Popular Posts

Thursday, January 30, 2020

ከእግዚአብሔር ጋር የመኖር ብልሃት



ሰማይንና ምድርን የፈጠረው እግዚአብሄር ነው፡፡
ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ። እርሱ በባሕሮች መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም አጽንቶአታልና። መዝሙረ ዳዊት 24፡1-2
የምድር ባለቤት እግዚአብሄር ነው፡፡
ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡8
ምድርን እያስተዳደረ ያለው የምድር ገዢው እግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሔር ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና። መዝሙረ ዳዊት 47፡2
እግዚአብሄር የምድር ፈራጅ ነው፡፡
ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል። የሐዋርያት ሥራ 17፡31
ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው እግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ለአላማው ነው፡፡
ታዲያ ለሰው ከምድር ባለቤት ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት መኖር እንዳለበት ከማወቅ የበለጠ የሚያስፈልገው እውቀት የለም፡፡ ለሰው መጀመሪያ የሚያስፈልገው እውቀት ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት በሰላም እንደሚኖር የሚያሳውቀው እግዚአብሄርን የመፍራት ጥበብ ነው፡፡   
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 9፡10
ሰው ምንም እውቀት ቢኖረው ከምድር አስተዳዳሪ ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት መኖር እንዳለበት ካላወቀ ያለው ሌሎች አውቀቶች ሁሉ ዋጋ የላቸውም፡፡ ሰው ምንም እውቀት ቢኖረው ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደሚኖር ካላወቀ ገና ምንም አያውቅም፡፡
በምድር በሰላም እና በስኬት ለመኖር ዝቅተኛው መመዘኛ እግዚአብሄርን እንደ እግዚአብሄርነቱ ማክበር ወይም እግዚአብሄርን የመፍራት እጥበብ ነው፡፡
ለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡21-22
ከምድር ባለቤት ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደሚኖር ሳያውቅ በሰላም እኖራለሁ ማለት ዘበት ነው፡፡
ከምድር ገዢ ጋር በትህትና ሳይሄዱ ይሳካልኛል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ትንቢተ ሚክያስ 6፡8
ሰው በምድር ላይ ያሉትን ፈተናዎች ሁሉ ተቋቁሞ ማለፍ የሚችለው እግዚአብሄርን እንዴት እንደሚፈራው ሲያውቅ ብቻ ነው፡፡
እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፈራ ዘንድ፥ ይህችንም ሥርዓት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን። ኦሪት ዘዳግም 6፡21
እግዚአብሄር ከሰው እጅግ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር ብዙ የሚያልፋቸው ነገሮች አሉ ነገር ግን እርሱን በመፍራት ላይ ግን አይደራደርም፡፡ እግዚአብሄር ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን ባይጠብቅም  እርሱን መፍራትን ግን ከሰው ይጠብቃል፡፡
የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መጽሐፈ መክብብ 12፡13-14
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ መጽሐፈ ምሳሌ 9፡10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment