Popular Posts

Saturday, October 1, 2022

የአዲሱ ኪዳን ፀሎት ትኩረት

 

ክርስቶስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ ከሞተ እና በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ የምንኖርበት ኪዳን በኢየሱስ የተደረገው አዲስ ኪዳን ነው፡፡

ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በሃጢያታችን ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ጠላቶች ነበርን፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያታችን በመሞት ከእግዚአብሄር ጋር አስታርቆናል፡፡ አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ነን፡፡

ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት በብሉይ ኪዳን ለጥቂት ለተመረጡ ሰዎች ይሰጥ የነበረውንም መንፈስ ቅዱስን እርሱን ለተቀበልን ለሁላችንም እንዲሰጠን እና መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን አንዲኖር አስችሎናል፡፡

ከእግዚአብሄር ጋር ጥል በነበሩበትና በክርስቶስ ደም ባልታረቁበት ጊዜ የሚፀለየውን ፀሎቶች በዚህ በአዲሱ ኪዳን ብንፀልይ ውጤታማ አንሆንም፡፡

በአዲሱ ኪዳን የተፀለየውን አንዱን ፀሎት ለምሳሌ ብንወስድ ፀሎቱ የሚያተኩረው ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሰራልንን ስራ በመረዳት ላይ ነው፡፡

የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡17-19

ይህ አይነቱን ፀሎት ፍሬያማ የሚያደርገው በመስቀል ላይ የተሰራውን ስራ እውቅና መስጠቱ ነው፡፡ እንዲሁም ይህን ተሰርቶ የተጠናቀቀውን ስራ በሚገባ እንድንረዳ አይናችን እንዲከፈት እግዚአብሄርን መለመኑ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ የአዲስ ኪዳን ፀሎት እግዚአብሄርን በማወቅ የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጠን ይጠይቃል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa  


No comments:

Post a Comment