I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
If you had it to do over again, you’d marry me for love Love and Let Live Love and Let Live By Dale Carnegie How To Win Friends And I...
-
ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል ? ኣላቸው። የሐዋርያት ሥራ 16:30 ይህ የብዙ ሰው የልብ ጨኸት ነው፡፡ ይህ በህይወት ዘመን ሊመለስ የሚገባው ወሳኝ ጥያቄ ...
-
Enjoying the goodness of the Lord in every moment of my life.
-
ምስክርነት በአቢይ ዋቁማ ዲንሳ Witnessing Abiy Wakuma Dinsa
-
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው፡፡የሰው መኖሪያ ቤቱ እና ስጋው ከምድር አፈር ቢበጅም ሰው ግን አፈር አይደለም፡፡ ሰው በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረ በስጋ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ነው፡፡ እግዚአ...
-
We are a part of generations. We build a foundation for the next generation and we actually shape it in what we say and do. We co...
-
የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። መዝሙር 33፡4 እግዚአብሄር ቅን ነው፡፡ የእግዚአብሄርም ቃል ቅን ነው፡፡ የእግዚአብሄ ቃል ቀጥተኛ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እንዳለ ሊቀበሉት...
Thursday, April 23, 2020
እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል። የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል ያገኙህማል። አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ። የሆድህ ፍሬ፥ የምድርህም ፍሬ፥ የከብትህም ፍሬ፥ የላምህም ርቢ፥ የበግህም ርቢ ቡሩክ ይሆናል። እንቅብህና ቡሃቃህ ቡሩክ ይሆናል። አንተም በመግባትህ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በመውጣትህም ቡሩክ ትሆናለህ። እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፥ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ። እግዚአብሔር በረከቱ በአንተ ላይ በጐተራህ በእጅህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ያዝዛል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል። የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትጠብቅ፥ በመንገዱም ብትሄድ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለልህ ለእርሱ የተቀደሰ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል። የምድር አሕዛብም ሁሉ የእግዚአብሔር ስም በአንተ ላይ እንደ ተጠራ አይተው ይፈሩሃል። እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በከብትህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ እግዚአብሔር በጎነቱን በላይህ ያበዛል። እግዚአብሔርም ለምድርህ በወራቱ ዝናብ ይሰጥ ዘንድ፥ የእጅህንም ሥራ ሁሉ ይባርክ ዘንድ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትልሃል፤ ለብዙ አሕዝብም ታበድራለህ፥ አንተ ግን ከማንም አትበደርም። ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም። ኦሪት ዘዳግም 28፡1-14
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment