I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል። 1ኛዮሐንስ 3:19-20
-
ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 ፣6 7 ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ስለእኛ ነው። ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው እኛ በሃጢያታችን...
-
Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deessi, maqaa isaas Amaanu'el jettee in mo...
-
Name it claim it Take it! “So Jesus answered and said to them, “Have faith in God. For assuredly, I say to you, whoever says to this mount...
-
የብልጽግና ወንጌል ምሥጢር ሲገለጥ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡16 ወንጌል በሃጢያታቸው ምክኒያት ለዘላለም ከእ...
-
ጸሎት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው። ጸሎት ሊደረግ የሚችለው ከእግዚአብሄር ጋር በመግባባት ብቻ ነው። ጸሎት የሚሰምረው እንደ እግዚአብሄር አሳብ ስንጸልይ ብቻ ነው። በአጠቃላይ ለእግዚአብሄር ያለን አመለካከት ...
-
የምንሞትለት እንጂ የምንገድልለት አምላክም ሆነ ሀይማኖት የለንም! አምላክ ሀያል ነው የእኛ እርዳታ አይፈልግም። እንዲገድሉለት የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት እውነተኛ ሀይማኖት አይደለም። የሰውን እርዳታ የሚፈልግ...
-
ብዙ ጊዜ የምናተኩረው በክርስቶስ ስለተደረገልን ነገር ነው፡፡ በክርስቶስ የተደረገልን ነገር ሁሉ ያልለፋንበት ስጦታ ነው፡፡ በክርስቶስ ይህ ሁሉ ነገር ተፈደርጎልንም ለሃላፊነት የማንበቃ ህፃናት ልንሆን እንችላለን፡፡ ...
-
ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙር 50፡23 ምስጋና እግዚአብሄር ስለደረገልን መልካምነት ምላሽ ከመስጠት ያልፋል፡፡ ምስጋና ከእግዚአብሄር...
-
እግዚአብሄር የመርህ አምላክ ነው፡፡ ሰው የልቡ መነሻ ሃሳብ ካልጠራ ፀሎቱ እንደማይመለስ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ የሰው የልቡ መነሻ ሃሳብ ወይም ሞቲቭ ከእግዚአብሄር ሃሳብ ጋረ አብሮ ካልሄደ ፀሎቱ እንደማይመለ...
Sunday, February 7, 2021
Saturday, February 6, 2021
Friday, January 22, 2021
የመተው ባለጠግነት
እግዚአብሄር የመርህ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንድንይዘው የሚፈልገው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሄር እንዳንይዘው እንድንለቀው የሚፈልገው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሄር እንድንለቀው የሚፈልግውን ነገር ብንይዝ እኛ እንጎዳለን፡፡
ሰው አንዴ የያዘውን እግዚአብሄር
ቢያሳየውም ለመልቀቅ የሚያመነታው አንድ ጊዜ ሰርቶለት ስለሚያውቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር በፈጠራ የተሞላ አምላከ ነው፡፡ እግዚአብሄር አንድ መንገድ ብቻ የለውም፡፡ እግዚአብሄር በአንድ
አሰራር ብቻ አይወስንም፡፡
ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡10
ሰው አንዴ የያዘውን ነገር መልቀቅ
የማይፈልገው አጣለሁ ይጎድልብኛል ብሎ ስለሚፈራ ነው፡፡
አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ። ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። የሉቃስ ወንጌል 6፡37-38
እግዚአብሄር በሰው ላይ የያዝነውን
ቂም እንድንተው ሊፈልግ ይችእላል፡፡ እግዚአብሄር ያበደርነውን እንድንተው ሊነግረን ይችላል፡፡ እግዚአብሄር ክስን እንድንተው ሊጠይቀን
ይችላል፡፡ እግዚአብሄር የማይፈልገውን ልምምድ እንዳናደርግ ሊያዝዘን ይችላል፡፡
በምንም መልኩ ይሁን መተው ያለብንን
አለመተው እግዚአብሄር ካሰበልን ከሚበልጠው ነገር ያጎድለናል፡፡
መተው ያለብንን ነገር አለመተው
እግዚአብሄር ወዳሰበልን ወደሚቀጥለው የህይወት ደረጃ እንዳንሻገር ያቆመናል፡፡
መተው ያለብንን ነገር እንደመተው
ያለ ባለጠግነት ደግሞ ከሰማይ በታች የለም፡፡
አግዚአብሄር ተው ይበለን እንጂ
ለመተው ዛሬውኑ መወሰን አለብን፡፡
የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። ወደ ዕብራውያን 10፡34
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/AbiyWakumaDinsa/notes
Abiy Wakuma Dinsa አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
#አዲስፍጥረት #አዲስ #መዋጀት #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #መልቀቅ #አቁማዳ #መተው #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ጌታ #ማሪያም #መላእክት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ሰላም ትግስት #ልጅ
Tuesday, January 19, 2021
Thursday, January 14, 2021
Wednesday, January 13, 2021
አቢይ የጥሞና ቃል #ሰባት የእግዚአብሔር መንግሥት ደስታ
አቢይ የጥሞና ቃል #ሰባት የእግዚአብሔር መንግሥት ደስታ
የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡17
የእግዚአብሄር መንግስት ሁለንተናዋ ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ነው፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት አንዱ ውበትዋ በመንፈስ
ቅዱስም የሆነ ደስታ ነው፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት የመኖር አንዱ እድል
ደስታ በሌለበት አለም ደስታን ማግኘት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት አንዱ ጥቅም በሁኔታዎች ያልተደገፈ ደስተኝነት ነው፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት መልክ ከምንም ነገር ጋር ባልተያያዘ መልኩ በጌታ ደስ መሰኘት ነው፡፡
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡4
አለም በሚያሳዝን ነገር በተሞላች አለም ውስጥ ሃይላችንን የሚመጣው ከእግዚአብሄር ደስታ ብቻ ነው፡፡
እርሱም፦ ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፤ ዛሬ ለጌታችን
የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው። መጽሐፈ ነህምያ 8፡10
እግዚአብሄር ሆይ በልጅህ በክርስቶስ በኩል ስለሰጠኽኝ ደስታ አመሰግናለሁ፡፡ የደስታዬ ምንጭ አንተ ብቻ ስለሆንክ ደስታዬ በምንም ነገር
ስለማይለዋወጥ አመሰግናለሁ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!
#አቢይጥሞና #ሐዋርያውአቢይ #ሐዋርያጥሞና
Tuesday, January 12, 2021
አቢይ የጥሞና ቃል #ስድስት የእግዚአብሔር መንግሥት ሰላም
አቢይ የጥሞና ቃል #ስድስት የእግዚአብሔር መንግሥት
ሰላም
የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ወደ ሮሜ
ሰዎች 14፡17
እግዚአብሄር ንጉስዋ የሆነላትና በመንፈስ በምድር ላይ የምትገዛው የእግዚአብሄር መንግስት ሁለንተናዋ ጽድቅና ሰላም በመንፈስ
ቅዱስም የሆነ ደስታ ነው፡፡
ከጽድቅና ከሰላም በመንፈስ ቅዱስም ከሆነ ደስታ አንፃር ውጭ የእግዚአብሄር መንግስት ልትታይም ሆነ ልትለካ አትችልም፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት ሃላፊነትዋም ጥቅምዋም ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት ዜጎችዋን የምትባርክው በፅድቅ እና በሰላም ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ረብሻ በሞላበት አለም
ለዜጎችዋ ልዩ የሆነ አእምሮን የሚያልፍ ሰላምን በመስጠት ትታወቃለች፡፡
በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤
እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ። የዮሐንስ ወንጌል 16፡33
አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
4፡7
በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ የሚኖር ሰው ብዙ የሚታይ ነገር ላይኖረው ይችላል ነገር ግን ሰላም የእርሱ ነው፡፡ ለእግዚአብሄር
መንግስት የሚገዛ ሰው በመከራ ሊያልፍ ይችላል ነገር ግን ሁለንተናውን አእምሮ የሚያልፍ ሰላም ግን ይቆጣጠረዋል፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት ሰዎች በመጀመሪያ ከፈጠራቸው ከእግዚአብሄር ጋር ጥለኛ አይደሉም በክርስቶስ ኢየሱስ መስቀል ታርቀዋል
ሰላም ናቸው፡፡
ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን





