፡ ክርስትና እግዚአብሔርን በመታዘዝ የተፈጠርንበትን አላማ ማሳካት ነው፡፡
ይህ ከፍ ያለ የክርስትና የህይወት ደረጃ ወግና ስርአትን በመፈፀም ብቻ የሚገኝ አይደለም፡፡ ይህ ከፍ ያለ የክርስትና የኑሮ ደረጃ የእግዚአብሔርን ሃይል ይጠይቃል፡፡ ካለ እግዚአብሔር ሃይል ይህ ደረጃ የማይታሰብ ከፍ ያለ የህይወት ደረጃ ነው፡፡
ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራልንን ስራ የተቀበልብን ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን ይኖራል፡፡ ክርስትናን ከሌሎች ሃይማኖቶች ልዩ የሚያደርገው ክርስቶስ በተከታዮቹ ውስጥ መኖሩ ነው፡፡ ጌተራ ኢየሱስን አዳኛችን ያደረግን ሁላችን የእግዚአብሔር ልጅነት ስልጣንን አግኝተናል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅነትን ደረጃ ለመኖር የሚያስፈልገን ሃይል ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
በክርስትና የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን እንድኖር ብቁ የሚያደርገን የእግዚአብሔር መንፈስ በውሰጣችን ስለሚኖር ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ስራ የምንሰራው በራሳችን ይል አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን መስለን የምንኖረው በሰው ጉልበት አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ልጅነትን የህይወት ደረጃ የምናሟላው በውስጣችን በሚኖረው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡
በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5
መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን በውስጣችን ይኖራል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንድንኖር ሊያግዘን በልባችን ይኖራል፡፡
ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ዮሃንስ 14፡15-17
የእግዚአብሔርን ልጅነትን የህይወት ደረጃ የምናሟላው በእግዚአብሔርን መንፈስ ረዳትነት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር በልቡና በነፍሱ እንዳለ የምንኖረው በውስጣችን ባደረው በእግዚአብሔር መንፈስ ምሪት ነው፡፡
እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡27
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ቅባት #መንፈስቅዱስ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሔርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Monday, July 3, 2017

አራቱ የማይመለሱ የፀሎት አይነቶች

እግዚአብሄር የመርህ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጋር የሚደርስ ሰው ማድረግ የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ ማድረግ የማይገባቸው ነገሮች አሉ፡፡
ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
ሰው በእግዚአብሄር መንገድ ካልፀለየ አይመለስለትም፡፡
1.      ከፈቃዱ የሚቃረን ፀሎት  
ከሰው አፍ የወጣውን ሁሉ እግዚአብሄር አይመልስም፡፡ በተለይ ከፈቃዱ የሚፃረንን ፀሎት እግዚአብሄር በፍፁም አይመልስም፡፡ ከባህሪው ጋር የሚቃረንን ልመና እግዚአብሄር አይመልስም፡፡
እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። 1ኛ ዮሐንስ 5፡14
2.     በቅንጦት የተፀለየ ፀሎት
ስንፀልይ የሚያስፈልገንን ነገር እንድንፀልይ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ የእኛን የምኞት ጥያቄ እንደሚመለስ በየትኛውም የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል ቃል አልተገባልንም፡፡ ስለዚህ ከመፀለያችን በፊት እውነተኛ ፍላጎት መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ስለዚህ ነው ለመፀለይ መቸኮል የሌለብን ፡፡ ለመፀለይ ምን እንደሚያስፈልገን ለማወቅ ጊዜ መሰጠት ያለብን፡፡ እንድ ጊዜ ፍላጎታችንን ካወቅን የሚመለስ ፀሎትን ለመፀለይ ቀላል ይሆንልናል፡፡
ስለዚህ ነው መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደምንፀልይ ያለማወቅ ድካማችንን የሚያግዘን፡፡ ሮሜ 8፡26
ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡3
3.     በጥርጥር የተፀለየ ፀሎት
እግዚአብሄር እምነትን ከእኛ ይጠብቃል፡፡ እርሱ ለእኛ ያለውን ፍቅርና እንክብካቤ በመረዳት እንድንፀልይ ይፈልጋል፡፡ ልባችንን ከጥርጥር እንድናነፃ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡23
ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ 1፡6-8
4.     በማጉረምረም የሆነ ፀሎት
ወደእግዚአብሄር የመቅረብ ፕሮቶኮሉ ምስጋና ነውለእግዚአብሄርነቱና ለመልካምነቱ እውቅና መስጠት ግድ ይላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ምንም አድርጎልን እንደማያውቅ እግዚአብሄርን ለመውቀስ የምንወረውርው ቃል እግዚአብሄር አይመልሰውም፡፡
እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፤ መዝሙር 100፡3-4
ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ማጉረምረም #ምስጋና #ቅንጦት #ጥርጥር #እንደፈቃዱ #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል

Sunday, July 2, 2017

አምላክ የመሆኑ ትርጉም

እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።  መዝሙር 33፡12
ነገር ግን አምላኩ የመሆን ትርጉም ምንድነው፡፡ ወይም እግዚአብሄር ለህዝብ አምላኩ ሆነ ማለት ምን ማለት ነው፡፡
 እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ። ኤርሚያስ 11፡4
እግዚአብሄር አምላኩ የሆነለት ማለት ፡-
1.      በእግዚአብሄር ፍቅር ካለምክኒያት ተወደናል ማለት ነው፡፡
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡8
2.     እግዚአብሄር ስለእኛ ሃላፊነት ይወስዳል ይመራናል ማለት ነው፡፡
ጌታን ለመከተል በወሰንን በዚያን ጊዜ እግዚአብሄር በእኛ አምኖዋል፡፡ ልጆቼ ናቸው ብሎዋል፡፡ ስለእነርሱ ሃላፊነት እወስዳለሁ፡፡ ስለእነሱ እጠየቃለሁ ብሎዋል፡፡
ፍቅር . . . ሁሉን ያምናል፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡7
3.     እግዚአብሄር ስለእኛ ተጠሪ ነው ማለት ነው፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
ስለዚህም ምክንያት፦ ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም፦ እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም፦ እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም። ዕብራውያን 2፡13
መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። ዮሃንስ 10፡11
4.     እግዚአብሄር ስለእኛ ያቅዳል በእቅዱም ይመራናል ማለት ነው፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርምያስ 29፡11
5.     እኛ የእግዚአብሄር ነን ማለት ነው፡፡
በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20
እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ። ሚልክያስ 3፡17
በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ። ኢሳይያስ 43፡7
6.     ከእግዚአብሄር እጅ ሊነጥቀን የሚችል የለም ማለት ነው፡፡
እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። ዮሃንስ 10፡28-29
7.     እግዚአብሄር በእኛ ፋንታ ሃይሉን ይገልጣል ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ስንፍና አድርገሃል፥ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ ይሆንብሃል። 2ኛ ዜና 16፡9
8.     እግዚአብሄር ከፊታችን ይወጣል ማለት ነው፡፡
እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? አለው። ዘጸአት 33፡15-16
9.     ለክብሩ የፈጠረን ለክብሩ የሚጠቀምብን ነን ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። መዝሙር 100፡3
10.    የእግዚአብሄር የሆነውን ተካፍለናል ማለት ነው፡፡
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ የጴጥሮስ 1፡2-3
ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡23

#እግዚአብሔር #አምላክ #የተባረከ #የተመሰገነ #የታደለ #የተሞገሰ #የተወደደ #የተከናወነ #የተሳካ #የተለየ #የከበረ #የሚቀናበት #የተጠቀመ #እድለኛ #ክብር #ምሪት #ሰላም #ቃል #እረፍት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Saturday, July 1, 2017

እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው

ምስጉን ነው የሚለው ቃል ሰፊ ትርጉም ያለው ሲሆን ከእነዚህም መካከል የተባረከ ፣ የተመሰገነ ፣ የታደለ ፣ የተሞገሰ ፣ የተወደደ የተከናወነ ፣ የተሳካ ፣ የተለየ ፣ የከበረ ፣ የሚቀናበት ፣ የተጠቀመና እድለኛ የሚሉት በከፊል ሊገልፁት ይችላሉ፡፡
የእግዚአብሄር ህዝቦች እጅግ የተባረክብ ስለሆንን ማንም ተቃውሞን አይዘልቅም፡፡
እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ሮሜ 8፡31
የእግዚአብሄር ህዝብ እጅግ ከመመስገኑ የተነሳ እግዚአብሄር ሊያወስው የጠራው ነው
እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።  መዝሙር 33፡12
የእግዚአብሄር ህዝብ እጅግ ከመመስገኑ የተነሳ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ይኖራል
አምላካችን እግዚአብሔር በምንጠራው ጊዜ ሁሉ እንደሚቀርበን፥ አምላኩ ወደ እርሱ የቀረበው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው? ዘዳግም 4፡7
የእግዚአብሄር ህዝብ እጅግ ከመመስገኑ የተነሳ እግዚአብሄር ህዝቡን ለመቤዠት ከፊቱ ይሄዳል
አንተ እግዚአብሔር ከግብጽ ካወጣኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብን በማሳደድ በታላቅና በሚያስፈራ ነገር ለአንተ ስም ታደርግ ዘንድ፥ ለአንተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደሄድህለት እንዳንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን? ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘላለም ሕዝብህ አደረግኸው፤ አንተም፥ አቤቱ፥ አምላክ ሆነኸዋል። 2ኛ ዜና 17፡21-22
አምላኩ እግዚአብሄር የሆነ ህዝብ የተባረከ ህዝብ ነው
እንደዚህ የሚሆን ሕዝብ የተመሰገነ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው። መዝሙር 144፡15
አምላኩ እግዚአብሄር ከመሆን በላይ የሆነ ደረጃ የለም
ለአንተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደሄድህለት እንዳንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን? 2ኛ ዜና 17፡21
እግዚአብሄር አምላኩ የሆነ ህዝብ ካልተደሰተ ፣ ከተጨነቀ ፣ ካልተረጋጋና ካልፈነጠዘ ማን ሊደሰት ይችላል?
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሔር #አምላክ #የተባረከ #የተመሰገነ #የታደለ #የተሞገሰ #የተወደደ #የተከናወነ #የተሳካ #የተለየ #የከበረ #የሚቀናበት #የተጠቀመ #እድለኛ #ክብር #ምሪት #ሰላም #ቃል #እረፍት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ