ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14
በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገረው ኢየሱስ ከመወለዱ ከ700 አመት በፊት ነበር። ትንቢቱም ድንግል እንደምትጸንስ ወንድ ልጅም እንደምትወልድ ተናግሮ ነበር። የሚወለደው ልጅ ስም አማኤል እንደሚባል በትንቢቱ ተነግሮ ነበር። አማኑኤል የሚለው ስም ትርጉም እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ማለት ነው።
ትንቢቱ በኢየሱስ ከድንግል ማርያም መወለድ ተፈጸመ።
በነቢይ ከጌታ ዘንድ፦ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው። የማቴዎስ ወንጌል 1፡22-23
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ከእርሱ ጋር እንዲኖር እና ህብረት እንዲያደርግ ነበር።
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 2፡26-27
ነገር ግን እግዚአብሄርን ባለመታዘዙ ሰው ከእግዚአብሄር ፍጹም ተለያይቶ ነበር።
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ኦሪት ዘፍጥረት 2፡16-17
የእግዚአብሄር ልጅ የሆነው ኢየሱስ በድንግል ማርያም በኩል ወደምድር የመጣው በሃጢያታችን ምክኒያት ነው።
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ፀሎት #ፈቃዱ #መልስ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ክሪስማስ #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ልደት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #ገና
No comments:
Post a Comment