Popular Posts

Thursday, August 15, 2024

ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር ክፍል 2

 

እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡1-2

በማንኛውም የህይወታችን ክፍል  ጸጥና ዝግ ብሎ የመኖሩ ሚስጥር መፅሃፍ ቅዱስ አስቀድመን እንድናደርግ የመከረውን ነገር መተግበሩ ላይ ነው፡፡ 

ጸጥ እና ዝግ ብለን የመኖሩ ሃላፊነት በእኛ ጫንቃ ላይ እንደወደቅ ማወቃችን እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀውን ነገር በማድረግ ፍሬያማ እንድንሆን ያበረታታናል፡፡  

አስቀድመን እንድናደርግ የተመከርነው ነገር ልመናና ጸሎት እንዲሁም ምልጃም ምስጋና ነው፡፡ ልመናና ጸሎት ማድረግ እንዲሁም ምልጃና ምስጋና ማቅረብ የክርስትና ቀዳሚው ሃላፊነታችን ነው፡፡ 

በሰዎች ህይወት ውስጥ የምናያቸው ጉድለቶች መፍትሄው ያለው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡ አይናችንን አንስተን መፍትሄ ወዳለበት ወደ ሰማይ ለለውጥ መጮህ አለብን፡፡ 

ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ። ትንቢተ ኤርምያስ 33፡3

ብዙ ጊዜ ግን መፍትሄን የምንፈልገው መፍትሄ ከሌላቸው ቦታዎች ነው፡፡ መፍትሄ የሌላቸው ለሚመስሉ  ነገሮች ሁሉ መፍትሄ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ነው፡፡ 

እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡1-2

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa 

 #ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት

No comments:

Post a Comment