ለማንም
አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፥ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ አለው። የማርቆስ ወንጌል 1
፥44
ለማንም
አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት የማርቆስ ወንጌል 7፥36
ወደ
ቤቱም ሰደደውና፦ ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው። የማርቆስ ወንጌል 8፥26
ስለ
እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው። የማርቆስ ወንጌል 8፥30
ከተራራውም
ሲወርዱ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያዩትን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው። የማርቆስ ወንጌል 9፥9
እርሱም
ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፥ ነገር ግን፦ ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፥ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው። የሉቃስ ወንጌል 5፥14
ወላጆችዋም
ተገረሙ፤ እርሱ ግን የሆነውን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው። የሉቃስ ወንጌል 8፥56
ኢየሱስ
ከፈወሰ እና ድንቅ እና ታእምራት ካደረገ በኋላ ለማንም አትናገሩ ሲል በተከታታይ እናያለን፡፡ ሰዎች የእግዚአብሄርን ድንቅ መናገራቸው መልካም ቢሆንም ነገር ግን ያለጊዜው የሰዎችን ትኩረት መሳብ እና ዝነኛ መሆን በኢየሱስ ላይ የሚያመጣው ጉዳት ስለሚበልጥ ለማንም አትናገሩ ብሎ ድንቅ የተደረገላቸውን
ያስጠነቅቅቃአቸው
ነበር፡፡
ኢየሱስ
የትኩረት እጥረት አልነበረበትም፡፡ የኢየሱስ ትኩረት የእግዚአብሄርን የአባቱን ፈቃድ በምድር ላይ አድርጎ አብን ማክበር ነበር፡፡ በትኩረትም ያለትኩረትም የእግዚአብሄርን
ፈቃድ መፈፀም አነደሚቻል ኢየሱስ በአገልግሎቱ አሳትይቶዋል፡፡ የእግዚአብሄርን የልቡን ፈቃድ አድርጎ ለማለፍ የሰውን ትኩረት መሳብ
ግዴታ አይደለም፡፡
እነሆ
የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
አይከራከርም
አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። ማቴዎስ 12፡18-19
የኢየሱስ
ትኩረት ብዙ ሰዎችን መሰብሰብ ሳይሆን ወደ እርሱ የመጡትን በታማኝነት እና በትጋት ማገልገል
ነበር፡፡
የኢየሱስ
የምድር ላይ አገልግሎት የሚመዘነው በተከተሉት ሰዎች ብዛት እንዳልነበረ ኦየሱስ ጠንቅቆ ያውቅ ስለነበረ
ትኩረቱ ወደእርሱ የመጡትን በታማኝነት እና በትጋት ማስተማር እና መፈወስ ነበር፡፡
እንዲያውም
ኢየሱስ ይጠነቀቀ
የነበረው ካለጊዜው የመጣ ዝና በአገልግሎቱ ላይ አላስፈላጊ ጫና እንዳይፈጥርበት እና ከአገልግሎቱ እንዳያስተጓጉለው ነበር፡፡
እግዚአብሄር
አብ ብዙዎች በኢየሱስ አገልግሎት የሚጠቀሙበት ጊዜው ሲደርስ የኢየሱስ ዝና እስከ ሶርያ ድረስ እንደ ወጣ መፅሃፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡
ያም
ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ። ማቴዎስ 9፡26
ኢየሱስ
ከፈወሰ በሁዋላ ለማንም አትናገሩ ቢልም የኢየሱስ ዝና የሚወጣበት ትክክለፃው ጊዜ ሲመጣ ግን ኢየሱስን ዝነፃ እንዳይሆን ምንም ነገር አላገደውም ነበር፡፡
ጊዜ
በጊዜው የሚመጣ ርያ ድረስ ወጣ
ዝናውም
ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም። የማቴዎስ ወንጌል 4፥24
ያም
ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ። የማቴዎስ ወንጌል 9፥26
በዚያ
ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፥ የማቴዎስ ወንጌል 14፥1
ዝናውም
ወዲያው በየስፍራው ወደ ገሊላ ዙሪያ ሁሉ ወጣ።የማርቆስ ወንጌል 1፥28
ኢየሱስም
በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው አገር ሁሉ ዝና ወጣ።የሉቃስ ወንጌል 4፥14
ዝናም
በዙሪያው ባለች አገር ወደ ስፍራው ሁሉ ስለ እርሱ ወጣ። የሉቃስ ወንጌል 4፥37
ይህም
ዝና ስለ እርሱ በይሁዳ ሁሉ በዙሪያውም ባለች አገር ሁሉ ወጣ።የሉቃስ ወንጌል 7፥17
እግዚአብሄር ሞገስን ሲያበዛ ካለምንም ጥረት እና
ጭንቀት በጊዜው ስማችንን ያወጣዋል፡፡
እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡6
የእግዚአብሄር
ሞገስ ህዝቡን በጥረት ሳይሆን በመለኮታዊ መንገድ በቀላሉ ይጠራል፡፡
እነሆ፥ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፥ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣሉ። ትንቢተ ኢሳይያስ 55፡5
ጊዜውን
የጠበቀ ዝና ሰዎችን ለፈውስ እና ለነፃነት እንደሚሰበስብ ሁሉ ያለጊዜው የሆነ የሰዎችን ትኩረት መፈለግ በአገልጋዩ ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ከአገልግሎት ሊያስተጓጉል ይችላል፡፡
እግዚአብሄር
አንዳንዴ ህይወታችንን ቀለል የሚያደርገው እና ለጊዜው የሚደብቀን ከጊዜው በፊት ያለውን የዝነኝነት አላስፈላጊ ሸክም እንዳንሸከም ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት ትኩረትን መሳብ አስፈላጊ አይደለም፡፡
አገልጋይም
ዝና ያለውን ጥቅም ብቻ ካየ እና ከዝናው መምጣት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ሃላፊነቱን ካላየ ዝናውን ብቻ ሲያሳድድ እግዚአብሄር ከሰጠው አገልግሎት ይስተጓጎላል፡፡
ከዝና
ጋር አብረው የሚመጡ ብዙ አላስፈላጊ ሸክሞች አሉ፡፡ ሰው ራሱ ፈልጎ ዝናውን ካላመጣው እና እግዚአብሄር በራሱ ጊዜ ካመጣው ከዝና ጋር የሚመጡ ሸክሞችን የሚሸከምበት ፀጋን ራሱ እግዚአብሄር ያበዛለታል፡፡
ነገር
ግን ሰው ራሱን የሰዎችን ትኩረት ከሳበ ፣ ራሱን ዝነኛ ካደረገ እና በቅልጥፍናው ራሱን አላግባብ ካስተዋወቀ ዝናውን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ዝናውን ለመጠበቅ አላስፈላጊ ዋጋ ይከፍላል፡፡ በተጋነነው ማስታወቂያ የመጡትን ሰዎች ማርካት ችግር ይሆናል፡፡ አላግባብ ትኩረታቸው የተሳበውን
ሰዎች ለማስደሰት እግዚአብሄር ከሰጠው የህይወት አላማ ለመውጣት ይፈተናል፡፡ በራሱ ያመጣውን ታዋቂነት እና ዝና ለማስጠበቅ እግዚአብሄርን ያማከለ ሳይሆን ህዝብን ያማከለ ሰው ይሆናል፡፡
እግዚአብሄር
ህዝቡን እንዲያገለግልበት የሰጠውን አቅርቦት ዝናን ለማስጠበቅ ሊያባክነው ይችላል፡፡
በጊዜው
እግዚአብሄር ያመጣውን ዝና የሚጠብቅለት ማንም ሰው እስከማያስፈልገው ድረስ ራሱ እግዚአብሄር ይጠብቀዋል፡፡ ሰው በራሱ ያመጣውን ዝነኝነት ራሱ እንዳመጣው በራሱ ወጭ ይጠብቀዋል እንጂ እግዚአብሄር አይጠብቅለትም፡፡
አገልጋዩ የሚያገለግለውን አገልግሎት አያስተዋውቅ
ማለት ሳይሆን የራሱን የስጋ ክንድ በመጨመር ትከረቱ ማስተዋወቁ ላይ አይሁን ነው፡፡ የአገልጋይ ትኩረት መሆን ያለበት እግዚአብሄር
የላከለትን ሰዎች በታማኝነት ማገልገል ላይ መሆን አለበት፡፡
በምንም ነገር ላይ ማስተዋወቅ ያለብን ጌታን እንጂ
ራሳችንን መሆን የለበትም፡፡ መታወቅም ካለብን ጌታን በማስተዋወቅ እንጂ ራሳችንን ብቻ በማስተዋወቅ መሆን የለበትም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ መጣጥፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
#ራዕይ #የቅንጦት #አስፈላጊነቱ
#ፈቃዱ #መምራቱ
#አጀንዳው #ኢየሱስ
#ጌታ #ቤተ
ክርስቲያን #ስኬት
# #ተመስጦ #ስብከት
#ትኩረት #ዝና #ማስታወቅ