Popular Posts

Monday, November 14, 2022

የእግዚአብሔር ፈቃድ ወይም ሞት!

 


የእግዚአብሔር ፈቃድ ወይም ሞት!

የተፈጠርኩት ለእግዚአብሔር ክብር እንደሆነ አውቃለሁ፡፡

በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ። ትንቢተ ኢሳይያስ 43፡6-7

በዋጋ እንደተገዛሁ አውቃለሁ፡፡

በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡23

እኔ የራሴ እንዳልሆንኩ አውቃለሁ

በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡20

የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ላረጋግጥ እንጂ ምንም ነገር አደርጋለሁ!

የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ላረጋግጥ እንጂ የፈለገውን ያክል ሞኝ ያስብለኝ እንጅ ምንም ነገር አደርጋለሁ፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ላረጋግጥ እንጂ ተቃውሞ በሁሉም አቅጣጫ ያስነሳብኝ እንጂ ፈቃዱ እንደሆነ ያመንኩበትን ምንም ነገር አደርጋለሁ፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ያላረጋገጥኩት ነገር በወርቅ ቢንቆጠቆጥ ዞር ብዬ እንኳን አላየውም፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ የማንንም እሺታ አልጠብቅም፡፡

ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥ ወደ ገላትያ ሰዎች 1፡15-16

የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ሰዎች የሚያከብሩትን ነገር ሁሉ እንቃለሁ ሰዎች የሚንቁትን ነገር ሁሉ አከብራለሁ፡፡

አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:8-9

የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ላረጋግጥ እንጂ በሁሉም ዘንድ ያስጠላኝ እንጂ ለሚያስከትልብኝ አደጋ ወይም ሪስክ ራሴን እሰጣለሁ፡፡

ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። ወደ ገላትያ ሰዎች 1፡10

የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ላረጋግጥ እንጂ ሁሉን ባጣ እንደክብር እቆጥረዋለሁ፡፡

ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ። መዝሙር 84፡10

የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳለበት ያወቅኩትን ነገር ምክኒያቱ ባይገባኝም እንኳን አብሬው እሞታለሁ፡፡

እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። ወደ ዕብራውያን 11፡13

ለእኔ ሃብት ማለት በእጦትም ቢሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈፀም ነው፡፡ ለእኔ ድህነት ማለት ሁሉም ሞልቶለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ መሳት አለመፈፀም ነው፡፡ ለእኔ ዝና ማለት በመደበቅ እና በመጥፋት የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈፀም ነው፡፡ ለእኔ ዝነኛ አለመሆን ማለት በአለም ሁሉ ተከቦ እና ተደንቆ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መሳት አለመፈፀም ነው፡፡ ለእኔ ሃያልነት ማለት በድካም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈፀም እና ጌታን ደስ ማሰኘት ነው፡፡ ለእኔ ድካም ማለት እጅግ ሃያል ሆኖ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር መተላለፍ ነው፡

ለእኔ ስኬት ማለት አይን ውስጥ የማይገባውን የተደበቀውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈፀም ነው፡፡ ለእኔ ውድቀት ማለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሌለበትን ታላላቅ ነገር ማድረግ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ የሚያስጠላው ያምረኛል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሌለበት የሚያምረው ያስጠላኛል፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ ካለበት የሚመረው ይጣፍጠኛል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሌለበት የሚጣፍጠው ነገር ያቅለሸልሸኛል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 

Friday, November 11, 2022

Don’t dream big for God.


 Don’t dream big for God.

I hear people say, "Dream big for God." I'm telling you never dream big about God. God is not lacking in dreams. God is sufficiently creative to know what He wants of you. God knows why he created you. God knows what brings the greatest glory into your life.

The best thing you can do instead is to discover what goal He has for your life. Leaving your comfort zone to do what He wants you to do beyond your capabilities is the best thing you can do for Him. The best thing you can do is to go beyond your natural boundaries and be in the realm of the supernatural possibility that he shows you. You leave "your ship" to "walk on the water", obedient to the voice of the master.

"Lord, if it’s you," Peter replied, "tell me to come to you on the water." "Come," he said. Then Peter got down out of the boat, walked on the water and came toward Jesus. Matthew 14:28-29

The best risk you can take is obeying the teacher to do the most "strange" thing on earth. The most effective way to take a risk is to stretch yourself to the level of doing the will of God for your life.

Your childhood dream is too small for God. That's not even his dream for you. It isn’t worth living for. Besides, it is a cheap imitation of God's goal in your life.

Dream big with the Lord!

Abiy Wakuma Dinsa

Sunday, October 2, 2022

ርህራሔ የሌለበት የኢሬቻ አስተያየት

 

ርህራሔ የሌለበት የኢሬቻ አስተያየት
ሰሞኑን የኢሬቻ በአል እየተከበረ ይገኛል:: ስለ ኢሬቻ በአል ብዙ አይነት አስተያየቶችን ሰምቻለሁ እንብቤያለው::
አንድ የታዘብኩት ነገር ግን የኢሬቻን በአል ተቃውመው የሚናገሩ አንዳንድ ሰዎች ፍቅርና ትህትና በጎደለው ሁኔታ የበአሉን ታዳሚዎች ሲወቅሱ ማየቴ ነው፡፡  
በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:15
የበፊቱን አላውቅም በአሁኑ ዘመን ከማየው ስነሳ የኢሬቻ በአል ከሀይማኖትነቱ ይልቅ ብሔራዊ ባህልነቱ ያመዝንብኛ፡፡ 
ሀይማኖት ቢኖረንም ባህልም ያለን ባህላዊ ሰዎች ነን:: ሃይማኖትን በማይነካ መልኩ የምናስተናግዳቸው ብዙ ባህሎች አሉን፡፡ ባህል በሃይማኖታችን ላይ ምንም ያህል ተፅእኖ እንዳያደርግ እና የሀይማኖት ህይወታችንን እንዳያዘገይ ወይም እንዳያቆም በኑሮዋችን መጠንቀቅ የእለት ተእለት ሃላፊነታችን ነው:: 
ማንኛውም ባህል እምነታችንን የሚቃወም ከሆነ የትኛውንም ባህል አውጥተን እንጥላለን እንተወዋለን:: ስለ እምነታችን ከእግዚአሔር ቃል ጋር ከማይሄድውን ባህላችንን በደስታ እንተዋለን:: 
እኔን በተመለከተ ስለሀጢያቴ በመስቀል ላይ የሞተውን ሞትን ድል አድርጎ በሶስተኛው ቀን የተነሳውን ኢየሱን ክርስቶስን አዳኝና ጌታ አድርጌ እከተላለው:: ኢየሱስን ለማይከተል ሰው ከዚህ ታላቅ በረከት ስለጎደለ በቅንነት አዝንለታለሁ:: 
ነገር ግን የኢሬቻን በአል በሚያከብር ሰው ላይ ላለመፍረድ እጠነቀቃለው:: የምናገረው ንግግር የዋህነትና ትህትናን ካጣ ከጥቅሙ በላይ ጉዳቱ ያመዝናል:: በፍቅር ያልተደረገ ነገር ከንቱ ነው ምንም አይጠቅምም:: 
በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1ኛ ቆሮንጦስ 13:1-3 
የማንወደውን ሰው ልናገለግለው እንችልም:: እንደ እግዚአብሔር ቃል ያልሆነ ባህል እምነታችንን እንዳይጎዳ መጠንቀቅ ፣ ሌሎችን በየዋህነት እና በትህትና መምከር እንጂ ርህራሔ ያጣ አስተያየት መስጠት ምንም ለምንም አይጠቅምም::
 በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:15
አቢይ ዋቁማዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


Saturday, October 1, 2022

የአዲሱ ኪዳን ፀሎት ትኩረት

 

ክርስቶስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ ከሞተ እና በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ የምንኖርበት ኪዳን በኢየሱስ የተደረገው አዲስ ኪዳን ነው፡፡

ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በሃጢያታችን ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ጠላቶች ነበርን፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያታችን በመሞት ከእግዚአብሄር ጋር አስታርቆናል፡፡ አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ነን፡፡

ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት በብሉይ ኪዳን ለጥቂት ለተመረጡ ሰዎች ይሰጥ የነበረውንም መንፈስ ቅዱስን እርሱን ለተቀበልን ለሁላችንም እንዲሰጠን እና መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን አንዲኖር አስችሎናል፡፡

ከእግዚአብሄር ጋር ጥል በነበሩበትና በክርስቶስ ደም ባልታረቁበት ጊዜ የሚፀለየውን ፀሎቶች በዚህ በአዲሱ ኪዳን ብንፀልይ ውጤታማ አንሆንም፡፡

በአዲሱ ኪዳን የተፀለየውን አንዱን ፀሎት ለምሳሌ ብንወስድ ፀሎቱ የሚያተኩረው ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሰራልንን ስራ በመረዳት ላይ ነው፡፡

የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡17-19

ይህ አይነቱን ፀሎት ፍሬያማ የሚያደርገው በመስቀል ላይ የተሰራውን ስራ እውቅና መስጠቱ ነው፡፡ እንዲሁም ይህን ተሰርቶ የተጠናቀቀውን ስራ በሚገባ እንድንረዳ አይናችን እንዲከፈት እግዚአብሄርን መለመኑ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ የአዲስ ኪዳን ፀሎት እግዚአብሄርን በማወቅ የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጠን ይጠይቃል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa  


 

አእምሮን የሚያልፍ
በእርሱ ከታመንን ከአካባቢያችን ጩኽትና ረብሻ ከፍ ያለ አእምሮን የሚያልፍ ሰላም እንደምናገኝ መፅሀፍ ቅዱስ ይናገራል:: ህይወታችን ሁልጊዜ ጥርት ያለ ቀጥታ መስመር እይደለም:: በህይወታችን ያለውን ነገር ሁሉ አንረዳውም:: ህይወታችን በአእምሮ መርምረን የምንጨርሰው አይደለም:: አእምሮን የሚያልፍ ሰላም ልባችንንና አሳባችንን
መጠበቅ ያለበት ህይወታችን ሁሉንም ጠንቅቀን ከምንረዳው በላይ አእምሮን  የሚያልፍ በመሆኑ ነው:: 
አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።  ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች  4:7
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


Friday, September 30, 2022

እግዚአብሄር ለምን ግድ ይለዋል ?

 

እግዚአብሄር የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለክብሩ ነው፡፡  የፈጠረን እግዚአብሄር በህይወታችን ምን እንደምንሰራ ግድ ይለዋል፡፡ እግዚአብሄር ምን እንደምንሰራ ግድ እንደሚለው ሁሉ ለምን ምክኒያት እንደምንሰራው ደግሞ ግድ ይለዋል፡፡

አንድን ነገር ለማድረግ ያነሳሳን ነገር በተለይም የተደበቀ ወይም ግልጽ ያልሆነ ምክንያት ተነሳሽነት /motive/ ይባላል። ታዲያ የምንሰራውን ነገር ከምንም የልብ መነሻ ሃሳብ ወይም ተነሳሽነት /motive/ እንደሆነ እግዚአብሄር ማወቅ ይፈልጋል፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ምንም መልካም ነገር ብናደርግ ከፍቅር መነሻ ሃሳብ ካላደረግነው ከንቱ እንደሆነ እና ምንም እንደማይጠቅመን ያስተምረናል፡፡ ልብን የሚመዝነው እግዚአብሄር የምናደርገውን ነገር ብቻ ሳይሆን በምን መነሻ ሃሳብ እንደምናደርገው ያያል፡፡ እግዚአብሄር እንድን መልካም ነገርን ስላደርግን ብቻ ጎሽ አይለንም ወይም ደስ አይሰኝም፡፡ በፍቅር ወይም በራስ ወዳድነት ለግል ስማችን ብለን ወይም በፉክክር ስሜት እንዳደረግነው የሰውን ልብ የሚመዝነው እግዚአብሄር ያውቃል፡፡

ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡2-3

መልካሙን ነገር በፍቅር ካላደረግከው እና በጥላቻ ወይም በፉክክር ካደረግከው ተራሮችን በእምነት ስናፈልስ ወንድማችንን ለመጉዳት የወንድማችን መንገድ ለመዝጋት ልናደርገው እንችላለን፡፡

እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡2

በምታደርገው ነገር ልትረካ ሰውንም ልታስደንቅ ትችላለን እግዚአብሄርን ግን በተበላሸ የልብ መነሻ ሃሳብ ባደረግከው ነገር ልታታልለው ወይም ልታስደንቀው አትችልም፡፡

ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡5

ስለዚህ መልካምም ነገር ቢሆን እንኳን የምናደርገው ነገር በምን የልብ መነሻ ሃሳብ እንደምናደርገው ልባችንን መመርመር ከንቱ በሆነ እና በማይጠቅም ነገር ላይ ህይወታችንን ከማባከን ያድነናል፡፡  

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 


Thursday, September 29, 2022

ቅንነትና ንጽሕና እንዳይለወጥ

 


በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡2-3

በምንም መልኩ ይሁን ንፅህና ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡ በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ስለተፈጠረን ንፅህናን እንወዳለን፡፡ ንፅህና ሲጎድል ደግሞ በእጅጉ ደስታችንን እናጣለን፡፡ ሰውነታችን ከቆሸሸ ከምግብ እና ከመኝታ አስቀድመን የምናደርገው ነገር በመታጠብ እንደገና ንፅህናችንን መጠበቅ ነው፡፡ ንፁህ ልብስ ያልለበስን ጊዜ የነበረን ድፍረታችን ሁሉ ይመታል፡፡ ቤታችን ሲመሰቃቀል እና ሲቆሽሽ መልሰን አስክናፀዳው እረፍት እናጣለን፡፡

ይህ ሁሉ ንፅህና በጣም ደስ የሚያሰኝ እና የሚበረታታ ነገር ነው፡፡ እነዚህ የቤት ፣ የገላ እና የልብፅ ንፅህና መጓደል በህይወታችነ ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ አስተዋፅኦ አለ፡፡ ነገር ግን የእነዚህ የንፅህና ጉድለት በህይወታችን ላይ ከሚያሳድረው አሉታዊ አስተዋእፆ በላይ የህይወት ወይም የልብ ንፅህና  መጓደል የሚያስከትለው ጥፋት እጅግ አስከፊ ነው፡፡

ሰው ለልብሱ ለገላው ለቤቱ ንፅህና ከሚጠፋው ጊዜ በላይ በህይወቱ ላይ በብዙ እጥፍ እጅግ ወሳኝ በሆነው በልቡ ንፅህና ላይ የሚያጠፋው ጊዜ እጅግ መብለጥ አለበት፡፡

ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ነው። ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። የማቴዎስ ወንጌል 15፡18-19

ንፅህና እጅግ ትጋትና ክትትል የሚፈልግ ነገር ነው፡፡ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ አፀዳሁት የሚባል ነገር የለም፡፡ አፅድተህ ስትጨርስ ለሚቀጥለው ፅዳት አቅድ ማውጣት ግድ ይላል፡፡ እንደፀዳ የሚቆይ ነገር የለም፡፡ እንዲሁ ከተውከው ምንም ነገር ይቆሽሻል፡፡  

የልብም ንፅህና እንዲሁ ነው፡፡ የልብ ንፅህና በየጊዜው ራሳችንን ማየት መፈተሽ ይጠይቃል፡፡ ትላንት አፅድቼዋለሁ ብለን ብንሰንፍ ወይም ችላ ብንል ከንፅህና እንጎድላለን፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ በየእለቱ ልባችንን እንድንመረምረ ልባችንን እንድንፈትሽ በራሳችን ላይ እንድንፈርድ እና ቶሎ እንድንመለስ የሚያስተምረን ስለዚህ ነው፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ ወደ ዕብራውያን 3፡12-13

ልባቸው እግዚአብሄርን ወደመካድ እና ወደአለማመን የተለወጡ ሰዎች በአንድ ጊዜ እግዚአብሄርን የሚያምኑ መልካም ልብ የነበራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን የልባቸውን ንፅህና ለመጠበቅ ቸልተኛ በመሆናቸው በእኔ ላይ አይደርስም ብለው በትእቢት ስላሰቡ ወድቀዋል፡፡

ሄዋን መልካም ሴት ነበረች፡፡ ሃሳብዋ ቅን ልብዋም ንፁህ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን ቅንነትና ንፅህናዋን የሚጠብቅላትን የእግዚአብሄርን ቃል ከምሰማት ይልቅ የሰይጣንን ቃል ሰማች፡፡ የምትሰማውን ማንኛውም ተቃራኒ ቃል በእግዚአብሄር ቃል ፈትና ከመጣል ይልቅ ታስተናግደው ጀመረች፡፡ የልብንም ስሜትና አሳብ ለሚመረምረው ለእግዚአብሄር ቃል ራስዋን ሙሉ በሙሉ ስላልሰጠች ወደቀች፡፡  

የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።ወደ ዕብራውያን 4፡12-13

የምናስበው ሃሳብ እንደእግዚአብሄር ሃሳብ እንደሆነ ልናደርግ ያሰብነው ነገር በመልካም ልብ አነሳሽነት /motive/ እንደሆነ የልባችንን ንፅህና በትጋት መከታተል ቀዳሚው ሃላፊነታችን ነው፡፡ ቃሉ በሃሳባችን በልባችን መነሻ ሃሳብ ላይ ብርሃን በማብራት ከእርሱ ወይስ ከጠላት እንደሆነ እውነተኛ ማንነቱን ያሳየናል፡፡

ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ። የያዕቆብ መልእክት 1፡21

በኑሮዋችን በስራችን በአገልግሎታቸን እግዚአብሄርን ማየት ከፈለግን በትጋት ልባችንን መጠበቅ የእኛ የዘወትር ግዴታ ነው፡፡

ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና። የማቴዎስ ወንጌል 5፡8

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Saturday, August 27, 2022

ሲሾም ያልበላ

 


እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ አምላክ ነው:: በቅንነት ህዝብን እንዲያስተዳድርና እንዲፈርድ እግዚአብሔር የስልጣንእድልን ይሰጣል:: 


ሰው እግዚአብሄር የሰጠውን ስልጣን ተጠቅሞ የብዙዎችን ህይወት ሊለውጥ ይችላል:: 


አንዳንድ ሰው ግን ከሚከፈለው በላይ መኖር ሲመኝ እግዚአብሔር ብዙ ሰዎችን እንዲባርክበት የስጠውንስልጣን አላግባብ በመጠቀም ህዝብን ያስጨንቃል የማይገባውን ገንዘብ  ይነጥቃል:: 


ማማለጃን አትቀበል፤ ማማለጃ የዓይናማዎችን ሰዎች ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። ዘፅአት28:8


ጉቦኝነት የየዋህነት ተቃራኒ ተንኮለኝነት ነው:: 


በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃ ተሞልታለች። መዝሙር 26:10


ጉቦኝነት በየውሃቴ ሄጃለሁ፤ አድነኝ ማረኝም ብለን እንዳንፀልይ በእግዚአብሔር ፊት ያለንን ድፍረት ይመታል:: 


ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ። በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውምመማለጃ ተሞልታለች።እኔ ግን በየውሃቴ ሄጃለሁ፤ አድነኝ ማረኝም። መዝሙር 26:9-11


ህይወቱን ለማስተካከል ጉቦ የሚቀበል ሰው ተታሏል:: በህይወት የማይታውከው ደሞዜ ይበቃኛል ብሎ ጉቦየማይቀበል ሰው ነው:: 


ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።መዝሙር 15:5


ጉቦ የሚቀበል ሰው ቀለል ያለ ህይወቱን እላግባብ ያወሳስባል:: 


ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል፤ መማለጃን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል። ምሳሌ 18:27


ጉቦ ልብን ያቆሽሻል:: ጉቦ በንፁህ ልብ እግዚአብሔርን እንዳናይ ያደርጋል:: 


ግፍ ጠቢቡን ያሳብደዋል፤ ጉቦም ልቡን ያጠፋዋል። መክብብ 7:7


ሰውን ለመርዳት ጉቦን የሚቀበል ሰው የለም:: ሰው ጉቦ ሲቀበል ጉቦ የሚቀበለውን ሰው ይጎዳል:: ሰው ጉቦሲቀበል የባለመብቱን ፍትህ ያጣምማል:: 


ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። አሞፅ 5:12


ሰው ጉቦ ሲቀበል ለማይገባው ሰው ይፈቅድለታል ይሚገባውን በመከልከል የባለመብቱን ፍትህ ያጣምማል:: 


ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃልያጣምማልና ጉቦ አትቀበል። ዘዳግም 16:19


ጉቦ ፍትህን ያሸጣል:: 


ኀጥእ የፍርድን መንገድ ለማጥመም ከብብት መማለጃን ይወስዳል። ምሳሌ 17:23


ሰው ጉቦ ሲቀበል የማይገባውን ሰው አላግባብ ይጠቅማል:: ሀገር በህግ ሳይሆን በጥቅማ ጥቅም እንድትመራያደርጋል:: 


ሰው በቅንነት ከመፍረድ ይልቅ ጉቦ ሲቀበል ሰው በሰውነቱ እንዳይከበር ጉልበተኛ በጉልበቱ ተመክቶ የፈለገውንእንዲያደር ያደርጋል:: 


አለቆችሽ አመጸኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፥ ዋጋም ለማግኘት ይሮጣሉ፤ ለድሀ አደጉአይፈርዱም፥ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም። ኢሳያስ 1:23


ጉቦ ሁሉም ሰው ሰርቶ እንዳያድግ እና እንዳይለወጥ በተቃራኒው ሌቦችና አጭበርባሪዎች በነፃነት እንዲዘርፉያደርጋል:: ህዝብ ሁሉ እንዲደኸይ ጥቂቶች ብቻ ሃብቱን አላግባብ እንዲያካብቱ ያደርጋል::


ልጆቹም በመንገዱ አልሄዱም፥ ነገር ግን ረብ ለማግኘት ፈቀቅ አሉ፥ ጉቦም እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።1 ሳሙኤል 8:3


የንጹሑን ሰው ነፍስ ለመግደል ጉቦ የሚቀበል ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። ዘዳግም 27:25


እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ክእንግዲህ ወዲህም አንገተደንዳና አትሁኑ። ዘዳግም 10:17


በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸውኢሳያስ 5:23


ጉቦ የሚቀበል ሰው አገሬን እወዳለው የሚለው ውሸቱን ነው:: ጉቦ ቤተሰብን ብሎም እገርን ያፈርሳል::


ንጉሥ በፍርድ አገሩን ያጸናል፤ መማለጃ የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል። ምሳሌ 29:4


ጉቦ የሚቀበል ሰው እግዚአብሔር ቤቴን እግዚአብሔር ይጠብቀዋል የሚለውን ድፍረቱን ያጣል:: 


የዝንጉዎች ጉባኤ ሁሉ ለጥፋት ይሆናል፥

የጉቦ ተቀባዮችንም ድንኳን እሳት ትበላለች። ኢዮብ 15:34 


እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፤ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ። ሚክያስ 7:3


የገንዘብ ፍቅር ያለበት ጉቦ የሚቀበል ኢየሱስ መሞቱን እንኳን ይክዳል::


ከሽማግሎች ጋርም ተሰብስበው ተማከሩና ለጭፍሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋቸው። እኛ ተኝተን ሳለን ደቀመዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ። ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለንእናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን አሉአቸው። እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸውአደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል። ማቴዎስ 28:12-15


ጉቦ የሚቀበል እግዚአብሔር በነፃ የሰጠውን ቸርችሮ የሚበላበት ሰው እግዚአብሔርን አያምንም:: 


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፤ ከዚህምጋር። እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምንክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔርይታመናሉ። ሚክያስ 3:11


ጉቦ የሚቀበል እግዚአብሔር በህዝብ እንዲያገለግል የሰጠውን ስልጣን አላግባብ የሚጠቀም ሰውእግዚአብሔርን የረሳ ነው:: 


በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ጉቦን ተቀበሉ፤ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ከባልንጀሮችሽም በቅሚያየስስትን ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ህዝቅኤል 22:12


እግዚአብሔርን የሚያስደስት ሰው:: 


በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁንየሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቍር፥ ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው።ኢሳያስ 33:15


ያን ጊዜም ደግሞ እንዲፈታው ጳውሎስ ገንዘብ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ አደረገ፤ ስለዚህ ደግሞ ብዙ ጊዜ እያስመጣያነጋግረው ነበር። ሐዋርያት 24:26


ጉቦ የሰጠህ ሰው አንተ ትልቅ ቦታ ላይ ሆነህ በገንዘብ ስለገዛህ በልቡ ይንቅሀል ሳይወድ ስለዘረፍከው ደግሞበልቡ ይረግምሀል:: ሰው ሲረግምህ መንገድህ አይቀናም:: 


በጉቦ የተቀበልከው ጥቅም ላብህ ስላይደለ ያንተ አይደለምና በወጉ አትጠቀምበት:: በንፅህና ስላላገኘህው ኮሽባለ ቁጥር ትደነግጣለህ ኑሮህ የቆቅ ኑሮ ይሆናል::  


ጉቦ አእምሮን ስለሚያበላሽ ከምትጠቀምበት በላይ ስለምትሰበስብ በጉቦ ያገኘኸውን ገንዘብ ለመደበቅ ስትጥርበመሃል ሌላው ይበላዋል:: 


በእጆችህ በመድከም ቀስ በቅስ የተከማቸ ሃብት ስላይደ ለአያያዙን ስለማታውቅበት እንደጠላት ገንዘብትበትነዋለህ:: 


ከደሃ አስጨንቀህ መቀበልህን እንጂ ራስህ እንደምትጠቀምበት እርግጠኛ መሆን አትችልም:: ከድሀ ኪስአውጥተህ ለማንም እንዳይሆን በክንቱ ትበትነዋለህ:: 


ለራሱ ጥቅም ለመጨመር ሲል ድሀን የሚጐዳ፥ ለባለጠጋም የሚሰጥ፥ እርሱ ወደ ድህነት ይወድቃል። ምሳሌ22:16 


ሲሾም ያልበላ በሰላም ይኖራል:: 


አቢይ ዋቁማ ዲንሳ