ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር ክፍል 3
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡1-2
መፅሃፍ ቅዱስ ስለሰዎች በተለይ ስለነገስታት መፀለያችን ጸጥ እና ዝግ ብለን እንድንኖር እንደሚያስችለን መፅሃፍ ቅዱስ አጥብቆ ይመክረናል፡፡
ክርስትያን ባለው መንግስታዊ አስተዳደር ደስተኛ ሊሆንም ይችላል ላይሆንም ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በነገስታቱ እና በመኳንንቱ ላይ ቅሬታ ሊኖረው ይችላል፡፡ በነገስታቱ እና በመኳንንቱ ላይ ቅሬታ አለው ማለት ግን ልመናና ጸሎት ምልጃና ምስጋና እንዳያቀርብ ፈቃድ ይሰጠዋል ማለት ግን አይደለም፡፡
በነገስታቱ እና በመኳንንቱ የሚወሰነውን ውሳኔ ይደግፍም ይቃወምም ክርስትያን ከመፀለይ ውጭ ተበላሽቷል የሚላቸውን ነገሮችን ለማስተካከል የሚችልበት ሌላ ምንም አማራጭ አይኖረውም፡፡
እንዲያውም የተበላሹትን ነገሮች የምናስተካክልበትና በዚያም ጸጥ እና ዝግ ብለን መኖር የምንችልበት መንገድ ልመናና ጸሎት ምልጃና ምስጋና አብዝተን ማቅረባችን ብቻ ነው፡፡
ክርስትያን እንደአገር ዜጋ በፖለቲካ ወይም በአገር አስተዳደር ጉዳዮች መሳተፍ ይኖርበታል፡፡ ክርስትያን የተበላሹ ነገሮች እንዲስተካከሉ የመናገር እና የመሞገት ሃላፊነት እንዳለበት አሌ የማይባል ሃቅ ነው፡፡
ክርስትያን ተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ መሳተፍ እና አማራጭ የፖለቲካ ፖሊሲዎችን ማራመድ ይችላል፡፡ ነገር ግን ተቃዋሚነቱ የእግዚአብሄር ስርአት ወገን ከመሆን ሊያግደው በፍፁም አይገባም፡፡ ከገዢው ፓርቲ የተለየ አቋም መያዙ ለነገስታቱ እና ለመኳንንቱ ለሰዎች ሁሉ እንዳይፀልይ ሊያግደው አይገባም፡፡ ተቃዋሚነቱ ለነገስታቱ እና ለመኳንንቱ እስካለመፀለይ ድረስ ካደረሰው የእግዚአብሄርን ስርአት ይቃወማል፡፡ ምንም አይነት የፖለቲካ አቋሙ የእግዚአብሄርን ስርአት እንዲቃወም ማለትም ስለነገስታ እና ስለመኳንንቱ እንዳይፀልይ ሊያደርገው አይገባም፡፡
ከማንኛውም የፖለቲካ አመለካታችን በላይ እንደ ክርስትያን ስለ ነገስታ እና መኳንንት እንዲሁም ስለ ሰዎች ሁሉ ልመናና ጸሎት ምልጃና ምስጋና ልናቀርብ ይገባናል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት
No comments:
Post a Comment