እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃምምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደጢሞቴዎስ 2፡1-2
መፅሃፍ ቅዱስ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉእንዲደረጉ እያስተማረ ይህንን ምክር እስከማንቀበል ድረስ የምንቃወም ከሆንን ለስጋችን አርነት እየሰጠንእንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
ምክኒያቱም ስልጣን ሁሉ ከእግዚአብሄር ነው፡፡
ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡1
ሰይጣን እግዚአብሄርን አታልሎት የተሾመ ባለስልጣን የለም፡፡ ስልጣን የእግዚአብሄር ስርአት አካል ነው፡፡የማንኛውም ስልጣን አላማ ደግሞ መልካም አስተዳር ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስርአት ደጋፊዎች ነን፡፡ እንደክርስትያን ለዚህ የእግዚአብሄር ስርአት ግብ መምታት ልመናና ፀሎት ምልጃም ምስጋናም ማቅረብ ይገባናል፡፡
ባለስልጣንን በቅድሚያ የምናየው በእግዚአብሄር ስርአት ነው፡፡ ባለስልጣንን የምናየው በመልካነቱ ወይምበክፉነቱ ሳይሆን በእግዚአብሄር ስርአት አስፈፃሚነቱ ነው፡፡
ሃላፊነታችንን ሳንወጣ ብናጉረመርም ምንም የሚመጣ ውጤት አይኖርም፡፡ ነገር ግን ፀጥ እና ዝግ ብለንለመኖር ልመናና ጸሎት እና ምልጃም ምስጋናም ማቅረብ ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት#መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት