Popular Posts

Wednesday, December 9, 2020

እግዚአብሔር ግን የታመነ ነው

 


እግዚአብሔር ግን የታመነ ነው

እግዚአብሔር ግን የታመነ ነው፥ ለእናንተም የሚነገረው ቃላችን አዎንና አይደለም አይሆንም። በእኛ ማለት በእኔና በስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል። እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና፥ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ስለ ክብሩ በእኛ የሚነገረው አሜን በእርሱ ደግሞ ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:18-20

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች መፈፀም እንደማይችሉ ቢያውቁ ወይም ባይፈልጉም እንኳን በተለያየ ምክኒያት ተገደው ቃል ይገባሉ፡፡ ወይም ቃል የሚገቡት ቃል ባልገባለት ከዚህ ሰው ጋር ያለኝ ግንኙነት ይበላሻል ብለው ፈርተው ነው፡፡

እፈፅመዋለሁ ብለው ቢሆን ፈቃደኝነቱ ቢኖራቸው እንኳን ሰዎች ፍጥረት ስለሆኑና ውስን ስለሆኑ አንዳነበደ ጊዜ የገቡትን ቃል መፈፀም ያቅታቸዋል፡፡

ሰዎች ሰዎችን አይተው እግዚአብሄርን እንደዚያ ሃሳቡን የሚለዋውጥ አድርገው ያዩታል፡፡ እግዚአብሄር ግን የታመነ ነው፡፡

እግዚአብሄር ቃል ከገባ ይፈፅመዋል፡፡ እግዚአብሄር ቃል ከገባ ፈፅሞታል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ቃል ከገባ ፈቃደኝነቱም ሃይሉም አለው፡፡

እግዚአብሔርም፦ እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና መልካም አይተሃል አለኝ። ትንቢተ ኤርምያስ 1፡12

እግዚአብሄር ያሰበውንና ያቀደውን እንዳያደርግ የሚከለክለው ሀይል የለም፡፡

እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፤ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውን ቃል ፈጸመ፤ ሰቆቃው ኤርምያስ 2፡17

በእግዚአብሄር ቃል የተገቡ ነገሮች ሁሉ ተፈፅመዋል፡፡ እግዚአብሄር 100% ቃል የመፈፀም ታሪክ አለው፡፡

እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 21፡45

እነሆም፥ ዛሬ የምድርን ሁሉ መንገድ እሄዳለሁ፤ እናንተም እግዚአብሔር ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፤ ሁሉ ደርሶላችኋል፤ ከእርሱም አንድ ነገር አልቀረም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 23፡14

እግዚአብሄር የተናገረው መፈፀም ብቻ አይደለም የተናገረው አይዘገይም ሁሉም በጊዜው ይሆናል፡፡  

ስለዚህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ሕዝቅኤል 12፡28

ከእኛ የሚጠበቀው አሜን ብሎ ማመን ብቻ ነው፡፡

ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት። የሉቃስ ወንጌል 1፡45

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ታማኝ #የታመነ #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መደገፍ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 


No comments:

Post a Comment