Popular Posts

Sunday, January 26, 2020

የሚታየው የጊዜው ነው



የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ . . . የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡17-18
በተፈጥሮ አይናችን የምናየው ነገር ሁሉ ዘላለማዊ አይደለም፡፡ በተፈጥሮአዊ አይናችን የምናየው ነገር ሁሉ የጊዜው ነው፡፡ በተፈጥሮ አይናችን የምናየው ነገር ሁሉ የሚያልቅበት የሚያከትምበት ጊዜ አለው፡፡ በተፈጥሮ አይናችን የምናየው ነገር ሁሉ ይለወጣል፡፡ በተፈጥሮ አይናችን የምናየው ነገር ሁሉ ያልፋል ይጠፋል፡፡
በአይናችን የምናየው ሰማይና ምድር እንኳን ቋሚ አይደለም፡፡ በአይናችን የምናየው ሰማይና ምድር እንኳን ጊዜያዊ ነው፡፡ በአይናችን የምናየው ሰማይና ምድር እንኳን ዘላለማዊ አይደለም፡፡ በአይናችን የምናየው ሰማይና ምድር እንኳን ያልፋል ይጠፋል፡፡
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ የማቴዎስ ወንጌል 24፡35
በተፈጥሮ አይን የማይታየው የዘላለም ነው፡፡ ዘላቂው በተፈጥሮ አይን የማይታየው ብቻ ነው፡፡
የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡18
የማያልፈው በተፈጥሮ አይን የማይታየው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡ የማይታየው በእምነት አይናችን የምናየው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። የማቴዎስ ወንጌል 24፡35
የማይታየው በተፈጥሮ አይናችን የማናየው የእግዚአብሄር መንግስት ብቻ ነው፡፡ የማያልፈው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል የተፈጠረው መንፈስ ብቻ ነው፡፡
ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም። የሉቃስ ወንጌል 21፡33
የማያልፈው የእግዚአብሄርን ቃል የሚያደርገው ሰው ብቻ ነው፡፡ ለዘለላም የሚኖረው የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚያደርግ ሰው ብቻ ነው፡፡
ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፡17
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ . . . የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡17-18
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እንፍዋለት  #ሕይወታችሁ #ዘላለም #የእግዚአብሄርቃል #ዘላለም #የሚታየው #የማይታየው #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment