Popular Posts

Saturday, January 18, 2020

የአንድነት ዋጋ



መተባበርና አንድነት የከበረ ነገር ነው፡፡ አንድነት ትልቅ ዋጋ ያለው ሃብት ነው፡፡ ሰው በአንድነት የሚያደርጋቸው ነገሮች  በተናጥል ከሚያደርጋቸው ነገሮች በላይ ፍሬያማ ያደርጉታል፡፡
በአንድነት ውስጥ የታመቀ ትልቅ ጉልበት አለ፡፡ ሰው ሲተባበር እና በአንድ ላይ ሲሰራ በተናጥል ከሚያመጣው ውጤት በላይ የተሻለ ውጤት ያመጣል፡፡ ሰው ፣ በቤተሰብ ፣ በቤተክርስትያን ፣ በስራና በአገር ደረጃ በተናጥል ከሚሰራው ስራ ይልቅ ተባብሮ የሚሰራው ስራ ብዙ ጥቅምን ብዙ ነው፡
ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፥ መቶውም አሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። ኦሪት ዘሌዋውያን 26፡8
አንድነት ግን ቀላል አይደለም፡፡ አንድነት ይበልጥ ፍሬያማ እንደሚያደርግ ሁሉ አንድነት ይበልጥ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
ሰው ብዙን ጊዜ ከአንድነት ይልቅ መለያየትን የሚመረጥው በአንድነት ውስጥ ያለውን እምቅ ሃይል በቅጡ ስለማይረዳና አንድነት የሚጠይቀውን ዋጋ መክፈል ስለማይፈልግ ነው፡፡ ብዙ ሰው በአንድንት ያለውን ዋጋ ከመክፈል ይልው በስንፍና በተናጥል ያነሰ ነገርን ማግኘትን ይመርጣል፡፡ ሰው ለአንድነት ዋጋ መክፈል ሳይፈልግ ሲቀር በውስጡ ያለውን የአንድነትን እምቅ ጉልበት ያባክነዋል፡፡
ማንም ሃያል ሰው በጋራ ከሚሰራ ስራ በላይ ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ማንም ጠቢብ ሰው ብቻውን ምንም ያህል ቢጥር በጋራ ቢሰራ እንደሚያመጣው ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ በአንድነት ብቻ ውስጥ የሚገኝ በተናጥል ውስጥ የሚየገኝ ለአንድነት ብቻ የተለየ ታላቅ ሃይል አለ፡፡
አንድነት ከተናጥልነት በላይ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ነገር ግን አንድነት ከተናጥል በላይ እጅግ ብዙ ፍሬ እንድናፈራ ያደርገናል፡፡
አንድነት ማለት ተመሳሳይነት ማለት አይደለም፡፡ አንድነት ማለት የተለያዩ ሰዎች ለአንድ የጋራ አላማ መስራት ማለት ነው፡፡ እውነት ነው እኛን ከማይመስል ሰው ጋር ከመስራት ይልቅ ከእኛ ተመሳሳይ ሰው ጋር መስራት ይቀላል፡፡ ነገር ግን እኛን ከማይመስል ሰው ጋር ለጋራ አላማ መስራት ይበልጥ ፍሬያማ ያስደርጋል፡፡  
አንድነት ትህትናን ይጠይቃል፡፡ አንድነት የማይመስለንን ሰው መቀበል ይጠይቃል፡፡ አንድነት ከእኛ በተለየ ሰው ማመን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ከእኛ የተለየን ሰው ለጋራ አላማ መታገስን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ዋጋ ይከፍላል፡፡ አንድነት ዋጋን ይከፍላል፡፡
አንድነት ሌላውን መረዳትና ሌላውን ማመንን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ራስ ወዳድ አለመሆን ሌላውን ማስቀደምን ይጠይቃል፡፡ አንድነት እኛን የማይመስልን ሰው መታገስ ይጠይቃል፡፡ አንድነት የእኔ  አሳብ ብቻ ይሰማ አለማለትን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ትህትናን ለጋራ አላማ በሌሎች ሃሳብ መስማማትን ይጠይቃል፡  
በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡1-2
አንድነት የሰነፎች እና የቸልተኞች አይደለም፡፡ አንድነት ትጋትን ይጠይቃል፡፡
በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡2-3
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #መዳን #እምነት #አንድነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ህብረት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment