Popular Posts

Wednesday, May 13, 2020

ስጡ


ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። የሉቃስ ወንጌል 638

ይህ የኢየሱስ ንግግር ስለመስጠት እንጂ ስለ መቀበል የተደረገ ንግግር አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ይህን ክፍል ስለመቀበል ይሰብኩታል፡፡ የዚህ የመስጠት ትምህርት አላማ ግን መስጠት እንጂ በፍፁም መቀበል አይደለም፡፡

ሰው ሲሰጥ ወደ አእምሮው የሚመጣ ጥያቄ አለ፡፡ ስሰጥ እኔስ ቢጎድልብኝ የሚል ጥያቄ በሁላችንም አእምሮ ውስጥ ይመላለሳል፡፡

ሰጥቼ እኔስ ቢጎድልብኝ የሚለው ጥያቄ የሚፈጠርብን ምክኒያት ገንዘብ ጊዜያዊም ቢሆን የመተማመን ስሜትን ስለሚሰጠን ነው፡፡  

በአጠቃላይ አለምን የሚያንቀሳቅሰው የእግዚአብሄር ፍቅር ወይም የገንዘብ ማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ሰው እንዳያጣ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። የማቴዎስ ወንጌል 6፡31-32

ሰው ገንዘቡን ለመስጠት የሚገዳደረው ምክኒያት ገንዘብ የመተማመን ስሜትን በሰው ውስጥ ስለሚፈጥር ነው፡፡  

ታዲያ ገንዘባችንን ስንሰጥ የምንሰጠው መተማመኛችንን ነው፡፡ ገንዘባችንን ለመስጠት ከገንዘብ በላይ የምንተማመንበት እግዚአብሄርን ማመን ይጠይቃል፡፡ ገንዘብ ለመስጠት ከሚታየው ያለፈ የእግዚአብሄርን መንግስት አሰራር በእምነት አይን ማየት ይጠይቃል፡፡ ገንዘብን ለመስጠት የእግዚአብሄርን ቃል ማመን ይጠይቃል፡፡  

ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡10

ስጡ ብሎ ኢየሱስ ይሰጣችኋል ያለበት ምክኒያት በሰው ውስጥ የሚነሳውን ሰጥቼ ቢጎድልብኝስ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው፡፡ ስጡ ብሎ መልሱ ባጣስ ለሚለው ጥያቄ መልሱ ስለሰጣችሁ አይጎድልባችሁም የሚለው ነው፡፡ ስለሰጣችሁ አታጡም ስለሰጣችሁ አትከስሩም፡፡

ይህንም እላለሁ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡6

ስትሰጡ ይሰጣችሁዋል፡፡ ስትሰጡ ይጨመርላችሁዋል፡፡ ስትሰጡ ይበልጥ ይሰጣችሁዋል፡፡

ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። የሉቃስ ወንጌል 6፡38

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #መዝራት #ማጨድ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ


No comments:

Post a Comment