Popular Posts

Sunday, February 13, 2022

የፍቅር ምንጭ

 


ስለ ፍቅር ብዙ ይዘከራል ይወራል፡፡

ሁሉም ሰው ይህ የሚዘመርለትንና የሚሰበክለትን ፍቅር ማወቅ ፣ መኖር እና ማጣጣም ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ወደ ተግባር ሲመጣ ፍቅር በተግባር ሊተረጎም የማይችል ረቂቅ ነገር ብቻ ይሆንበታል፡፡

ሰው ደግሞ እውነተኛውን ፍቅርን ካልተረዳ ተመሳሳዩን ምኞትን እንደፍቅር ይዞት ባነሰ ነገር ረክቶ ይኖራል፡፡

ፍቅር ግን ምኞት አይደለም፡፡ ፍቅር ስሜት አይደለም፡፡ ፍቅር ከፍ ያለ የህይወት ደረጃ ነው፡፡

ስለፍቅር የሚናገሩትን መፅሃፍት በማንበብ ፍቅር አይመጣም፡፡ ፍቅር ከሰው አይመጣም፡፡ ሰው ራሱ ፍቅርን የተራበ እና ፍቅር የሚያስፈልገው ፍጥረት ስለሆነ ፍቅርን በራሱ ሊሰጥ አይችልም፡፡

ፍቅር የሚመጣው ፍቅር ከሆነው ከእግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። 1ኛ ዮሐንስ 4፡16

ፍቅርን ሊያውቅ በፍቅር ሊኖር የሚችለው በእግዚአብሄር የሚኖር ሰው እግዚአብሄርም በእርሱ የሚኖርበት ሰው ብቻ ነው፡፡

ሰው ፍቅርን ከእግዚአብሄር ካላገኘ ምኞትን እንጂ ፍቅርን በፍፁም ሊያውቀው አይችልም፡፡  

ሰው ከእግዚአብሄር ፍቅርን ካልተቀበለ ፍቅርን ተቀብሎ አያውቅም፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ፍቅር ጉልበት ካላገኘ በእውነተኛ ፍቅር ሌላውን የሚወድበት አቅም አይኖረውም፡፡  

ሰው ምክኒያታዊ ያልሆነውን እውነተኛውን ፍቅርን መማር የሚችለው ፍቅር ከሆነው ከእግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሄርን ፍቅር የቀመሰ ሰው ብቻ እውነተኛውን ፍቅር ያውቃል፡፡

የእግዚአብሄርን ፍቅር የቀመሰ ሰው ብቻ የተቀበለውን ፍቅር ለሌላው መስጠት ይችላል፡፡

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።  ሮሜ 5፡5

በእግዚአብሄር ፍቅር የረካ ሰው ብቻ ሌላውን ሰው በፍቅር ሊያረካ ይችላል፡፡

ሰው የእግዚአብሄርን ፍቅር በተቀበለ መጠን የእንካ በእንካ ያልሆነውን ፍቅር ለሌላው መስጠት ይችላል፡፡

Abiy Wakuma Dinsa አቢይ ዋቁማ ዲንሳ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #ስር #መሰረት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ከቅዱሳንሁሉጋር #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment