ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር ክፍል 4
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃምምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደጢሞቴዎስ 2፡1-2
መጽሃፍ ቅዱስ በሚያዘው መሰረት ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለመኳንንትም ሁሉ ማድረጋችን እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖርያስችለናል፡፡
ነገር ግን እንደ ክርስትያን ከልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ውጭ የሆነ እና እነዚህን ያላካተተ ማንኛውምመፍትሄ ፍሬያማ ሊሆን አይችልም፡፡
ክርስትያን ስለፍትህ መጮህ ይገባዋል፡፡ ነገር ግን ከልመናና ጸሎት ከምልጃና ምስጋና ውጭ የሆነ ባዶ ተቃውሞየታለመለትን አላማ ግብ ሊመታ አይችልም፡፡ ከልመናና ጸሎት ከምልጃና ምስጋና ያላስቀደመ ማንኛውም ነገርመፍትሔ ሊሆን አይችልም።
ስለነገስታት እና መኳንንት ከሚደረግ ልመናና ጸሎት ምልጃና ምስጋና የጎደለው ተቃውሞ ለስጋዊ ምኞት አርነትንመስጠት ብቻ ነው፡፡
ነገስታትን መኳንንትን ሰዎችን ሁሉ በልመና እና በጸሎት በምልጃ እና በምስጋና እንድናገለግል ተጠርተናል፡፡የማንወደውን ሰው በጸሎት ልናገለግለው አንችልም፡፡ ልንፀልይለት እስከማንችን ድረስ የምንጠላውን ሰውበፍፁም ልናገለግለው በፀሎት ልንደግፈው አንችልም፡፡ ልመና እና ጸሎት ምልጃ እና ምስጋና እንድናደርግከሚመክረን ከእግዚአብሔር ጋር በመወገን የእግዚአብሔርን ስርአት እንደግፍ።
ስለዚህ ትሁት ሆነን ለስጋችን አርነት ሳንሰጥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትናስለ መኳንንትም ሁሉ እናድርግ፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት#መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት
No comments:
Post a Comment