ግልፀ ደብዳቤ ለአገልጋይ ዮኒ
በቲክቶክ ላይ በብዙ ሰዎች የተካፈለ እና በከፍተኛ
ሁኔታ የተዘዋወረ ቪድዮ አየሁ፡፡ በቪድዮ ላይ አገልጋይ ዮኒ ፖለቲከኞችን ሚንስቶሮችን እንዴት እንደሚያስተምርና እንሚመክር ይናገራል፡፡
አገልጋይ ዮኒ ስለሙስና እና በስልጣንን ካለ አግባብ
ስለመጠቀም ሲናገር አትበሉም አልልም ትበላላችሁ በማለት ከአንድ የሃይማኖት መሪ የማይጠበቅ የብዙዎች መንፈሳዊ ንፅህና የሚያጎድል
እና ቅዱሳንን ለሰይጣን ጥቃት የሚያጋልጥ ክፉ ምክር ይመክራል፡፡
አትበሉም ብሎ መጀመር ሲኖርበት አትበሉም አልልም
በማለት ማንም ፖለቲከኛ ላይበላ እንደሚችል አምኖ ተቀብሎዋል፡፡ ሰው ፖለቲከኛ ሆኖ ንፁህ ሊሆን እንደሚችል በቃሉ ተስፋ ቆርጦዋል፡፡
አጋልጋይ ዮኒ ከንግግሩ ሰው ፖለቲከኛም የማይሰርቅ ክርስትያንም ሊሆን እንደሚችል አያምንም፡፡ ሰው በተለይም ፖለቲከኛ እና ባለስልጣን
በምድር ላይ ቅዱስ ሆኖ መኖር እንደማይችል ያለውን ተስፋ መቁረጥ በዚህ በተሸናፊነት ንግግሩ ያሳያል፡፡
ይባስ ብሎ ደግሞ "አትብሉ አልልም ብሉ" በማለት ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ጉባኤና ቪድዮ በሚለቀቅበት በመረጃ መረብ ፣ በማህበራዊ
ትስስር ገፆች የእግዚአብሄርን ቃል ለማያውቁ የአስተማሪን ቃል በእግዚአብሄር ቃል መዝነው ለማይቀበሉ ተከታዮች የሌብነት ፈቃድ ይሰጣል፡፡
ሲያስተምር የሚስሙት ሲደነግጡ ሳይሆን ሲስቁና ሲያጨበጭቡ ከጀርባ ይሰማል፡፡ በመረጃ መረብ ላይ በተለቀቀውም የቪድዮ ክሊፕ አስተያየት
ላይ እውነቱን ተናገረ ተብሎ ሲደነቅ አንብቤያለሁ፡፡
የመፅሃፍ ቅሱስ እውነት አትብሉ የሚለው ትእዛዝ
ነው እንጂ ብሉም ፣ ትንሽ ትንሽ ብሉም እንደመፅሃፍ ቅዱስ እውነት ግልፅ የስህተት ትምህርት ነው፡፡
ትንሽ ትንሽ ብሉ ማለት ምን ማለት ነው? ትንሽ
ትንሽ ብሉ ማለት ስንት ብሉ ማለት ነው? ትንሽ የሚለው ቃል ረቂቅና ሊመዘን የሚችል ስላይደለ አሻሚ ቃል ነው፡፡ ትንሽ የሚለው
ቃል ሰው ለስጋው የምኞት ሃጢያት አርነት እንዲሰጥ ከማድረግ ውጭ ሰው ራሱን በመግዛት ለእግዚአብሄር አላማ እንዲኖር አያበረታታም፡፡
ትንሽ ማለት ስንት ነው በመቶዎች በሺዎች በሚሊዮኖች ?
አገልጋይ ዮኒ ከአንድ የሃይማኖት መሪ የማይጠበቅ
የብዙዎች መንፈሳዊ ንፅህና የሚያጎድል ምክር ይመክራል፡፡
አገልጋይ ዮኒ በዚህ ንግግሩ እኔ ቅዱስ ነኝና
ቅዱሳን ሁኑ ከሚለው የእግዚአብሄር ቃል በተቃራኒ ያስተምራል፡፡ አገልጋይ ዮኒ በዚህ ትምህርቱ ራስን ከመግዛት ይልቅ ሰው በህይወቱ
ለሰይጣን ስፍራን እንዲሰጥ የሚያደርግ ጤናማ ያልሆነ ትምህርትን ያስተምራል፡፡
የእግዚአብሄር አገልጋይ የሆነው መጥምቁ ዮሃንስ
ስለባልስልጣኖች ሰልጣናቸውን ካለአግናባብ ሊጠቀሙ ስለሚችሉ ፖለቲከኞችና የአገር አስተዳዳሪዎች የመከረው ምክር አገልጋይ ዮኒ ከመከረው
ምክር ተቃራኒ ነው፡፡
ወታደሮ ደግሞ፣ “እኛስ
ምን እናድርግ?”
ብለው ጠየቁት።
እርሱም፣ “የማንንም ገንዘብ በግፍ
አትንጠቁ፤ ሰውንም
በሐሰት አትክሰሱ፤
ደመወዛችሁ ይብቃችሁ”
አላቸው። ሉቃስ
3:14
ይህ ማለት ግን አገልጋይ ዮኒ ያስተማራቸው ትምህርቶች
ሁሉ ስህተት ናቸው ማለት ግን አይደለም፡፡ ይህ ትምህርት ግን ንስሃንና መመለስን የሚጠይቅ እርሱም በህይወቱ ሊተገብረው የማይገባው
ሌሎችም ሊተገብሩት መምከር የሌለበት የስህተት ትምህርት መሆኑን አውቆ
በግልፅ ንስሃ መግባትና እንደመፅሃፍ ቅዱስ አስተምሮት አስተካክሎ ማስተማር አለበት፡፡
No comments:
Post a Comment