Popular Posts

Wednesday, August 14, 2024

ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር ክፍል 1

እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1 ወደ ጢሞቴዎስ 21-2

መቼም ጸጥና ዝግ ብሎ መኖር የማይፈልግ ማንም ሰው የለም፡፡ በዚህ የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ ጸጥና ዝግ ብሎ ለመኖር ክርስትያን ምን ማድረግ እንደሚገባው ይመክራል፡፡ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ የሚለው አባባሉ እንደ ክርስትያን እጅግ በጣም ከፍተኛ አፅንኦት መስጠት የሚገባን ሃላፊነት ያመለክታል፡፡

በዚህ ክፍል ውስጥ የሚመክረን ነገር ከሌሎች ሃላፊነታችን ሁሉ ሁሉ አስቀድመን ልዩ ቅድሚያ በመስጠት ሃላፊነታችንን መወጣት ያለብን ነገር እንደሆነ ስናስብ ምክሩን በተጠንቀቅ እንድንሰማው ያስገድደናል፡፡

ምንም ሌሎች ነገሮችን ብናደርግ እንኳን አስቀድመን ማድረግ ያለብንን ይህንን ነገር አለማድረግ ጸጥና ዝግ ብለን የመኖር አላማችንን እንደሚያስተጓጉለው ግልፅ ነው፡፡ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ ማድረጋችን  አስቀድመን ማድረግ ያለብንን ይህን ነገር በፍፁም ሊተካው እንደማይችን እንመለከታለን፡፡ ስለዚህ አስቀድመን ማድረግ ያለብንን ነገር ካላደረግን ሌሎች ነገሮችን ማድርጋችን ብቻ ውጤት እንደማይኖረው በግልፅ እናያለን፡፡

በሚቀጥለው በክፍል ሁለት ፅሁፍ ጸጥ እና ዝግ ብለን እንድንኖር አስቀድመን ምን ማድረግ እንዳለብን እናያለን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa  

 #ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት


 

No comments:

Post a Comment