ስለገንዘብ የመመካት ስጋዊነት
ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥየለም። 1 ኛ ዮሀንስ 3:15-16
ስለገንዘብ የመመካት ስጋዊነት ከህፃንነት የሚመነጭ የስጋዊነት ሀጢያት ነው::
ስለገንዘብ የመመካት ስጋዊነት የእግዚአብሔርን ፍቅር በአግባቡ ካለመረዳት የሚመጣ አለመብሰል እንጭጭነትነው::
ሰው በእግዚአብሐር የተወደደበትን ጥልቅ ፍቅር ሲረዳ የገንዘብን ትንሽነት እና ውስንነት ስለሚረዳ በገንዘብውይም በኑሮ ከመመካት የስጋዊነት ሀጢያት ይድናል::
ከክፉ የሚጠብቀውን የሚያኖረውን የእግዚአብሔርን ፍቅር በሚገባ የተረዳ ሰው ስለገንዘብ መመካትያሳፍረዋል::
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናውአይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔንበማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር። ኤርሚያስ 9:23-24
ሰው በሚበላው ምግብ ውድነት ከተመካ ስጋዊ ሰው ነው::
ሰው በሚነዳው መኪና ውድነት ከተመካ ስጋዊ ሰው ነው እንጂ መንፈሳዊ ሰው አይደለም::
ሰው ባለመማሩ ካዘነ እና ከተዋረደ መንፈሳዊ ስው አይደለም ማለት ነው::
ሰው ባለው እውቀት ከተመካ ከአለማዊ አስተሳሰብ ያልዳነ ስጋዊ ሰው ነው::
ሰው ባለው ሀብት ከተመካ ስጋዊ ሰው ነው::
ሰው ባለው ዘመድ ከተመካ ስጋዊ ሰው ነው::
ሰው በሚለብሰው ልብስ ውድነት ከተመካ መንፈሳዊ ሰው አይደለም::
ሰው በእግዚአብሔር ሳይሆን በውበቱ ከተመካ እን ደስ ድስ ከተሰኘ ስጋዊ ሰው ነው::
ሰው በድህነቱ ካዘነ እና ከተዋረደ መንፈሳዊ ስው አይደለም ማለት ነው::
በሚኖርበት ቤት ትልቅነት እና ውድነት የሚመካ ሰው መንፈሳዊ አይደለም ማለት ነው::
No comments:
Post a Comment