Popular Posts

Saturday, August 10, 2024

በጣቴ እንኳን ልነካው አልወድም



እግዚአብሔ ሔር የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚወደው እና የማይወደው የተለየ ነገር አለ፡፡ እግዚአብሔር ለህይወታችን የሚፈልገው እና የማይፈልገው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሔር ለህይወታችን ያቀደው የተለየ እቅድ አለ፡፡

በህይወቴ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ተረድቻለው፡፡ ካለ እግዚአብሔር እቅድ ምንም ነኝ ፣ ምንም የለኝም ፣ ምንም ላደርግ አልችልም፡፡

እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። መዝሙረ ዳዊት 16፡2

በህይወቴ ያለው ማንኛውም አቅርቦት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ብቻ የተያያዘ ነው፡፡ እግዚአብሔር በህይወቴ የሰጠኝ ጊዜ ፣ ችሎታ ፣ ስጦታ ፣ ክህሎት ፣ ፀጋ እና ጥበብ ሁሉ ለፈቃዱ ማስፈፀሚያ እንዲውል ብቻ ነው፡፡

ስለዚህ ያለኝን ማንኛውም ስጦታ እና ክህሎት ለእግዚአብሔር  ፈቃድ ካልተጠቀምኩበት አባክነዋለው እንጂ ለምንም አይጠቅምም፡፡

ከፈቃዱ ውጭ የምጠቀምበት ምንም ትርፍ ስጦታ እና አቅርቦት የለም፡፡ እግዚአብሔር የሰጠኝ ስጦታ ለፈቃዱ አያንስም፡፡ እንዲሁም ደግሞ እግዚአብሔር ለፈቃዱ ከምጠቀምበት በላይ ትርፍ ነገር አይሰጠኝም፡፡ ለእግዚአብሔርም ፈቃድ እንዲሁም ፈቃዱ ላልሆነም ነገር የሚበቃ ምንም ትርፍ እቅርቦት የለኝም፡፡  

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማስፈፀም የተሰጠኝን ስጦታ ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ ብቻ ለማዋል እተጋለሁ፡፡ የእግዚአብሔ ፈቃድ እንዳለበት ባረጋገጥኩት ነገር ላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል በሙሉ ልቤ እረባረባለሁ፡፡

በተቃራኒው ደግሞ የእግዚአብሔ ፈቃድ እንዳለበት አጥብቄ ባልተረዳሁበት ነገር ላይ ጊዜዬን ጉልበቴን እውቀቴን አላባክንም፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ የሌለበትን ነገር በጣቴ እንኳን ልነካው አልወድም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ

Abiy Wakuma Dinsa

 #ራዕይ #ምሪት #የእግዚአብሄርአጀንዳ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment