Popular Posts

Thursday, November 11, 2021

ብዙ ጊዜ ከምናስበው በላይ ተወደናል አንዳንድ ጊዜ እንደምናስበው በጣም አስፈላጊ አይደለንም

 


ብዙ ጊዜ ከምናስበው በላይ ተወደናል አንዳንድ ጊዜ እንደምናስበው በጣም አስፈላጊ አይደለንም

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡3

አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ከሆነውም በላይ አስፈላጊ እንደሆንን ይሰማናል በዚያም ራሳችንን ከመጠን በላይ ከፍ ከፍ እናደርጋለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሰማይን አምድ ደግፈን እንደያዝን እኛ ብንለቀው ሰማይ እንደሚከሰከስ ይሰማናል፡፡  

አንገስ ቡከን የተባለው የደቡብ አፍሪካው ሰባኪ ሲናገር የራሳችንን አስፈላጊነት በጣም ከማጋነናችን የተነሳ ስንሞት መልከአ ምድር ሁሉ የሚለወጥ ይመስለናል፡፡ ነገር ግን ስንሞት ነገሮች እንደበፊቱ ይቀጥላሉ ይላል፡፡

ለምድር የምናበረክተው ትልቅ አስተዋፅኦ አለ ነገር ግን እኔ ካልሰራሁት እግዚአብሄር አለቀለት የሚል አስተሳሰብ ትክክልኛ አስተሳሰብ አይደለም፡፡ እኛ ግዴታ አይደለንም፡፡ ስንሄድ ሌላ ሰው አለው፡፡ ምንም ባይመስል ሙሴ ሲሄድ እንኳን በኢያሱ ተተክቶ ነበር፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ ጊዜ ከምናስበው በላይ በእግዚአብሄር ወደናል፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር ተረድተን አንጨርሰውም፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ፍቅር የተረዳነው በከፊል ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር እጅግ ይወደናል፡፡

እግዚአብሄር ምን ያህል እንደሚወደን ብንረዳ ጭንቀት ከህይወታችን ፈፅሞ ይሞት ነበር፡፡

ብዙ ጊዜ ከምናስበው በላይ ተወደናል በፍቅሩ እንኑር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደምናስበው በጣም አስፈላጊ አይደለንም ራሳችንን ትሁት እናደርግ በእረፍት እንኑር፡፡

ብዙ ጊዜ ከምናስበው በላይ ተወደናል አንዳንድ ጊዜ እንደምናስበው በጣም አስፈላጊ አይደለንም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #የክርስቶስፍቅር #ስር #መሰረት #ትእዛዝ #መስጠት #ሃሳብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #ደስታ #ሐዋርያ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #መውደድ #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment