Popular Posts

Saturday, October 5, 2024

ኢሬቻ እና ክርስትና

 

ኢሬቻ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብሄራዊ ክልላዊ መንግስቱ እንደ ብሄራዊ በአል ሲከበር ቆይቶዋል። በዚህ ጽሁፍ ኢሬቻ ባህል ነው ወይስ ሃይማኖት የሚለው ትንተና ውስጥ መግባት አልፈልግም። እሬቻ ባህል ወይስ ሃይማኖት በሚል ርእስ   ያቀረብኩትን መልክታዬን ሊንኩን ከዚህ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ ትቼዋለሁ። 

ለአንዳንዶች በተለይ የዋቄፈና እምነትን ለሚከተሉ ሃይማኖት ብቻ እንጂ ሌላ ምንም ነገር ሊሆን አይችልም። ለሌሎች  በተለይ የዋቄፈታ እምነት ውጭ ያለን ሃይማኖት ለሚከተሉ ባህል መሆኑ ይታወቃል። 

ባጠቃላይ ኢሬቻ ባህል ነው ወይስ ሃይማኖት ነው ለሚለው ጥያቄ ጥርት ያል መልስ ለመስጠት መሞከር ለውስብስብ ጥያቄ ቀላል መልስ ለመስጠት  እንደ መሞክር ነው።  

ምክኒያቱም በሰው ልጅ ህይወት ባህል እና ሃይማኖት የሚቀላቀልበት ጊዜ ጥቂት አይደለም። ሃይማኖትን የሚጎዳ ባህል እስክሆነ ድረስ ምንም ችግር የለውም።  

በዚህ ጽሁፍ ግን እንደ ክርስትያን ባህልን እስክምን ድረስ ማክበር እንችላለን ለሚለው ጥያቄ በጥቂቱ ለመመለስ መሰረታዊ ነገሮችን ለመጻፍ እሞክራለሁ። 

ክርስትያን ባህልን እስክምን መከተል ይችላል የሚለውን ከመነጋገራችን በፊት ግን ክርስትያን ከዚህ ብታች የተዘረዘሩትን ማወቅ እና መቀበል አለበት በሚለው ሃሳብ አስቅድመን መስማማት አለብን።  

  1. አንድ አውነተኛ አምላክ ብቻ እንዳለ ማመን  

በሰዎች የሚመለኩ ብዙ አማልክት ቢኖሩም እውነተኛው አምላክ አንድ ብቻ ነው። ስለዚህ ወደ እውነተኛው አምላክ አንድ እንጂ የሚያደርስ ብዙ መንገድ የለም።  

እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። የዮሐንስ ወንጌል 17፡3 

  1. እውነተኛው አምላክ የተገለጠው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን ማወቅ 

እውነተኛው አምላክ የተገለጠው ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያት እዳችንን ሁሉ በከፈለው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን ማወቅ አለብን። እውነተኛውን አምላክ የምንገናኘው ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያት እዳችንን ሁሉ በከፈለው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን ማወቅ። 

የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡20 

አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡5 

 

  1. በአለም ላይ ሁለት አይነት መናፍስት ብቻ እንዳሉ መረዳት  

ልዕለ ተፈጥሮአዊ ሁሉ ከእግዚአብሄር አይደለም። የእግዚአብሄር ቅዱስ መንፈስ አለ የሰይጣን እርኩስ መንፈስ አለ። ከሁልቱ ውጭ ገለልተኛ መንፈስ የለም። የእግዚአብሄር ከሆን የሰይጣን አይደለም ከእግዚአብሄር ካልሆነ የሰይጣን ነው።  

እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡12 

በዚህ ረገድ ወደ ክርስቶስ የማያሳይ መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሄር አይልም። ሠው ትኩረቱን ከክርስቶስ ላይ አንስቶ ወደ ሌላ ወደ ምንም ነገር ላይ እንዲያተኩር የሚያደርግ ማንኛውም መንፈስ ከእግዚአብሄር አይደለም።  

  1. የእግዚአብሄር እና የሰይጣን መንፈስ የሚለየው በስራው ነው። 

የአንድ አገር ባህልም ቢሆን ከመጽሃፍ ቅዱስ ጋር ከተጋጨ ባህሉን እንጥለዋለን እንጂ ለጊዜያዊ ባህል ብለን በእግዚአብሄር ቃል ላይ አናምጽም። ቅድሚያ የምንሰጠው የእግዚአብሄርን ቃል እንጂ ባህልን አይደለም። 

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10።10  

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 

ለተጨማሪ ፅሁፎች ኢሬቻ ባህል ወይስ ሃይማኖት? 

https://www.facebook.com/notes/787041595414553/ 

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos 

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መንፈስቅዱስ #ፈትኑ #ባህል #ሃይማኖት #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #እርኩስመንፈስ #ሰይጣን #ኢሬቻ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ኦሮሞ #ዋቄፈታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

 


Thursday, October 3, 2024

ከሁሉ በፊት እመክራለሁ ክፍል 3

 


እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2 


አንደ ክርስትያን የመጀመሪያው ጥሪያችን ጸሎት ነው። ለክርስትያን ለመንግስት መጸለይ በምንም መልኩ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አማራጭ አይደለም።  


የነገስታት አና የመኳንንት የፖለቲካ አቋም እንድንጸልይላቸው እንጂ እንዳንጸልይላቸው ሊያደርገን አይገባም ።  


ክርስትያኖችም ብንሆን የመቃወምም ሆነ የመደገፍም የግል የፖለቲካ አቋም ሊኖረን ይችላል። አንድን የፖለቲካ አቋም መቃወምም መደገፍም ማንም የማይሰጠን ማንም የማይከለክለን ከእግዚአብሄር የተቸረን የህሊና ነጻነታችን ነው።  


ብንደግፍም ብንቃወምም የፖለቲካ አቋማችን ለመንግስታት ግን ከቀዳሚው ጥሪያችን ክመጸለይ ግን ሊያግደን አይገባም።  


በስልጣን ላይ ያለውን የፖለቲካ ድርጅት ብንደግፍም ብንቃወምም ክርስትያናዊ ሃላፊነታችን ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ መጸለይ ነው። 


የትኛውም የፖለቲካ አቋማችን ላለመጸለይ ፈቃድ ሊሰጠን አይችልም።  


እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2 


#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት 


Wednesday, October 2, 2024

ከሁሉ በፊት እመክራለሁ ክፍል 2




እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃምምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደጢሞቴዎስ 2:1-2


በአለም ላይ ሰዎችን ወደ መልካምነት ወደ ፍቅርና ወደ ሰላም የሚመራ የእግዚአብሔር መንፈስ አለ። በአለምላይ እንዲሁ ሰዎችን ወደ ጥፋት እና ጉስቁልና የሚነዳ የሰይጣን ክፉ መንፈስ ደግሞ አለ። 


በእግዚአብሔር ቃል  ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንድንፀልይላቸው የተመከርነውበስልጣን ላይ ያሉት ነገስታቱ እና መኳንንቱ በክፉ መንፈስ ተታልለው ህዝቡን እንዳያጎሳቁሉት ነው። 


ከፀለይንላቸው ክፋት ይጠበቃሉ። ካልፀለይንላቸው በክፋት አገዛዝ ስር በመውደቅ ፍትህ ያዛባሉ፣ የሚመሩትንህዝብ በቅንነት ከማገልገል ይልቅ በስግብግብነት ሰላም እና እረፍት ይነሱታል። 


ምክሩን ተቀብለን ከፀለይንላቸው ግን እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን መኖርእንችላለን።


እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃምምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደጢሞቴዎስ 2:1-2


#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት#መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ክፍል 3 አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

 የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ክፍል 3 አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Tuesday, October 1, 2024

ከሁሉ በፊት እመክራለሁ

 


እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2
ሁላችንም በእግዚአብሄርን ፈቃድ መኖር እንፈልጋለን። ፍቃዱን አገልግለን ማለፍን ዘወትር እንራባለን እንጠማለን። በተለይ በእግዚብሄር ልብ ቅድሚያ የሚሰጠውን ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።
በዚህ ረገድ የአዲስ ኪዳንን አንድ ሶስተኛውን የጻፈው ሀዋርያው ጳውሎስ ከሁሉም በፊት እመክራለሁ የሚለውን ጆሮ ሰጥቶ መስማት ብልህነት ነው፡፡
ሀዋርያው ጳውሎስ ከሁሉም በፊት የሚመክረው ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲጸለይ ነው።
እንደ ክርስትያን ከሁሉ በፊት እንድናደርግ የተመከርነው ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንድንጸልይ ነው።
ክርስትያን ለሀገርና ለህዝብ የተለያዩ ሃላፊነቶች አሉበት። የትኛውም ሀላፊነት ግን ጸሎትን ሊተካው ፈጽሞ አይችልም።  ክርስትያን ለሀገርና ለህዝብ ያሉበት የተለያዩ ሃላፊነቶች ከመጸለይ ሃላፊነቱ በፊት ቅድሚያ ሊሰጣችው ፈጽሞ አይችልም። 
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት