ኢኮኖሚ ምጣኔ ሀብት ነው፡፡ ሀብት ውስን ነው። የምጣኔ ሀብትጥናት ውስን የሆነውን
ሀብት መጥኖ ስለመጠቀም ያስተምራል፡፡ውስን የሆነውን ሀብት ቅድሚያ ለሚሰጠው ነገር በሚገባካልተጠቀምንበት አላግባብ ይባክናል። የእግዚአብሔር መንግስትምጣኔ ሀብት የሚሰራው በመልካም አስተዳደር ነው። በህይወታችንውስጥ ያለው ፀጋ ፣ ክህሎት ፣ ጊዜ እና ጉልበት ሁሉ ለታቀደለትለእግዚአብሔር ፈቃድ ብቻ ካልተጠቀንበት ይባክናል። እግዚአብሔርየሰጠን ማንኛውም ስጦታ ውስን እና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭለሆነ ነገር የሚበቃ አይደለም። የእግዚአብሔር አቅርቦት ለፈቃዱበትክክል የሚበቃ እንጂ የሚያንስም የሚጎድልም አይደለም። እግዚአብሔር የሰጠንን አቅርቦታ ፈቃዱ ባልሆነ ነገር ላይከተጠቀምንበት እና አላግባብ ካባከንነው የእግዚአብሔርን ፈቃድመፈፀም ያቅተናል። ለፈቃዱ የማንጠቀምበት ሁሉ ለታለመለትአላማ ስላልዋለ የአመፃ ገንዘብ ይባላል። እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። የሉቃስ ወንጌል 16:9
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ራዕይ #ምሪት #የእግዚአብሄርአጀንዳ #የእግዚአብሄርፈቃድ#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን#መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #አማርኛ #ሰላም#ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር#ኢትዮጲያ #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment