I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ያልተጋባች ሴትና ድንግል 1 ኛ ቆሮንጦስ 7:34 ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ ...
-
የምንሞትለት እንጂ የምንገድልለት አምላክም ሆነ ሀይማኖት የለንም! አምላክ ሀያል ነው የእኛ እርዳታ አይፈልግም። እንዲገድሉለት የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት እውነተኛ ሀይማኖት አይደለም። የሰውን እርዳታ የሚፈልግ...
-
ኢየሱስ በስጋ ወደምድር ከመምጣቱ በፊት ብሉይ ኪዳን ' የጉብኝት ባህል ' እና በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የተደረገው አዲስ ኪዳን ግሞ ' የ መ ኖር ባህል ' ተብሎ ...
-
♫ Fikiru Nektogn, Vol. 3 - Solomon Yirga. Listen @cdbaby : Click to listen at CDBaby
-
Video Transcript: In the far east they have something that’s call the Chinese bamboo tree. The Chinese bamboo tree takes five years to ...
-
በህይወታችን በፍፁም መሳተፍ የሌለብን መልካም ያልሆኑ የገድል አይነቶች አሉ፡፡ እንደ እነዚህ አይነት የገድል አይነቶች ውስጥ መሳተፍ አላስፈላጊ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡ በተሳሳተ ገድል ላይ መካተት ህይወታችን ፍሬ ቢስ እን...
-
ሚስት ከባል ልዩ ፍቅር ትፈልጋለች ። ሰው ውስን ነው ። ሰው ሁሉን ነገር ማድረግ አይችልም ። ሰው ከሚስቱ ጋር ለመጣበቅ ልዩ ትኩረት ያስፈልገዋል ። ሰው አባቱንና እናቱን ሳይተው ...
-
የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ነገር የመስራት እና የመለወጥ አቅም አለው። ያዕቆብ 5:16 … የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሀይል በፀሎታችን አይወሰንም። እግዚአብሔር ከምንለምነው ...
-
https://youtu.be/hF7MnU_o36Y?si=75Hl88sHQkHj597v
Sunday, September 6, 2020
ህይወት ልንደሰትበት የሚገባ የእግዚአብሄር ስጦታ
ህይወት
ትልቅ ሃላፊነት ነው፡፡ የተፈጠርንበትን አላማ ለመኖር ትልቅ ትጋት ይጠይቃል፡፡
ህይወት ጥንቃቄን የሚጠይቅ የቤት ስራ ነው፡፡ ህይወት ትልቅ ሃላፊነትን የሚጠይቅ ሸክም ነው፡፡
ህይወት
ደግሞ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ ህይወት ሸክም ብቻ ሳይሆን ልንደሰትበት የሚገባ የእግዚአብሄር በረከት ነው፡፡ በህይወት በመኖራችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ በመስራታችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ እግዚአብሄርን በመፍራታችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ ለእግዚአብሄር መንግስት ዋጋ በመክፈላችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ እግዚአብሄር እምላካችን ስለሆን ልንደሰት ይገባል፡፡ ለእግዚአብሄር ነገር ታማኝ
በመሆናችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ ለእግዚአብሄር ስራ በመትጋታችን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ ካለፍርሃት በደስታ እንድናገለግለው ሰጥቶናል፡፡
በእርሱም
ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን። የሉቃስ ወንጌል 1፡74-75
ሰይጣን
እንደሆነ የሚለው ምንም ነገራችን በቂ አይደለም ነው፡፡ ለሰይጣን ምንም ነገራችን አያምረውም፡፡ የሰይጣን አላማ እኛን ማሰናከል ስለሆነ ለሰይጣን ምንም ነገራችን አበቃውም፡፡ ለሰይጣን ምንም ነገራችን አይጥመውም፡፡ የሰይጣንን ነገር እየሰማን በላያችን ላይ ልንከፋ አይገባም፡፡
እግዚአብሄር
ደግሞ ከእኛ ብዙ ነገር አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው በመጨረሻ እንድምንጠየቅ አድርገን ብቻ እንድንወጣና ህይወታችንን በደስታ እንድንኖር ብቻ ነው፡፡
የነገሩን
ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መጽሐፈ መክብብ 12፡13-14
እግዚአብሄር
እንድንደክም ብቻ ሳይሆን በድካማችን ደስ እንዲለን ይፈልጋል፡፡ ህይወት ሸክም ብቻ ሳይሆን ስጦታ መሆኑን አውቀን እንድንደሰትበት የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡
ህይወትን
እንደሸክም ብቻ በሚያየው ሰው እና እንደስጦታ በማይደሰትበት ሰው እግዚአብሄር አይደሰትበትም፡፡ ህይወትን እንደሸክም ብቻ የሚያየው ሰው እና እንደስጦታ የማይደሰትበት ሰው በህይወቱ ስኬታማ አይሆንም፡፡ ህይወትን እንደሸክም ብቻ የሚያየው ሰው እና እንደስጦታ የማይደሰትበት ሰው በሚዛናዊነት ስላልያዘው ብዙም አይዘልቅም፡፡
ተቈጣም
ሊገባም አልወደደም፤ አባቱም ወጥቶ ለመነው። እርሱ ግን መልሶ አባቱን፦ እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት እንደ ባሪያ ተገዝቼልሃለሁ ከትእዛዝህም ከቶ አልተላለፍሁም፤ ለእኔም ከወዳጆቼ ጋር ደስ እንዲለኝ አንድ ጥቦት ስንኳ አልሰጠኸኝም፤ የሉቃስ ወንጌል 15፡28-29
የአባቱ
መልስ ግን ለእኔ ለአባትህ መኖር በአባትህ እንዳትደሰት ሊያደርግህ አይገባም ነበር የሚል መልዕክት ያለው ነበር፡፡
እርሱ
ግን፦ ልጄ ሆይ፥ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፥ ለእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፤ የሉቃስ ወንጌል 15፡31
እግዚአብሄር
ሲባርክ የሚባርከው በትጋትና በደስታ ነው፡፡ ደስታ የሌለው ትጋት አሰቃቂ ነው፡፡ የህይወትን ሸክም የሚያቀለው የልባችን ደስታ ነው፡፡
እነሆ፥
እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ እድል ፈንታው ነውና። እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። እግዚአብሔር በልቡ ደስታን ስለ ሰጠው እርሱ የሕይወቱን ዘመን እጅግ አያስብም። መጽሐፈ መክብብ 5፡18-20
ዛሬ
አሁን ባለንበት በዚሁ በደረስንበት ደረጃ በእግዚአብሄር ስጦታ በህይወት መደሰት ካልቻልን የሆነ ያልገባን ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ህይወት ሸክም ብቻ ሳይሆን እያንዳንዷን ደረጃና ዝርዝር ልንደሰትበት የሚገባ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡
ከሚበላውና
ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል። መጽሐፈ መክብብ 8፡15
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ብልፅግና #መደሰት #ስኬት #ህይወት #ስጦታ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #ሃዋርያውአቢይ #አቢይዋቁማ #ሃዋርያውአቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #ማስተዳደር #እረፍት
Saturday, September 5, 2020
Friday, September 4, 2020
Thursday, September 3, 2020
የተሸነቆረ ሸክላ
እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት አምነን የዳንን ሁላችን እግዚአብሄር በምድር ላይ ለሰጠን የቤት ስራ በእግዚአብሄር መንፈስ ተቀብተናል፡፡ ካለ እግዚአብሄር መንፈስ እርዳታ የእግዚአብሄርን ስራ መስራት አይቻልም፡፡ የእግዚአብሄር አላማ በምድር ላይ መፈፀም ካለበት የእግዚአብሄር መንፈስ አብሮን ሊሰራ ይገባዋል፡፡
በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡21
ታዲያ
ችግሩ ቅባቱን ጠብቆ ለሚፈለገው አላማ ማዋል እንጂ መቀባቱ አይደለም፡፡ ምንም ያህል ብንቀባ ቅባቱን በመልካም የእግዚአብሄራዊ ባህሪ
ጠብቀን ካላቆየነው ለታለመለት አላማ ሊውል አይችልም፡፡
የቅባቱ
መያዣ ሸክላው በባህሪ ጉድለት የተሸነቆረና በክርስቶስ ባህሪ ካልተጠበቀ በስተቀር ቅባቱን ያባክነዋል፡፡
እግዚአብሄር
ብዙ ጊዜ የሚፈጅበት እኛን መቀባት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ብዙ ጊዜ የሚፈጅበት የተቀባነውን ቅባት ለረጅም ጊዜ አቆይተን ለታለመለት
አላማ ሁሉ መጠቀም እንድንችል የቅባቱን መያዣ ሸክላውን መስራት ነው፡፡ እኛን መቀባት ለእግዚአብሄር የሰከንድ ስራ ነው፡፡ ነገር
ግን የቅባቱን አስተዳዳሪ እኛን እግዚአብሄርን በመምሰል መስራት ግን
የብዙ ጊዜ ስራ ነው፡፡
ህይወታችን
ትእግስት ፣ የዋህነት እና ፍቅር ከጎደለው የተቀባነውን ቅባት ለታለመለት አላማ ሳይውል እናባክነዋለን፡፡
ስለዚህ
ነው ቅባት ወደከፍታ ይወስድሃል ባህሪ በከፍታው ላይ ይጠብቅሃል የሚባለው፡፡
ብዙ
ሰዎች ግን ስለመቀባታቸው ሃይል ስለማግኘታቸው እንጂ ሃይሉን ለረጅም ጊዜ ስለሚያቆየው ስለባህሪያቸው አያስቡም፡፡ እኛ መቀባት ከምንፈልገው
በላይ እኛ እንድንቀባ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ የእኛ ድርሻ ቅባቱን ለረጅም ጊዜ እና ለታለመለት አላማ ሁሉ ለመጠቀም የሚያስችለንን
የቅባቱን መያዣ ባህሪያችንን በእግዚአብሄር ቃል ለመስራት እንትጋ፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #ቅባት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ሃይል #ሰላም #ደስታ #ሃዋርያውአቢይ #ሃዋርያውአቢይዋቁማ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #የዋህነት #ትግስት #መሪ






