Popular Posts

Monday, July 25, 2022

ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ

 


የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና። ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል። የያዕቆብ መልእክት 1:9-11

ሁላችንም በህይወታችን ከእኛ የሚበልጥ የሚያስመካ ሃያል ነገርን እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን ያስመካል ብለን የምናስበው ነገር ሁሉ የሚያስመካ አይደለም፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ በሚታይ ነገር የተዋረደ ወንድም ሊዋረድ እንደማይገባው ያስተምረናል፡፡ በምድራዊ ነገር ብዙ ነገር የሌለው ሰው በውርደቱ እንዳይዋረድ መፅሃፍ ቅዱስ ያስጠነቅቃል፡፡ በምድራዊ ህይወት ደረጃው ዝቅተኛ የሆነ ሰው ውርደቱን በሚሸፍን በእግዚአብሄር እንዲመካ ያስተምራል፡፡

በምድራዊ ነገር ባለጠጋ መሆን ለመመካት ብቁ ያልሆነ ነገር በመሆኑ በምድራዊ ነገር ባለጠጋ የሆነ ሰው በባለጠግነቱ እንዳይመካ መፅሃፍ ቅዱስ ይመክራል፡፡ ባለጠጋ መመካት ያለበት የሚያስፈልገውን በማያጎድልበት በእግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሄር ነገር ብቻ እንጂ በምድር ላይ ምንም የሚያስተማምን ምንም ቋሚ ነገር የለም፡፡

ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ኢሳያስ 4030-31

No comments:

Post a Comment